www.maledatimes.com በአዲስ አበባና በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የመንግስት ታጣቂዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ እየፈጸሙ ያሉትን ግድያ የአለም አቀፍ ሚዲያዎች በሰፊው እየዘገቡት ይገኛሉ። በአቤኔዘር አህመድ ከጀርመን - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በአዲስ አበባና በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የመንግስት ታጣቂዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ እየፈጸሙ ያሉትን ግድያ የአለም አቀፍ ሚዲያዎች በሰፊው እየዘገቡት ይገኛሉ። በአቤኔዘር አህመድ ከጀርመን

By   /   August 8, 2016  /   Comments Off on በአዲስ አበባና በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የመንግስት ታጣቂዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ እየፈጸሙ ያሉትን ግድያ የአለም አቀፍ ሚዲያዎች በሰፊው እየዘገቡት ይገኛሉ። በአቤኔዘር አህመድ ከጀርመን

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 14 Second

 በአፍሪቃ መዲና በአዲስ አበባ የጎንደርንና የኦሮምያን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ በ30/11/2008 ዓም(06 Aug 2016) እና በ ቀን 1ነሃሴ 2008 ዓም (07Aug 2016) በተደረገው መንግስትን የመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በመንግስት ታጣቂዎች የንጹዋን ህይወት ማለፉንና በብዙ የሚቆጠሩ እንደታሰሩ የተለያዩ አለም አቀፍ የዜና አውታሮች ዘግበውታል። አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) መንግስትን ለመቋወም የወጡ ሰዎች ታሰሩ “Dozens arrested in Ethiopia anti-government protest” በሚል እርእስ የአዲስ አበባውን የተቋውሞ ሰልፉንና የመንግስትን የሀይል ምላሽ ዘግቦታል። አልጄዜራ (Aljazeera English) ግድያና እስራት እየፋፋመ ባለው ተቋውሞ በኢትዮጵያ በሚል ርእስ “Deaths and detentions in Ethiopia as protests flare” የአዲስ አበባውን የጎንደርን እንዲሁም የኦሮምያን ተቋውሞ በዘገባው አስፍሮታል። በማስቀጠልም በነሃሴ 2 2008 ዓም (08 Aug 2016) ባወጣው የዜና ዘገባው የመንግስት ታጣቂዎች ሰላማዊ ለልፈኞችን በጥይት ተኩስ እንደገደለ አትቷል “Scores killed in Ethiopia protest crackdown. Security forces accused of shooting dead people in Oromia and Amhara regions in attempt to suppress wave of protests.” (Aljazeera English) ቢቢሲም (BBC)“What is behind Ethiopia’s wave of protests?” (BBC NEWS 08 Aug 2016) በተጨማሪም በ29 /11 /2008 (BBC NEWS on 05 Aug 2016)ቢቢሲ በዘገባው እያገረሸው ያለውን የጎንደርን ተቋውሞ “Renewed protests in Ethiopia’s northern city of Gondar” በሚል ርእስ ዘገባ አቅርቦበታል።

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) በአዲስ አበባው የተቋውሞ ሰልፍ ላይ ነጻነታችንን እንፈልጋለን የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱልን በማለት ከፍ ባለ ድምጽ ሲጠይቁ እንደነበር እንዲሁም ፖሊስም በአፋጣኝ ሰልፉን ለመበተን እንደተንቀሳቀሰ እማኝነቱን ሰጥቱዋል “Some 500 people gathered amid a heavy police presence on the capital’s main Meskels Square shouting slogans such as “ we want freedom” and “free our political prisoners.” ይህንን የህዝብ አመጽ ለመቆጣጠር መንግስት የማህበራዊ ሚዲያዎችን እንደዘጋም የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ጋዜጤኛ ምስክርነቱን አስፍሯል “Authorities have blocked access to social media,the activists’ key channel for such rallying calls, since Friday. Internet access was nearly impossible Saturday in Addis Ababa itself, an AFP journalists said.”

አልጄዜራ በእንግሊዘኛው የዜና ሽፋኑም ጎንደር ውስጥ በትንሹ የስድስት ሰዎች በመንግስት ታጣቂዎች መገደላቸውንና በአዲስ አበባ ብዙ ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ዘግቧል “At least six people have been reported killed over two days of protest in Ethiopia while dozens were arrested in the capital, Addis Ababa.” በዚሁ ዘገባውም ንጹሀን ሰልፈኞች በፖሊስ ሃይሎች ሲደበደቡ እንደነበረ ከሮይተርስ የዜና ኤጀንሲ ባገኘው የምስል መረጃ ማረጋገጥ እንደቻለ አስፍሯል “ A Reuters news agency video of the confrontation showed unarmed protesters being beaten and kicked by police officers, as protesters ran to evade arrest.”

የዘገባዎቹን ሙሉ ይዘት በእንግሊዘኛ ለማንበብ የሚከተሉትን ምንጮችን ይከታተሉ

-http://www.aljazeera.com/news/2016/08/ethiopia-protests-160806132205709.html

-http://www.bbc.com/news/world/africa/live

-http://www.dailymail.co.uk/wires/afp/article-3726998/Dozens-arrested-Ethiopia-anti-government-protest.html
-http://www.bbc.com/news/world-africa-36940906

-http://www.aljazeera.com/news/2016/08/30-killed-ethiopia-protests-opposition-160808105428331.html

Aljazeera English
AFP
BBC news
Abenezer Ahmed/ From German

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on August 8, 2016
  • By:
  • Last Modified: August 8, 2016 @ 5:46 pm
  • Filed Under: Ethiopia

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar