በሙሉቀን ተስፋው
የቆሰሉና የሞቱ ሰዎች ቁጥር አይታወቅም፤ ዓባይ ማዶ ኮበል በቃጠሎ ወድሟል
• ከጎንደር የሚሔዱ ዐማሮች ዘንዘሊማ ላይ መታገዳቸው ለግጭቱ መንስኤ ሆኗል
በጎጃም እምብርት ባሕር ዳር ዐማሮች በጠዋት ነበር ወደ ተጋድሎ ሰልፍ የወጡት፡፡ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ በዐማራ ወገኖቻቸው ላይ የሚደርሰውን በደል እና የጅምላ ግድያ በማውገዝ ወደ መስቀል አደባባይ ሕዝቡ በአንድነት ሔደ፡፡ በዚህ መካከል ከጎንደር ለተጋድሎ የሚመጡ ዐማሮች ዘንዘሊማ ላይ በወያኔ ጦር ወደ ባሕር ዳር መግባት እንዳይችሉ መታገዳቸው ተሰማ፡፡ ሕዝቡ ተመልሶ ከጎንደር አካባቢ የመጡትን ወገኖችን ለማስለቅ ወደ ዓባይ ማዶ መንገድ አመራ፡፡ በቀበሌ 18 የሚገኘውን የመንግስት መስሪያ ቤቶችን በአማራው ህዝብ ቁጥጥር ስር መዋሉ እና ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ነጻነቱን ለማስከበር መታሩ ምን ያህል በመንግስት ላይ ያለውን ጥላቻ የሚያሳይ ሲሆን በሌሎች በአማራ ክልል የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ስልት ተጠቅመው የክልሉን ወታደራዊ ስርአት በቁጥጥሩ ስል ለማድረግ የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ የተለያዩ ቅየሳዎችን እያደረገ እንደሆነ ከአማራ ክልል ለማለዳ ታይምስ የደረሰው ዘገባ ያመለክታል ።
የዐማራ ተጋድሎ ተሳታፊዎች እግረ መንገዳቸውን ባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ (ፖሊ ካምፓስ)፣ ክልል ምክር ቤት፣ አማራ ብድርና ተቋምና ሌሎች መሥሪያ ቤቶች አካባቢ ያሉ የወያኔን ድሪቶ ባንዲራ የአባቶቻችን ደም በፈሰሰባት ትክክለኛ ሰንደቅዓላማ በመቀየር እንዲሁም የክልሉ ምክር ቤት ፊት ለፊት የነበረውን የመለስ ቢል ቦርድ በማቃጠል ወደ ዓባይ ማዶ ነገዶ፡፡ ባሕር ዳር ከተማ የቀረ አንድም ዐማራ አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡
የዓባይን ድልድልይ ተሻግረው ወደ ዘንዘሊማ ለመሔድ መንገድ ሲጀምሩ አዲስ ዓለም ገበያ አካባቢ ‹‹ኮበል›› የሚባል የወያኔ ምልስ ወታደሮች ንብረት የሆነ ስጋ ቤትና ግዙፍ የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት አለ፡፡ ይህ ድርጅት በተለምዶም ‹‹ዳሸን ቢር ጋርደን›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከዚህ ግቢ ውስጥ በሰለማዊ መልኩ ተጋድሎውን ሲቀጥል በነበረው ሕዝብ ላይ የተኩስ እሩምታ ተከፈተ፡፡ ኮበል ማዶ ካሉ ኮንዶሚኒየም ሕንጻዎች ፎቅ ላይ የወጡ የወያኔ አልሞ ተኳሾች በተቃራኒ አቅጣጫ ከሕዝቡ ላይ ጥይት አርከፈከፉ፡፡ ባዶ እጃቸውን የነበሩ ዐማሮችን ደም ወያኔዎች አፈሰሱ፡፡
በዚህ የተበሳጨው የዐማራ ነበልባል ወጣት ከማደያ ነዳጅ እየቀዳ የኮበል ኢንዳስትሪን ሙሉ በሙሉ በእሳት አጋዬ፡፡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዐማሮች ሌሎችን ለማኖር ሲሉ ተሰውተዋል፡፡ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል፡፡ አሁን በዓባይ ማዶ መካከለኛ ክሊኒክና በአዲስ ዓለም ጠቅላላ ሆስፒታል በርካታ እስረኛና ቁስለኛ እንዳለ ነው ከቦታው ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው፡፡
ባሕር ዳር በአሁኑ ሰአት ዝናብ ቢሆንም ወጣቶች ተጋድሏቸውን አላቆሙም፡፡ ‹‹ደም ሰፈስ ደም ይፈላል›› እንዲሉ አበው፤ የዐማራ ወጣቶች ተጋድሎ ያለምንም ጥርጥር በሰማእት ወንድሞቻችን አጥንት ካስማ መሠረት ላይ ይገነባል፡፡
ይህ ሁሉ ግን የመጀመሪያው መጨረሻ ነው!!
ወያኔ በባሕርዳር፣ ጎጃም ዐማራ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ በቃን
Read Time:1 Minute, 42 Second
- Published: 8 years ago on August 7, 2016
- By: maleda times
- Last Modified: August 7, 2016 @ 5:47 pm
- Filed Under: Ethiopia
Average Rating