በአዲስ አበባ ናዝሬት ጎንደር እና ዝዋይ የተካሄደው አገር አቀፍ ተቃውሞ በየክልሎቹ መዛመቱ እንደማይቀር እና ጥሪው ከሰሜን አሜሪካ የሄደ ሳይሆን እዚያው ያለው መንግስት በፈጠረው አፈና እና የጭቁኑ ህዝብ ብሶት ነው ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ሲናገሩ ፣መንግስት በበኩሉ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ አሸባሪዎች ናቸው ይህንን ችግር የፈጠሩት ሆኑም ግን ችግሩን በቁጥጥጥር ስር አውለነዋል ሲል በመረጃ ማእከሉ ለመናገር ችሎአል።
http://www.ethiotube.net/video/36299 ይህንን ሊንክ ተጭነው ይመልከቱ እና ግንዛቤዎን ይስጡ
የወያኔ መንግስት ጥቂት ሽብርተኞች ብሎ የጠራቸው የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን ይመስል ነበር ፣ሰሞኑን ደግሞ አይሎ ሊወጣ የሚችለውን ህዝብ ሲታሰብ ምንኛ በእራሱ ስራ ሊያፍር እንደሚችል የሚያሳይ መሆኑን ይጠቁማል .
በኢትዮጱያ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ያለው እና ክልመና ወደ መንግስትነት ነው የመጣው እየተባለ የሚጠራው የወያኔ መንግስት አስተዳድር ዛሬ ካሉበት ደረጃ እንዲደር ያደረገውን የጎንደርን ህዝብ ውለታ እረስቶ ጥይት አዝንቦበታል ሲሉ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የደባርቅ ተወላጆች ለማለዳ ታይምስ ገልጸዋል ። በአሁን ሰአት መንግስት እያደረገው ያለው ትልቁ ሴላ ሊኮላሽ እና ሊደመሰስ የሚችለው በእኛ በአንድነት የመጠናከር ሲሆን ፣ህይወታችንን እስከመጨረሻው ለመሰዋት ዝግጁዎች ነን ሲሉም አክለው ገልጸዋል።
ሃገራችን በሰሜኑ ክልል ለሱዳን እና ለትግራይ እየተባለ መሬቱዋን እንደ ቅርጫ ስጋ እየተከፋፈለ ሲሰጥ ማየት ከዚህ በላይ ሞት የለም ስለዚህ አሁንም በዚሁ ሂደት ላይ ሳለን ሌላ ተጨማሪ ሳይመጣብን ይህንን ስርአት ማስወገድ ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል።
Average Rating