www.maledatimes.com ለተከበሩት አቶ ደብረ ጽዮን (ዶክተርነትዎትን በተረጋገጠ የትምህርት ማስረጃ ስላልሆነ ዶክተር ብሎ መጥራት ያሳፍረኛል ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ለተከበሩት አቶ ደብረ ጽዮን (ዶክተርነትዎትን በተረጋገጠ የትምህርት ማስረጃ ስላልሆነ ዶክተር ብሎ መጥራት ያሳፍረኛል )

By   /   August 31, 2016  /   Comments Off on ለተከበሩት አቶ ደብረ ጽዮን (ዶክተርነትዎትን በተረጋገጠ የትምህርት ማስረጃ ስላልሆነ ዶክተር ብሎ መጥራት ያሳፍረኛል )

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 7 Second
ይህንን አጭር ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ መሰረቱ የአምባገነንትዎትን አንደበት ምን እንደሆነ ለመናገር ሲሆን ምናልባትም እርስዎ ይህንን ከምንም ላይቆጥሩት ይችሉ ይሆናል ሰፊው ህዝብ ግን ከምን ሊያደርሰው እንደሚችል አምናለሁ እና ነው ።
በመጀመሪያ ደረጃ የናቁት እና ያዋረዱት ሰፊውን እና መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ መደምሰስ እና መግደልም የፈለጉት ይህንኑ ህዝብ እንደሆነ በጥንቃቄ ተረድተውት ከአንደበትዎት ያወጡት ቃላቶች ይመሰክሩታል።
ይህም ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝብ ታጋሽ እና ፍቅር የለበሰ ስለሆነ እንጂ እንደ እርስዎ ደም የጠማው ህዝብ ቢሆን ኖሮ የወያኔ ስርአት 25 አመታትን ባልተቀመጠ ነበር ፣ምናልባትም ስርአተ ቀብሩ ይፈጸም የነበረው የዛሬ 11 አመት አካባቢ እንደነበር አይዘነጋም::

ታዲያ ዛሬም የልጁን ንጹህ ደም በመንገድ እንዳይፈስ አንገቱን የደፋው ህዝብ በቃኝ የወያኔን አንገፍጋፊ ኑሮ አልፈልግም በማለት በአደባባይ ጩኽቱን ባሰማበት ወቅት እናንተው የባሩድ እሳት አውርዳችሁበት አሸባሪ በማለት ሰይማችሁታል ፣መቼም ከአሜሪካውያኖች እየወረሳችሁ አሸባሪ የሚለውን ቃል የምትጠቀሙት ደካማ አመራሮች መሆናችሁን 92 ሚሊዮን ህዝብ ሊነግራችሁ ይችላል፣ሆኖም ዘርን ከዘር ሃገርን ከሃገር ህዝብን ከህዝብ አጋጭታችሁ ዛሬ ደግሞ መሬትን በቅርምት በመሸጥ እና በመለወጥ ያንን እርስዎ የፈለቁበትን ደረቁን የትግራይን መሬት ምርታማ እንዲሆን ለም አፈር ያለውን የአማራን ፣ኦሮሞን ና የጋምቤላውን መሬት በራሳችሁ አመራር ሰዎች ቁጥጥር ውስጥ እንዲሆን ለማድረግ ጥረታችሁን እያደረጋችሁ ትገኛላችሁ ፣ይህ አልሳካላችሁ ያለው ከ12 አመታት ቆይታ በሁዋላ በመሆኑ አዝናለሁ፣ ገና በእንጭጩ ቢቆረጥ ኖሮ እናንተም ዛሬ ላይ አትኖሩም ነበር ለዚህም መሰናክል ለሆነ ችግር ባልገጠማችሁ እላለሁ።

ትክክለኛው የኢትዮጵያ መለያ ባንዲራ


ምናልባትም እንደ ምሳሌ ሊጠቀስ የሚገባው በናዝሬት የተከናወነው የዛሬ 12 ዓመታት ሲሆን ከዚያም በሁዋላ በ2007 የዚሁ የመሬትን ማካለል ስብሰባ ተከናውኖአል ስለዚህ እናንተ ለጋዜጠኞች ማስፈራሪያ እሰጣችሁ ምንም መረጃ እናይወጣ አድርጋችሁ ነበር። ሆኖም ግን የሃገሩ ጉዳይ ይበልጥብኛል ያለ ጋዜጠኛ በሙሉ በአገኙት አጋጣሚዎች በሙሉ ተጠቅመው ለህዝብ አደረሱት ስለዚህ የኦሮምያም ጩኸት ሆነ የአማራው ተሰሚነት እንዲኖረው እና እናንተም ስርአታችሁን ትይዙ ዘንድ ብትጠየቁም አልሆንላችሁ አለ።

ምን ይደረግ ያደለው ህዝብ መንግስቱ ይቅርታ ይጠይቀው ነበር ሆኖም ግን በማስፈራራት እና ዛቻ አንገቱን እየደፋ ንጹሃኑን ህዝብ እና ገበሬ ያዛችሁን በእድገት መሰረት በሚል የገጠሩንም ሆነ የከተማውን እንዳይናገር በካድሬዎችችሁ አማካይነት ሁሉም ነገር እንዲጠብ አድርጋችኋል ፣ዛሬስ ህዝቡ ሲነቃ እና ማንነታችሁን ሲያቅ አልገዛም ከአሁን በሁዋላ ዘረኝነት ፣ክፍፍል እንዲሁም ጎጠኝነት ለእኔ ምንም አይጠቅመኝም ብሎ ሲያድምባችሁ የጦር መሳሪያ በህዝቡ ላይ ለማዝመት ወሰናችሁ…….አዎ የአምባገንነ መውደቂያው ሲደርስ ይህ ነው የሚከተለው ፣ ስለዚህ ነገ ከተጠያቂነት የሚያድናችሁን ስራ ብትሰሩ ያዋጣችሁ ነበር። ይህ ካልሆነ ግን በሰላማዊ መንገድ የዘረፋችሁትን እንደዘረፋችሁ ከሃገሪቱ ብትወጡ አለበለዚያም በሰላማዊ መንገድ ከህዝቡ ጋር ብትኖሩ መልካም ይሆን ነበር ህዝቡም የይቅርታ ልቡን ከፍቶ እናንተም ከወገናችሁ ጋር በሰላማዊ መንገድ የምትኖሩበት መንገድ በተከፈተ ፥ይህንንም ግን እያደረጋችሁት አይደለም ይበልጡኑ ህዝቡን ገፍታችሁ ደም ለማፋሰስ እየሮጣችሁ ቢሆንም ያልተረዳችሁት ነገር ቢኖር የመከላከያ ሰራዊታችን የህዝብ ልጅ መሆኑን የረሳችሁት ይመስለኛል ። ስለዚህ ህዝቡም በተጠንቀቅ ይጠብቅዎታል።

 የእናንተ ማስፈራራት ይህዝብን ውሳኔ ከምንም አያደርሰውም ይበልጡኑ በጥንቃቄ እንዲጓዝ እና መፈንቅለ መንግስታዊ ጉዞ እንዲያደርግ ብርታቱ እና የጉልበቱ ጥንካሬ ይሰጠዋል ብለን እናምናለን ፣ለእርስዎ እና ለፓርቲዎም ችሩን ይግጠማችሁ ። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ፣አሁም ሰላም ለኢትዮጵያችን
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on August 31, 2016
  • By:
  • Last Modified: August 31, 2016 @ 3:02 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar