www.maledatimes.com የማለዳ ወግ …የጀግና ልጅ ልደቱ በሀዘንና በመከራ ይከበራል ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማለዳ ወግ …የጀግና ልጅ ልደቱ በሀዘንና በመከራ ይከበራል  !

By   /   August 3, 2016  /   Comments Off on የማለዳ ወግ …የጀግና ልጅ ልደቱ በሀዘንና በመከራ ይከበራል  !

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 20 Second
habtamu_and_daughter

habtamu and daughter

*   እንኳንም ተወለድሽ ህፃን ኤማንዳ ሐብታሙ

ዛሬ የወጣቱ አባዎራ ሐብታሙ የአብራክ ክፋይ ህጻን ኤማንዳ ሐብታሙ  4ኛው ዓመት የልደት ቀን መሆኑን ስሰማ ከልብ የመነጨ መልካም ምኞቴን ለመግለጽ ፣ ብሎም በህግ ሽፋን በአቧቷ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በማውገዝ እንደ ዜጋ ማለት የምለውን ማለት ፈለግኩ  !

በሰለጠነው በእኛ 21ኛ ክፍለ ዘመን፣  በእኛ ሀገር ፣ ለሀገራቸው መጻኤ ህይዎት ለፍትህና ዲሞክራሲ መከበር ተግተው መጨረሻቸው መሳደድ ፣ መታሰር መገረፍና መሞት እጣ ፈንታቸው የሆነ ትንታግ ዜጎች እውቃለሁ ። ይህን ሁሉ አደጋ እየተመለከቱ ጥቂቶች የወጣትነት ለጋ እድሜያቸው በቀሰሙት እውቀት ለመደገፍ ሽተው ተደናቅፈዋል፣ እየተደናቀፉም ነው ። እንደ ሰው ሀብት ንብረት ከማካበት የወጣት ጎልማሳነት እድሜያቸውን ለፍትህ ነጻነት ሲታገሉ ከባድ መስዋዕት ሲከፍሉ  ከቤተሰብ ሀላፊነት ባሻገር የሀገርና የህዝባቸውን ነገር አንገንግቧቸው ” እኔም ለሀገሬ ” በሚል የከፈሉትንና እየከፈሉት ያለው የከበደ መስዋዕትነት የሚዘነጋ አይሆንም !

ከምንም በላይ ለዘመናት የሀገርና የህዘብን ኑሮ እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ እየጎተተው ያለውን የሀገራችን በአንባገነኖች የሚዘዎር ፖለቲካ ለመቀየር ትግል ከተጀመረ ከራረመ ። ውጤቱ አመርቂ ባልሆነው ፖለቲካውን በሰላማዊ መንገድ ለመቀየር የሚደረገው ትግል ውስብስብ በሆነበት ሰአት መድረሳችን ያሳዝናል!  መሳሪያ ሳያነግቡ ሀሳናቸውን በአደባባይ በመግለጽ የተሰለፉት ወገኖች እየደረሰባቸው ያለውን ጫና ለመረዳት ብዙ ርቆ መሔድ አያስፈልግንም ። የቅርብ የዛሬ ህያው ምክስራችንና ዋቢያችን በወህኒ ቆይታው በጠና ታሞ  የሚንከላዎሰው ወጣቱ ፖለቲከኛ ሐብታሙ አያሌው ይጠቀሳል …

ዛሬ  ህጻን ኤማንዳ የ4ኛ ልደቷን ስታከብር እንደ ህጻናት አባቷና እናቷ አጅበዋት ሻማ ለማብራት አልታደለችም ፣ ኤልማንዳ  አባቷ ሐብታሙ አንድ ልጁን  ከጎኗ ሆኖ ማድመቁ ቢቀር እሷ ስትደሰት እሱ ህመም ስቃዩ ፈውስ አግኝቶ ” እንኳን አደረሰሽ !” ለማለት አልታደለም  🙁 እናም ኤማልዳ በአባቷ ህመም በሀዘን ተሞልታ የዛሬ ልደት የምታከብር ምንዱብ ሆናለች ፣ የሀገሬ ፖለቲካ ፣ የሀገሬ አምባገነኖች አቧቷን የሚቀልዱበት የኢትዮጵያ ተገፊ ህጻን ኤማንዳ  🙁 ታሳዝናለች ፣ እኛም እናሳዝናለን  🙁

እንደ ሀብታሙ ሁሉ ለሀገራችንና ለህዝባችን ያገባናል ያሉ ዜጎች ግፍ በሚፈጸምባቸው ዜጎች ቁጥር የትየለሌ እየሆነ መምጣቱ ያማል: ( ልጆችና ቤተሰብ ደግሞ የግፉ ዳፋ ቀማሾች ሆነዋል  !  የግል ጥቅምን ከማስቀደም ሀገሬ ብለው ያስተማራቸውን ወገንና ሀገር ለመታደግ በተነቃቁ ፣  ተምረው ተመራምረው ለሀገራቸው እድገት ግብአት የሚሆን ህልም በሰነቁ  ፣ ጥቂት የማይባሉ ዜጎች ፍትህ ተነፍጓቸዋል ፣ ብዙዎች በፍርደ ገምድል የፍትህ አሰጣጥ አመታትን በወህኒ ያሳልፉ ዘንድ ግድ ሆኗል  !  የትንታግ ወጣት ጎልማሶችና አባት ፖለቲከኞች መጨረሻቸው ስቃይ ፣ መከራና መገፋት ሆኗል …

ወጣቱ አባዎራ ሐብታሙ ከሀገር ወጥቶ ህክምና እንዲያገኝ ተወትውቶ የተሰየሙት የፍትህ አካላት ጉዳዩን የሚያዩበት አይን አሳዛኝ  ሆኗል ። ወጣቱ የቤተሰብ ኃላፊ በህመም  ተቀስፎ እየተሰቃየ የዳኞች አለመሟላት ፊዝ ይመስላል ፣ የቀጠሮው መደራረብም ወጣቱን ፖለቲከኛ ሀገሬው ” ፖለቲካ ኮረንቲ ነው! ” ብሎ እንዲርቅና ሐብታሙን  መቀጣጫ ለማድረግ የተወጠነ የፖለቲከኞች  የበቀል ሴራ ካልሆነ መልካም ነው  !

ዛሬ በዚህች ቀን ፍትህ ባይዘገይ ኖሮ በፍትህ ሥርአት ሐብታሙ አቅርብ ያለውን የዶክተሮች ምስክርነት ተቀብሎ ወደ ውጭ በላከው ነበር ፣ ስብዕና ቀድሞ ፣ ፍትህ በተግባር ማየት እውን ቢሆን ኖሮ ሐብታሙ በውጭ ሐገር ህክምናውን ከውኖ ለልጁ መልካም ምኞቱን ለአውሮፖ ይሁን ከእስያ ባንዱ የአለም ክፍል ” ልጀ ኤልማዳ እነሆ ተሽሎኝ እያገገምኩ ነው! ስላንችና ስለ ቀሩት የሀገሬ ቀጣይ ትውልድ ሰላማዊ ተጋድሎየን እቀጥላለሁ!  ያኔ ልደትሽ ደምቆ ከኢትዮጵያ ጋር ይከበራል  !” ይላት እንደነበር ሳስበው በዘገየው ፍትህ አዝናና ነፍሴ በሐዘን ትታወካለች   🙁

በዘገየው ፍትህ ተስፋ ያልቆረጠው ጀግና ግን ዛሬም ይናገራል …በልጁ ልደት ዋዜማ በሚጠዘጥዘው የቁስል ህምም የሚሰቃየው ወጣቱ ተገፊ ፖለቲከኛ ሀብታሙ እኩለ ሌሊት ላይ  ሊጠይቁት ለሄዱት ወዳጆቹ ለእነ አይታክቴው ጋዜጠኛ ኤልያስና ዳንኤል እንዲህ ነበር ያላቸው  ”  ለእኔ ከሀገር ወጥቼ እንዳልታከም እንዲህ በኢህአዴግ የተጨከነብኝ የውክልና ሞት ስለተፈረደብኝ ነው። በእኔ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ፣ በእኔ ብቻ ሳይሆን በሚሊየኖች ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ይገባኛል።” ነበር ያለው ፣ እሱ ስለ እውነትም እንደሚሰራበት ደባ ሐብታሙ ግን በሕይወት ይኖራል ፣  አልጠፋም ፣ ይህ በፈጣሪ የተጣለ ተስፋችን ነው ፣ በፈጣሪ እንጠበቃለንና  !

እየሆነ ያለው ሁሉ ቢያምምን ፣ ህመሙ እንደ ታማሚው ወንድም  ጠዝጥዞን እንደ ዜጋ ያማል ፣ ያማል ብንልም ዳሩ  በሐብታሙና በቤተሰቡ ላይ የሚፈጸመው በደል አያልፍ የለም ያልፋል !  እሱም በተባ አንደበቱ እንዳለው እመኑኝ እንኳንስ ኢህአዴግ ደርግም ወድቋል !

አዎ  ! ፍትህ በተግባር የምናይበት ብሩህ ቀን  ናፍቆናል ፣ ዛሬ መካከል ፍንጣቂ ብርሃን እያየን የሰላማዊው ትግል ጀግና አርበኛው የሐብታሙ አያሌው ልጅ ኤማንዳና የመሰሎቿ ግፉዕ ዜጎች ልደት በአርበኝነት ታጋድሎ እየተወደሰ ደምቆ ይከበራል እያልን ምኞታችን እንገልጻለን  ! እስከዚያው ግን ጨቋኝ አገዛዝ በነገሰበት ሰማይ ስር ጊዜው የፈቀደው የጀግና ልጅ ልደቱ የሚከበረው እንዲህ በሀዘንና በመከራ ሆኗል ፣ የጀግና ልጆች ልደታችሁ ዛሬ በሀዘን ፣ ቁጭት በመለያየት የታጀበ  ቢሆንም ነገም ሌላ ቀን ነውና ጨለማው ይነጋል ፣ ከፍ ያለው ዝቅ ይላል ፣ ሁሉም አላፊ ነው ፣ ያልፋል  ! ይህ እስኪሆን ከጀግኖችና ከቤተሰባቸው ጎን ሰፊው ህዝብ ክብር ይቆማል ፣ ኤልማዳ እኛ ኢትዮጵያን የምንወድ አባትሽ ስለከፈለልን የመስዋዕትነት እዳ ከአንችና ከመሰሎችሽ ጎን ነን ! ዛሬ እንኳን ተወለድሽ የምንልሽ በዚያ ህዝባዊ መንፈስ ነው ፣ እመኝኝ ! ዛሬ አባትሽና መሰል አርበኞች በከፈሉና በሚከፍሉት የከበደ መራራ መስዋዕትነት የነገን ብሩህ ቀን ተስፋ ይመጣል !

ብቻ እንኳንም ተወለድሽ  ህጻን ኤማንዳ ሐብታሙ  !

ነቢዩ ሲራክ
ሐምሌ 21 ቀን 2008 ዓም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar