www.maledatimes.com በጎንደር እና አውዳይ የሞቱት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ፣ህዝቡም ለለውጥ ተዘጋጅተናል ብሏል። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጎንደር እና አውዳይ የሞቱት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ፣ህዝቡም ለለውጥ ተዘጋጅተናል ብሏል።

By   /   August 6, 2016  /   Comments Off on በጎንደር እና አውዳይ የሞቱት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ፣ህዝቡም ለለውጥ ተዘጋጅተናል ብሏል።

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 37 Second

በጎንደር ቆላድባ ሕዝብ ከሕወሃት ወታደሮች ጋር እየተዋደቀ እንደሚገኝ የሚደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል:: በአወዳይ የሕወሃት ሰራዊት በንጹሃን ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ባወረደው ጥይት 70 ሰዎችን ሲያቆስል 3 ሰዎች መገደሉ ተዘግቧል::

ማለዳ ታይምስ

ማለዳ ታይምስ

የጎንደር ቆላድባ ከተማ በአሁኑ ወቅት የጦር አውድማ ትመስላለች የሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ሕዝቡ ቁጣውን ለመግለጽ ፍርድ ቤት; የክልሉን የመንግስት መስሪያቤቶች እና ከ14 በላይ የመንግስት መኪኖችን በማቃጠል ተቃውሞውን ገልጿል::

በተለይም በቆላድባ ከተማ የሚገኘውን የመንግስት መሳሪያ ግምዣ ቤትን በመስበር ሕዝቡ ራሱን አስታጥቆ መከላከያ ሰራዊቱ ን በጦርነት ገጥሞታል::

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ደብረታቦር እና ጋይንትም አለመረጋጋቱ እንዳለ ነው::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ በአወዳይ ዛሬም ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ:: 70 የሚሆኑ ንጹሃንም ቆስለዋል:: በአወዳይ ላይ ጥቃት ሲፈጽም የነበረው ህወሃት መራሹ መንግስት ዛሬም ጥቃቱን ቀጥሏል ያሉት ነዋሪዎች ለቢቢኤን እንደገለጹት ገና በማለዳዉ ከመስጊድ ሶላት ሰግደዉ የሚወጡን የእድሜ ባለጸጋ የሐይማኖት አባት አጋዚ በጥይት መመታታቸዉ አወዳይን እልህ ዉስጥ የከተተ መሆኑን ገልጸዋል።
ሁሌም አጋዚዎችን በቁርጠኝነት የሚጋፈጠዉ ነዋሪ ዛሬም አጋዚን ሲጋፈጥ መዋሉን ገልጸዋል። ህዝቡ ተቃዉሞን በሰላማዊ መንገድ ቢያሰማም አጋዚዎች ቀጥታ ወደ ህዝብ በመተኮሳቸዉ እስከ ሰባ የሚደርሱ የአወዳይ ነዋሪዎች መቁሰላቸዉ ለማወቅ ተችሏል። የህዝቡ ቁጣ በአወዳይ ዉስጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በማለዳ ሶላት ሰግደዉ ከመስጊድ ሲወጡ የነበሩት የሐማኖት አባት በጥይት መገደላቸዉ ዉጥረቱን ወደ ጦርነት ሳይቀይረዉ አይቀርም በማለት የአወዳይ ነዋሪዎች ስጋታቸዉን ገልጸዋል።
ስርዓቱ በጣረሞት ዉስጥ ነዉ በማለት ለቢቢኤን የገለጹት ነዋሪዎች እርምጃዎቹ የደመነፍስ እንደሆኑ አስረድተዋል። በስተመጨረሻ ድል የተጨቆነ ህዝብ በመሆኑ ለድል በጋራ እንነሳ የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል።

በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ከአቶ ሙሉነህ ኢዩኤል የደረሰን አጭር መጣጥፍ ይህንን ይመስላል

ዛሬ እጅግ በጣም ብዙ በሆኑ የተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች ሳይቀር ህዝቡ የወያኔን አገዛዝ እስከወዲያኛው ሊሰናበተው እንደሚፈልግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ አሳይቷል። በደቡብ ጎንደር በደብረታቦር ክፈተኛ ተቃውሞ እንደነበረ መረጃዎች ያሳያሉ። ምንም እንኳን በእነዚህ ቦታዎች የነበረው ህዝብ ጥያቄዎቹን በሰላማዊ መንገድ ለመግለፅ ቢወጣም የወያኔ ምላሽ የነበረው ጠመንጃ ነበር። እስካሁን ያለው መረጃ እንደሚያሳየው ከሃምሳ በላይ ሰዎች ተገለዋል።

በሰሜን ጎንደርም በአዘዞ በሚገኘው ወታደር ካምፕ ላይ ጥቃት ተሰንዝሮ በውስጡ ከሚገኘው የመሳሪያ ግምጃ ቤት እጅግ ብዙ የነፍስ ወከፍ መሳሪያና ጥይቶች ጥቃቱን በፈፀመው ጀግና ህዝብና ልጆቹ እንደተወሰደ ታውቋል። በተጨማሪም ህዝቡ ሊጠቀምባቸው የማይችላቸውን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች በእሳት መጋየቱን እየሰማን ነው።

ነገ የአማራ ክልላዊ መንግስት ዋና ከተማ በሆነችው ባህርዳር ላይ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል። ዛሬ ለዋዜማ ድምቀት በከተማዋ ካለው መነሃሪያ በመውጣት አውቶቡሶችና ሚኒ ባሶች ጥሩምባ እየነፉ ከተማዋን ሞቅ ደመቅ እንዳደረጉ ተሰምቷል። መልእክቱ ግልፅ ነው፥ነገ ይቀወጣል።

የጎንደር ህዝብ ምስጋና ይግባውና የፖለቲካ ድባባችንን ፈወሰው። የጎንደር ህዝብ “በኦሮሚያ የሚፈሰው ደም የኛ ደም ነው” ሲል በደስታ ሲቃ እንዳወራረድነው ቢያንስ አንድዬ ምስክር ነው። በእርግጥ በዚህ የተከፉ እንደሚኖሩ ለመጠርጠ ጠንቋይ መቀለብ አይኖርብንም። የጎንደር ህዝብ ድርጊት እኛን የደስታ እምባ ከማስነባት ያለፈ ፋይዳ ያለው ነው። ዛሬ በአፀፋው የአዳማ ህዝብ “አማራ የኛ ነው” ነው ሲል እንድንሰማ አድርጓል።

ሰሞኑን በተለያዩ ቦታዎች ያሉ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ዛሬ በተደረጉ ሰልፎች ላይ እንዴት የአማራውን ህዝብ ብሶት እንደራሳቸው ብሶት ለማስተናገድ በሚገርም መጠን ደፋ ቀና ሲሉ አይተናል። ሰሞኑን ኢሳት የኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ የአማርኛ ፕሮግራም ኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ ደግሞ የኢሳት የኦሮሚኛ ክፍል መስሎ እንዲሰነብት እንዳደረገ ኖረን አይተናል። ይህን ተአምር ሳያይ ለሞተው ለመለስ ዜናዊ ዛሬ አዘንኩለት።

አቦይ እንኳን የሸራተን አዲስ ሉዊ 16ኛ ያልገደለዎ። በረከት እንኳን ይህን ጉድ ኖረህ አየህ። አባይ እንኳንም ያልሞትክ። አዜብ ሃዘኑ አንቺ ላይ ሊበረታ እንደሚችል ባስብም አላዘንኩልሽም። እንዲህ አይነቱን ነገር ኖሮ ማየት ብቻውን ትልቅ ህመም ሆኖ ሳለ በጣም የምትወጂው ባልሽ የእድሜ ልኩ ድካም እንዲሁ መና ሲቀር ከማየት በላይ የሚያቃጥል ነገር ከወዴት ይገኛል? አይዞሽ አቃጥሎ አቃጥሎ ይገልሻል፤ያኔ እስከወዲያኛው ትገላገይዋለሽ።

አሁን የተፈጠረውን የህዝብ መነሳሳት ከፍ ወዳለ ደረጃ እናሳድገው በሚለው ጉዳይ ላይ መነጋገር ይኖርብናል። እስካሁን የተደረጉት ሰልፎች ከሁለቱ ክልሎች በላይ አድማሳቸው ሊሰፋ ይገባል። እስካሁን የተደረጉት ሰልፎች ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸውን አቅርበው ወደቤት የሚመለሱ ናቸው። ከዚህ በሗላ የሚደረጉ ሰልፎች ግን ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸው ሳይመለስ ወደየቤታቸው የማይመለሱበት እንዲሆን ምን ማድረግ ይኖርብናል? በጎንደር አካባቢ ያየነውን አይነት “ከተኮስክብኝ እተኩስብሃለሁ” የሚለውን ህዝብን አንገቱን ቀና የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች እንዴት በሁሉም ቦታዎች እንዲቀጣጠሉ ማድረግ ይኖርብናል? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች ላይ የፖለቲካ ሃይሎች መነጋገርና አቅጣጫ መስጠት ይኖርባቸዋል። ከወያኔ በሗላ ሀገራችን የሚኖራት መንግስት ምን መምሰል ይኖርበታል በሚል ሃሳብ ላይ የሰከነ ውይይት ሊደረግ ይገባል። በተለይ ኢሳትና ኦኤምኤን በዚህ ዙሪያ ሰፊ ውይይት መክፈት ያለባቸው ይመስለኛል።

ከላይ ከተነሳው ሃሳብ ጎን ለጎን በአፋጣኝ በውጭ ባሉ የኢትዮጵያ ልጆች መሰራት ያለበት ጉዳይ ያለ ይመስለኛል። በሃገር ውስጥ ላለው እንቅስቃሴ በውጭ የምንገኝ የዚያች መከረኛ ሃገር ልጆች እኛም አጋርነታችንን ማሳየት ይኖርብናል። በተለያዩ ቦታዎች በህዝባችን ላይ የሚደረገውን ግፍና መከራ በምንኖርባቸው ሀገሮች ልናስረዳ ይገባል። በተለያዩ ሀገራት የሚደረጉ የአጋርነት ሰልፎች የጎንደርንና የአዳማን መንፈስ የያዙ መሆን ይኖርባቸዋል። መከራ አንድ እንዳደረገን፥እነርሱ አንዳቸው ለሌላቸው እንደሚያስቡ ሁሉ እኛም እንደምንተሳሰብ እናሳያቸው።ሰልፎቹ በሁሉም የማህበረሰብ አባላት እንዲጠሩ እናድርግ።በአንድ ከተማ የሚኖሩ የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ አባላት ከሌሎች የኢትዮጵያ ኮሚኒቲዎች ጋር አብረው ሰልፍ ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል። በተለይ የትግራይ ኮሚዩኒቲ አባላትን ለማሳተፍ መጣር ይኖርብናል። እኛም ትግሬዎች እንደሆን ልናሳይ እነርሱም በእርግጥ ሞታችን ሞታቸው እንደሆነ ሊያሳዩ ይገባል። ኢትዮጵያ የሁላችን፥ሁላችንም የኢትዮጵያ ነን።

ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርክ! ብል የሚቀየመኝ ማን ነው?

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on August 6, 2016
  • By:
  • Last Modified: August 6, 2016 @ 3:41 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar