በአዲስ አበባ የከፍተኛው ፌደራል ፍርድ ቤት 19ኛው ምድብ ችሎት ባሳለፈው ችሎት መሰረት 5 የኦሮሚያ ተማሪዎችን በጥፋተኝነት የወሰነ ሲሆን ስድስተኛውን ተከሳሽ የዋስትና ካሳ ክፍያ ከፍሎ እንዲወጣ ወስኖበታል።
እንደ ፍርድቤቱ ውስኔ መሰረት የጥፋተኝነት ተከላካይ የነበረው አበበ ኡርጌሳ የጥፋተኝንት ክሱ የተመሰረተበት በሽብር ወንጀል በአንቀጽ 3 ሲሆን ሁለተኛው ተከሳሽ ሶስተኛው እና አራተኛው ተከሳሽ ተማሪዎች መገርሳ ወርቁ ፣አዱኛ ኬሶ እና ቤልሱማ ዳማና የጥፋተኝንት ወንጀለኝነታቸው የተነገራቸው በሽብር ወንጀል 7/1 መሰረት ሲሆን ጥፋተኛ ተብለው ተወንጅለዋል አምስተኛው ተከሳሽ የሆነው ተሾመ በቀለ በ ሽብር ወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 257/ሀ መሰረት ህጉን በመጣሱ ምክንያት የፍርድ ማቅለያ ተደርጎለት ክሱን ለሰሚ ችሎት ፍርድ በት በማቅረብ እንደገና እንዲታይለት የታዘዘለት ከመሆኑም በላይ የዋስትናው መብቱ የተጠበቀለት እንደሆነ እና የተጠየቀውን ዋስትና የሚያቀርብ ከሆነ ከወንጀሉ ነጻ ሆኖ ከእስር ቤት ሊወጣ እንደሚችል ፍርድቤቱ አሳስቦ ፋይሉን ዘግቶአል ። በሌሎቹ የኦሮሚያ ከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ላይ የተደረገው ውሳኔ ፣አዲስ አበባን በኦሮሚያ ክልል ማካለል የሚል እና የኦሮሞ ቋንቋ የሃገሪቱ ዋነኛ ቋንቋ እንዲሆን ህብረተሰቡን ግፊት ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው ይህ ደግሞ ህገ መንግስቱንም ተጻረዋል የሚል ክስም ሳይቀርብባቸው እንዳልቀረ ተጠቁሞአል ።
ሌሎች በዚህ ክስ ላይ ያልተጠቀሱ 4 ወንጀለኞች ለተለዋጭ ቀጠሮ ጉዳያቸው እንዲታይ ፍርድቤቱ የወሰነ ሲሆን ሁሉም ወንጀለኞች የመከላከያ መረጃቸውን ማቅረብ እንዲችሉ ፍርድቤቱ አዟል ችሎቱንም ለጥር 10 2008 አዘዋውሮአል።
Average Rating