www.maledatimes.com የማለዳ ወግ … ዝም የማይባል የወገን ድረሱልን ጥሪ ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማለዳ ወግ … ዝም የማይባል የወገን ድረሱልን ጥሪ   !

By   /   August 26, 2016  /   Comments Off on የማለዳ ወግ … ዝም የማይባል የወገን ድረሱልን ጥሪ   !

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 10 Second
=============================
* ” የዛፍ ላይ እንቅልፍ !” ስደት
* የኮንትራት ሰራተኞች “ድረሱልን” ድምጽ
https://youtu.be/VZP-9yOvdg0
የመረጃ መረቡ ከሃገር ቤት በሚሰማው የህዝብ እንቢተኝነት አመጽ ተጨናንቆ እኛንም አጨናንቆን ከርሟል ። በዚህ የመረጃ ቅብብሎሽ መካከል ወደ ምሥራቅ ሳውዲ ለስራ ጉዳይ አቅንቸ  ነበር ። ርያድ ፤ ደማም ፡ ጁቤል፤ ሃፍር አልበጠንን ለአንድ ሳምንት ሳካልል ከሃገር ቤት ከሚሰማው መረጃ  እኩል በሳውዲ ዙሪያ ያሉ በርካታ ወገኖቸ የተለያዩ መረጃዎች በስልክ  አድርሰውኛል ። በተዘዋዎርኩባቸው ከተሞች ያገኘኋቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቸም የሚያመውን የስደት ህመም ሳይደምቁ አጫውተውኛል ።  ሁሉም አሳሳቢ ናቸው ፣ ሁሉም ቢያንስ መፍትሔ ይሻሉና ዝም የማይባለውን የወገንን ድረሱልኝ ጥሪ አሳውቃችኋላሁ   !

ዛሬም በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች የተበተኑ ችግር የገጠማቸው ዜጎች መብት አስከባሪ አጥተው ሲንከራተቱ ፣ ሲንገላቱና የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ነው ! በአንጻሩ አዲስ ኮንትራት ውል ከሳውዲ አረቢያ ጋር ለመስማማት ደጋግሞ ሞክሮ ያልተሳካለት የኢህአዴግ መንግስት ኮንትራት ውሉን ለማሳካት እየተሯሯጠ መሆኑን ከሪያድ ኢምባሲ ሁነኛ መረጃ ደርሶኛል ። ይህ እየተሰራ ባለበት በሳውዲ በባህር መጥተው ለከፍተኛ አደጋ የተጋለጡትን መከራ መስማት ይከብዳል ፣ ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ኃይማኖት ከየመን በየመን በኩል በሚደረገው በሳውዲ መዳረሻ በመንገዱ ያለውን አሰቃቂ ሁኔታ እፍታ እፍታውን ደጋግሞ  ገልጾታልና ደግሜ አላሰለቻችሁም  ! ብቻ መከረኞቸን መታደግ ሳይቻለን በመቀረቱ አልመች ብሏቸው እንጀራ ፈልገው  በየመን የሚጎርፉት ዜጎች ”  መከራውን እያወቁት መርጠው የመጡት ነው! ይበላቸው ! ” የሚል ሰብዕና የጎደለው የጨካኝ ምክንያት እየሰጠን ለመርዳት ከመደገፍ መሸሽን መርጫችን አድርገናል  ! … ያሳዝናል   !

የባህርተኞቹ ጉዳይ ይሁን ቢባል ፣ ህጋዊ በተባለው በኮንትራት ስራ ሳይደራጁ “በተደራጁት  ” ኤጀንሲዎች መጥተው በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች የተበተኑት እህቶች ጉዳይ አሳሳቢ ከሆነ ከራርሟል ።  በኮንትራት በሚሰሩባቸው የአረብ ቤቶች በስራ ጫና ፣ በሚደርስባቸው በደል ፣ በሕመምና በጭንቀት ፣ ብሎም ”  የተሻለ እናገኛለን ” ብለው ከአሰሪዎች የጠፉና ”   የተሻለ ስራ እናስገባለን  !”  በሚሉ ሆድ አደር ደላሎች የተፈናቀሉ አብዛኛው እህቶች ቁጥር እጅግ በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል  ! አንድ በኩባንያው ስራዬ በኩል በቅርብ የማውቀው ለፖስፖርት ጽ/ቤት መረጃ ቅርብ የሆነ ሳውዲ ከፍተኛ ኃላፊ በኮንትራት መጥተው ከአሰሪዎቻቸው የጠፉ ” ሁሩብ ” ተብለው የተመዘገቡ ኢትዮጵያን ቁጥር ወደ 60 እና 70 ሽህ እንደሚገመት አጫውቶኛል ።  ለእኒህ ከአሰሪዎቻቸው የጠፉ  ወገኖች መካከል በጠፉበት ሆነው ኑሮን በስደት ሲገፉ ጥቂት የማይባሉ ” ህገወጥ”መሆናቸው ሳያስፈራቸው ቤት ይዘው ፣  ትዳር መስርተው   ፣ ልጅ ወልደው የሚገኙት ቁጥር ቀላል አይደለም ።

” የዛፍ ላይ እንቅልፍ !” ስደት
==================
አደጋው የደላ ቤት ይዘው ፡ ትዳር መስርተው ፤ ቀን መዳር መኳሉ  ልጅ መውለዱ አይደለም ። የሞቀው ሲበርድ ፤ አፍላው አልፎ ፤ የእውነቱ ኑሮ ሲጀመር ኑሮን በሃላፊነነት የመግፋቱ ክብደት የመጣ ጊዜ ነው ፍተናው  ! ሞልቶ የማይሞላው ” የዛፍ ላይ እንቅልፍ ”  የስደቱን ኑሮ እንዳሰቡት አልሰምር ሲል ደግሞ ከላጤዎች ይልቅ ቤተሰብ መስርተውና በስደቱ  የልጅ ፍሬ በረከት ለታደሉት መከራው የከፋ ይሆናል ።  በስቃይ ፣ መከራው  ፣ በእምነት ክህደት ፣ ውስብሰቡ  ህይወት ያመጧልቸው የስደት ፍሬ ልጆቻቸው ደግሞ የመከራው ገፈት ቀማሽ ይሆናሉ  !  ነገሮች ይወሳቡባቸዋል  ! …ታዲያ  ”  የመጣ ይምጣ ወደ ሃገር እንግባ  ፣   የስደቱን ኑሮ ይብቃን  ! ” ብለው ወደ ሐገር መግባት የፈለጉ ቀን ለከፋ ስቅየት ይዳረጋሉ … !

በተለይም ከአስሪዎቻቸው ጠፍተው ከርመዋልና ጠፉ ወይም ” ሁሩብ“ ተብለው በፓስፖርት መ/ቤት የሚፈለጉት ወደ ሐገር ለመግባት ሲፈልጉ ጣጣው የከፋ ሆኗል ። በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች ወደ ሃገር ለመግባት ፈልገው የሚይዛቸው እና የሚሸኛቸው አካል አጥተው ” ወደ እስር ቤት  አስገብተን ወደ ሃገር እንልካለን በሚሉ የራሳችን ዜጎች ደላሎች ከፍተኛ ገንዘብ ከስክሰው እስር ቤት ከገቡ በኋላ ለወራት በእስር ቤት እየማቀቁ ያሉት ቁጥር ቀላል አይደለም ። ከዚ በታጓዳኝ ለደላላ የሚሰጥ ገንዘብ የሌላቸው ይዞ በእስር ቤት በኩል ወደ ሃገር ቤት የሚልካቸው ፖሊስ አጥተው የሚንክተቱ ቁጥር እጅግ ከፍ ያለ መሆኑን ተመለክቻለሁ ። በሌላ በኩል ከአሰሪዎቻቸው ሳይጠፉ “ ኑሮው በቃኝ !” ያሉ ጊዘ ወደ ሃገር ለመግባት ፈልገው ፈቃድ ከአሰሪዎቻቸው የማይሰጣቸው ፤ የመውጫ ቪዛ ለማስመታት ከፍተኛ ገንዘብ በመጠየቃቸው እጃቸው ለፖሊ ሰጥተው መያዙ የቀናቸው እስር ቤት ከገቡ በኋላ በወህኒ መጉላላት እ ደሚደርስባቸው መረጃዎች ደርሰውኛል ። ወደ ሃገር ቤት ለመግባት ፈልገው የተያዙት እና ሳይፈልጉ በቤት ለቤት ሰበራ ፍተሻ ተይዘው እስር ቤት የተወረዎሩት ከወራት በኋላ እንኳ ወደ ሀገረቸው ለመግባት የከፋ  እንግልት እንደሚደርስባቸው በዝርዝር አጫውተውኛል  !

በከፋ አደጋ ላይ ስለመሆናቸው የገለጹልኝ ህጻናትን የያዙ እናቶች ወደ ሀገር ለመግባት ቢፈልጉም ከነገ ዛሬ እየተባሉ ለወራት በወህኒ ሲቆዩ በስቃይ ላይ መሆኑን አጫውተውኛል ። ወ ደ ሃገር ቤት እንግባ ብለው እጃቸው የሰጡ በማናቸውም መንገድ ወደ እስር ቤት የገቡ የኮ ንትራት ሰራተኞች በተደጋጋሚ ባደረሱኝ  መረጃ ህጻናት ፤ ነፍሰ ጥሩዎችና አቅመ ደካማ የአእምሮ ህመምተኞች የሚቀይሩት የረባ ልብስ ፤ ምግብና ንጹህ መጠጥ በበቂ ሁኔታ እንደማያገኙ ገልጸውልኛል ። ነፍሰ ጥሩዎችና  የአእምሮ መታዎክ የደረሰባቸው እህቶች መኖራቸውን ከእስር ቤት መረጃ ያቀበሉኝ እኒህ ወገኖች ሌላው ቀርቶ የጅዳ ቆንስልና የሪያድ ኢንባሲ ተወካዮች ልባቸው ለህጻናቱ ራርቶ ወተትና መጸዳጃ እንዲያገኙ እንደማያደርጉ ጠቁመው የተገፊ ድምጻቸውን እንዳሰማ አደራ ብለውኛል !ሙሉና ዘርዘር ያለውን በድምጽና ምስል የተላከልኝን ጠልቆ የሚያመውን የድረሱልኝ መልዕክት መረጃ ዛሬ አላቀርበውም ፤ ብቻ ድምጻቸው ይሰማ ዘንድ እነሆ ደረሰብን የሚሉትን መረጃው እንዲህ አቀብላቸኋለሁ !

ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
ነሐሴ 18 ቀን 2008 ዓም

 

የማለዳ ወግ…” እማ…እንደበቅ “የህጻን ኤማንዳ ሽብር ህይዎት  !
========================================
* እልፍ አዕላፍን ያመመው የአባዎራው ፖለቲለኛ ህመም
* ህመማችን ይመማችሁ ፣ ሰብዕና ይሰማችሁ !
* የሐይማኖት አባቶች ሆይ ትለመናላችሁ  !

የእልፍ አዕላፍን … ህመም !
==================
አባወራው ወጣት ፖለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው ታመመ አሉን  ፣ አንበሳው በበሽታ ተቀስፎና ተሸንፎ በህክምና እርዳታ  መስጫ አልጋ ተጋድሞ ፣ የህክምና መሳሪያ ተገጥሞለት ተመለከትን …ሃብታሙን በአካል የሚያውቀው ብቻ ሳይሆን በስም በዝና የምናውቀው  ሁላችንም ደነገጥን  ፣ ህመሙ የመርዶ ያህል አስነባን ፣ ኢትዮጵያውያን ከአድማድ እስከ አድማስ የምንይዝ የምንጨብጠው አሳጣን …  !  የሃብታሙን በጸና መታመም እንደሰማሁ ለሚመለከታቸው የምልጃ መልዕክቴን እንደ ዜጋ ፣ ብሎም የድረሱለት  መረጃችን በገጼ ላይ አስተላለፍኩ ፣ አሰራጨሁ  !

ይህንን መረጃ ተከትሎ በሽዎች የሚቆጠሩ ወዳጆቸ ከአረብ ሃገራትና ከመላው አለም የወንድም ሃብታሙ መታመም የተጎዳ ስሜታቸውን ገልጸውኛል …እንዲያው በአጠቃላይ የሃብታሙ ህመም ያላመመው ሃገር ወዳድ አይገኝም ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም … ! የከሳሽ ፈራጁ የኢህአዴግ መንግስት ደጋፊዎች እንኳ ሰብዕና አጥቅቷቸው ያየሁበት አጋጣሚ የሃብታሙ መታመም ነበር ፣ አዝነው የተጎዳ ስሜታቸውን የገለጹልኝ ብዙ ናቸው! …  ብቻ በትንታጉ ወጣት ፖለቲከኛ አያያዝ  ያላዘነ የለም ፣ እውነቱ ይህ ሆነና እልፍ አዕላፎች ” ሃብታሙ አያሌው የተሻለ ህክምና ያግኝ ፣  የኢትዮጵያ መንግሰት የጣለበትን እገዳ ያነሳ  !” እያል በዘነበው የመረጃ ማስተላለፊያዎች የዜጋ ድምጻችን እያሰማን እንገኛለን   !

” እማ … እንደበቅ “የህጻን ኤማንዳ ሽብር ህይዎት !
=================================
በደመቀው የሮመዳን ምሽት ከሃገር ቤት የመጣች የአንድ ብርቱ ወዳጆን ልጅ ሊኑንና ጎረምሳ ልጆቸን ከነጓደኞቻቸው ሰባሰቤ ወደ አምድ መዝናኛ እያመራን እያለ ስልኬ አቃጨለ … አዲስ ቁጥር ነው ፣ መኪናየን በረድ አድርጌና ወደ አንዱ የመንገድ ጫፍ ጠጋ ብየ ስልኬን አነሳሁ ፣ እንባ የሚተናነቃት አንዲት እህት ስለ ሃብታሙ ስቃይና የተሰማትን ሃዘን በእልህ ቁጭት ገለጸችልኝ … ” አላህ አለ ፣ አላህ ፍርዱን ይሰጣል! ” ብላ እስክትሰናበተኝ በውስጤ ጥልቅ የተጎዳው ስሜቷ አልጠፋም…

ሃብታሙን በተጻፈውና ባየችው እንጅ በአካል የማያውቀው የዚህች ሰብአዊ እህት ቁጭትና አዘኔታ የወገን ኩራት ስንቅ ሲሆነኝ ሌላ ህመሜን ግን ጫረው  …የጫረብኝ ህመም አባት ሆኘ ከማውቀው የልጅ ፍቅር የተገናኘ ነውና ህመሙ ብርቱ ነው …  ውስጤን ሲያንገላታው  የሰነበተው የሃብታሙ የአራት አመት ልጅ የኤማንዳ መከራ ነበር  ! ኤማንዳ ህመሜን አበዛችው …ታሪኩን ከቀናት በፊት የሃብታሙ የክፉ ቀን ፣  የቅርብ ወዳጅ የሆነው ዳንኤል ሽበሽ ነው ያካፈለን …ያ የኤማንዳ የውስጥ እውነት የዳኒ ምስክርነት ቃል ቀልቤን ጨምድዶት ውሎ አድሯል  🙁  ” እማ እንደበቅ! ” ስላለችው የሃብታሙ ቅምጥል  የኤልዳማ ሽብር ህይዎት ህመም ዳንኤል ካስተላለፈውን መልዕክት ሳልወጣ ታሪኩን ሰብሰብ አድርጌ አስቃኛችኋለሁ ! የፈቀዳችሁ ብቻ ተከተሉኝ …

ህጻን ኤማንዳ ከሀምሌ አንድ ቀን 2006ዓ.ም ጀምሮ ታስሮባት ለሁለት አመት ከእናትዋ ጋር አባቷን ለመጠየቅ ወደ ማዕከላዊና ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ተመላልሳለች።  በእኒህ ሁለት አመታት ለሁለት ዓመቷ ህፃን ህግ አስከባሪ ፖሊስ ማለት ጭራቅ ሆኖ ተቀርጾባታል ፣ የደንብ ልብስ የለበሰ ህግ አስከባሪ ፖሊስ ለእርሷ ስታየው የምትበረግግ ጠላቷ ይሆን ዘንድ ተመርዛለች … የሁለተኛ አመቷን  ልደት በማዕከላዊ ሶስተኛ ዓመቷን በቂሊንጦ ወህኒ ቤት አክብራለች ፣ ልደቷን  በፖሊስ ከተከበበ አባቷ ጋር ላፍታ አክብራ ስትመለስ ከአባቷ የለያያት ፖሊስ መሆኑን ህጻኗ አውቀዋለችና ፖሊስን እንደ እንደ ሠይጣን ፣ ጭራቅ መፍራት ይዛለች … !

ህጻን ኤማንዳ በእስር ቤት ቆይታው በሽታ ላይ የወደቀው አባቷ  ሀብታሙ አያሌው ከእስር በነጻ ቢፈታም ህመሙ ጸንቶበት የአባቷን ስቃይ ተመልካች ሆነች …ምንም እንኳን ሃብታሙ በነጻ ከእስር ተፈትቶ አቃቤ ህግ ባቀረበው ይግባኝ ለመከራከር ቢፈቀድለትም ህመሙ አላላውስ ብሎ በርቶበታል …ህመሙ ከፍ ወዳለ ደረጃ ደርሶ በሃገር ውስጥ መታከም ስለማይችል ከሃገር ወጥቶ መታከም እንዳለበት ሐኪም መረጃ ሰጥቶታል ፣ ዳሩ ግን ጉዳዩ በፍርድ እየታየ በመሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ካገር እንዳይወጣ እግድ ተጥሎበታል  ! ህክምናው እያደር ሲበረታ ለፍርድ ቤቱ  የተሻለ ህክምና ያገኝ ዘንድ የተጻፈለትን የሀኪም ማስረጃ በማቅረብ  እገዳው ተነስቶለት  ካገር ውጭ ይታከም ዘንድ በጠበቀው በኩል ያቀረበው አቤቱታ አዎንታ ተነፈገው !

ሃብታሙ  ከሀገር ወጥቶ የመታከም ተስፋው በተጣለበት እገዳ ምክንያት ሲጨልም የጨነቃቸው ቤተሰብና ወዳጆቹ በባህል ህክምና እንዲያገኝ ሌላ መላ መቱ  !  … ከአዲስ አበባ 40 ኪ.ሜ ርቀን በአንድ ገጠር ቀበሌ ውስጥ ህክምና ጀመረ … በባህል ህክምናው ከባድ የስቃይ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ የባህል ሀኪሙ ወደ መኖሪያ ቤቱ መጥቶ እንዲረዳው የተደረገው ተማጽኖ ተሳክቶ የባህል ሀኪሙ ወደ ሃብታሙ ለመምጣት ፍቃደኛ ሆኑ ፣ ባለ ባህል ሐኪሙ የፓሊስ አባል የደንብ ልብሳቸውን እንደለበሱ ወደ አባወራው ወጣት ፖለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው ቤት ደረሱ …  በር አንኳኩተው በር ሲከፈትላቸው ብላቴናዋ የሃብታሙ ልጅ ኤማንዳ  ተመለከተች … በድንጋጤ ወደ ኋላ በመሮጥ የእናቷን ቀሚስ ይዛ ‹‹ እማ … እማ … እንደበቅ ፓሊስ መጣ ›› እያለች ግቢውን በጩኸት አደባለቀችው  🙁  ኤማንዳ በሁለት አመት የማዕከላዊና የቂሊንጦ  ምልልስ ፣ በልደቷ ቀን … ያየቻቸው ፣ የምታውቃቸው ፖሊሶችና የፖሊስ የደንብ  ልብስ  የለበሰ ያሸብራታል  🙁 እናም በገዛ ቤቷ ለአባቷ ፈውስ በመጣው ፖሊስ ሀኪም ትሸበር ዘንድ ግድ ሆነ  🙁  የኤማልዳን ሽብር ህይወት ህመም ዳንኤል በምስክር እማኝነቱ ካስተላለፈው መረጃ ጥቂቱ ህመም የጫረው የኤማንዳ ህመም የእኔን ልጆች ፣ የጋዜጠኛ እስክንድር ልጅ ፣ የጋዜጠኛ ውብሸት ልጅ  ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከመደረሱ የሚያሳድጋቸው ልጆች .. ብቻ ሳይሆን በግፍ የሚንገላቱ የብዙ ሽህ ወገኖች ልጆች  ህመም ነው  🙁

የሐይማኖት አባቶች ሆይ ስሙን  !
======================
አንደበተ ርቱዑ የሃብታሙ አያሌው ዛሬ ህመሙ ከፍቶበት ከላይ የፖሊስ ደንብ ልብስ አይታ ስትሸበር በምናብ ያየናት ህጻን ኤማንዳ ፣ በክፉ ደጉና በእንግልቱ ከጎኑ ያልተለየችው ባለቤቱ ፣ ወዳጆቹ ፣ አፍቃሪዎቹና ራዕዩን ተከትለን የምንወደው አፍቃሪዎቹ በሃብታሙ ህመም ታመን ከፍቶናል  🙁 ህመሙ የጸናበት ሀብታሙ እግዱ ተነስቶለት የተሻለ ህክምና ያገኝ ዘንድ እልፍ አዕላፍ ዜጎች መንግስትን እየተማጸንን እንገኛለን   !

የሐይማኖት አባቶች ሆይ  !  ወዴት ናችሁ  ? እያልን ትናንት አላደረጋችሁትምና አንወቅስ አናወግዛችሁም  ! ዛሬ ስለ ፈጣሪ ብላችሁ ፣ ሰብዕና ተሰምቷችሁ የተጨነቀው  ወንድማችን ሃብታሙ ፈውስ ያገኝ ዘንድ ምህረትን ለምኑለት  ! እንደ ሀገር ሽማግሌ ፣ እንደ ሃይማኖት አባት ደግሞ  አባወራው ፖለቲከኛ ወጣት ሃብታሙ አያሌው ከሐገር እንዳይወጣ የተጣለበት እገዳው ተነስቶለት ወደ ውጭ ሃገር ሄዶ እንዲታከም የእናንተን ድምጽና ግፊት ይሻል ፣ የቤተሰቡን ከምንም በላይ ብላቴና የኤማልዳን ህመም ተረዱት ፣  አባታዊ ጣልቃ ገብነታችሁ ያስፈልገናል  ! ከፈጣሪ በታች ድምጽ ትሆኑን ዘንድ እንማጸናችኋለን  !

ከምንም በላይ ሁሉን ማድረግ የማይሳነህ አምላክ ሁሉም በእጅህ ነውና ተማለደን   ! ለወጣቱ ፖለቲከኛና አባወራው ሃብታሙ አያሌው ምህረት ላክለት  !

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on August 26, 2016
  • By:
  • Last Modified: August 26, 2016 @ 11:41 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar