0
0
Read Time:36 Second
የጎንደር ማረሚያ ቤት በእሳት ቃጠሎ መያያዙ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል ። ምንጩ በአልታወቀ ምክንያት የእሳት አደጋው እንደተፈጸመበት ጠእቁሞ ይህ ማረሚያ ቤት አንጋፋ ተብለው ከሚጠሩት የማረሚያ ቤቶች አንዱ የሆነው የጎንደር ማረሚያ ቤት በዛሬው እለት በእሳት አደጋ ከፊሉ የወደመ ከመሆኑ የተነሳ በቃጠሎው ሳቢያ በውስጡ ይገኙ የነበሩ ታራሚዎች ለማምለጥ ሞክረዋል ቀሪዎቹም በቁጥጥር ስር ውለዋል እንዲሁም ህዝቡ ከታራሚው ጎን በመቆም እንዲጠፉ ሲተባበሩ ነበር ሲሉ በስፍራው የነበሩት ባልደረባዎቻችችን ጠቁመዋል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከ300 በላይ እስረኞች የአጥሩን ግንብ ዘለው ለማምለጥ የሞከሩ ሲሆን ፣የአካባቢው አስተዳደር ታራሚዎቹን ለመፈለግ አሰሳ ላይ እንዳለ ጠቁሞአል ።
በአሁን ሰአት በመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም ህዝባዊ ሰራዊት እና የማረሚያ ፖሊሶች በጋራ አካባቢውን ከበው በመጠበቅ ላይ የሚገኙ ሲሆን የአካባቢውም ህብረተሰብ የእሳት አደጋውን ወደ ሌሎች የማረሚያ ክፍሎች እንዳይዛመት ሲሉ ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን አይዘነጋም ሲል በስፍራው የተገኘው ሪፖርተራችን በቃሉ አሰፋ አስታውቆአል ።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating