0
0
Read Time:35 Second
በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት በተቀሰቀሰው ነውጥ ፣በመንግስት ታጣቂዎች ክፉኛ የሆነ ድብደባ በንጹሃን ዜጎች ላይ ተፈጽሞአል።
በተለይም በብሄራዊ ቴአትር አካባቢ በአንድነት ወደየቤታቸው ሲጓዙ የነበሩ ጓደኛሞችን በመደብደብ እራሳቸውን እንዲስቱ አድርገዋቸዋል ። ቀሪዎቹም በከፍተኛ ጉዳት ወደ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን ፣ከማእከላዊ የመረጃ ማእከል ለወታደራዊ ሰራዊቱ የተላለፈው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ በአዲስ አበባ ከተማ በጊዜ የማይገቡትን ወጣቶችንም ሆነ በጋራ ተሰብስበው የሚገኙትን ማንኛውንም ዜጎች ለማፈስ ጥሪ እንደተላለፈላቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ ሰሞኑን ለለውጥ እዘጋጃለሁ ብለው መነሳታቸውን እና የሌሎች ክፍለ ከተሞችንም ሆነ የክፍለ ሃገሪቱን ህዝቦች በአንድነት ጥሪ ማድረጋቸው ተስተውሎአል ።
የጦር መሳሪያ ሳይሆን ሊመልሰን የሚችለው ፍቅር ነው ለፍቅር ብለን በግፍ 25 አመታትን ተገፍተናል ዛሬ ግን በቃን ሲሉ ተደምጠዋል ።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating