ፒያሳ ላይ የትግሬው መከላከያ ሁለት ሰዎችን መግደሉ ተሰማ:: የወልቃይት ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ፍርድ ቤት ያለመቅረብ ጉዳይ የፍርድ ቤት ጉዳይ ለመከታተል የወጣው ሕዝብን አስቆጥቶ ለመበተን ይህን ሕዝብ የሕወሓት ሰራዊት በወሰደው እርምጃ እነዚህ ሁለት ንጹሃን መገደላቸው ብዙዎችን እያስቆጣ ይገኛል:: የሟቾች ቁጥር ከ3 በላይም ሊሆን እንደሚችል የዘ-ሐበሻ ምንጮች ይናገራሉ:: አንዱ ሰላማዊ ዜጋ በአናቱ ላይ በተተኮሰበት ጥይት አደባባይ ላይ ሞቶ የተገኘበት ፎቶ በሶሻል ሚድያዎች ተለቋል::
ሙሉቀን ተስፋው ዝርዝር ዘገባ አለው:-
• የትግራይ ልዩ ኃይል አርማጭሆ ወደ አርማጭሆ ሒዶ ዐማሮችን ሊበቀል እንደሚችል ተጠቁሟል
• ሁለት የትግራይ ሠላዮች አርማጭሆ አካባቢ ባልታወቀ ምክንያት ተገድለው ተገኝተዋል
ከሙሉቀን ተስፋው
ዛሬ ማለዳውን የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን የፍርድ ሒደት ለመከታተል በመጡ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የወያኔ ሠራዊት ተኩስ መክፈቱን ተከትሎ የዐማራ ገበሬዎች የአጸፋ መልስ ሰጥተዋል፡፡ በአጋዚ ጦር እስካሁን የሁለት ዐማሮች ሕይወት ማለፉን ለማወቅ የታቻለ ሲሆን አንድ የትግሬ መከላከያ ተገድሏል፤ በርካታ የፌደራል ፖሊሶችም ቆስለዋል፡፡
የትግሬው መንግሥት የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነትን ለማፈን በመፈለጉ መላውን የዐማራ ሕዝብ በቁጣ አነሳስቷል፡፡ ዛሬ ሐምሌ 29 ቀን 2008 ዓ.ም. መለው የጎንደር ከተማ ከወያኔ ቁጥጥር ውጭ ሆኗል፡፡ ከአዘዞ እስከ ሸንበቂት ድረስ ያሉ ሁሉም የጎንደር ከተማ መንገዶች ሞት በማይፈሩ ወጣቶችና የታጠቁ ገበሬዎች ተሞልቷል፡፡ የትግሬ መከላከያ ከጭልጋና እና ከባሕር ዳር እንዳይመጣ መንገዶች ሁሉ ተዘግተዋል፡፡
ከኹመራ፣ ዳንሻሻ ሶሮቃ፣ አብደራፊ፣ ሳንጃ፣ ትክል ድንጋይ፣ አሽሬ፣ ዳባትና ደባርቅ፣ ከበለሳ፣ አዲስ ዘመን፣ ጋይንት፣ ፋርጣና ፎገራ፣ ከደንቢያ፣ ከጯሒት፣ አቸፈር፣ ዳንጋላና ዱር ቤቴ፣ … በቅርብ የሚገኘው የዐማራ ታጣቂ ገበሬ ሁሉ ወደ ጎንደር በመሔድ ከወንድሞቹ ጋር እንዲዋደቅ ተደጋጋሚ ጥሪ እየቀረበ ነው፡፡ የትግሬ መንግሥት ይህን ተከትሎ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ሊያቋርጥ ይችላል እየተባለ ነው፡፡
አሁን ዘግይቶ በደረሰን ዜና የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ በዳንሻ ከተማ ዐማሮችን ማስፈራራት የቀጠለ ሲሆን አርማጭሆ በመሔድ ዐማሮች ላይ የበቀል እርምጃ እወስዳለሁ ማለቱ ከዳንሻ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ሁለት የትግራይ ሠላዮች ጎንደር ከተማ ሰንብተው ሲመለሱ አርማጭሆ ሲደርሱ ባልታወቀ ምክንያት ተገድለው መገኘታቸው ወያኔን አናዷል፡፡
Average Rating