አንደኛ – የማንም ንብረት ቢሆን በተያዘው የሕዝባዊ እምቢተኝነት ሰበብ ማቃጠሉና ማውደሙ ጠቃሚም ተገቢም አይደለም – መራራው የትግል ጉዟችን ብዙ ማስተዋልና ብዙ ማሰላሰል ያለበት ይሁን፡፡ በርግጥ በእስካሁኑ ሁኔታ የዐማራው ትግል ብስለትና ጨዋነት የተሞላበት መሆኑና ልዩ ጥንቃቄ መደረጉ የሚያስመሰግን ነው፡፡ አንዳንዴ የምናየውን የሚቃጠል ወይ የሚወድም ንብረትን ግን ወደ ሕዝብ ሀብትነት ለውጦ ለነጻነት ትግሉ እንዲጠቅም ማድረግ ይቻላል፡፡ ለምሣሌ የዳሸን ቢራን መኪና ወይም የወያኔዎችን ማናቸውንም ከሀገርና ከሕዝብ የዘረፉትን ንብረት ከማውደም በሕዝብ ቁጥጥር አውሎ ለትግሉ ስኬት እንዲያገለግል ማድረግ ይቻላል፡፡ መኪናውን ለዕቃና መሣሪያ ማመላለሻ ቢያውሉት የሚያስከፋ አይደለም፡፡ በመነመነ የሀገር ሀብት በእልህ እየተነሳሱ ቢያቃጥሉና ቢያወድሙ የገዛ ንብረትን እንደማውደም ነውና ሊመከርም ሊበረታታም አይገባውም፡፡
መደረግ ያለበት ጥንቃቄ ግን መረሳት የለበትም፡፡ እነዚህ ሰዎች የመጨረሻ ከይሲ ስለሆኑ የሚበሉና የሚጠጡ ነገሮች ላይ በተለይ በጣም መጠንቀቅ ይገባል፡፡ ጭራቅ ለሰው አያዝንም፡፡ ጭራቅ በሰው ሀዘን የሚደሰት ዐረመኔ ፍጡር ነው፡፡ ወያኔዎች ደግሞ የመጨረሻ ጭራቅና ጨካኞች እንደመሆናቸው ሕዝብን ለመፍጀት የማያደርጉት ነገር የለም – በዚያን ሰሞን በአንድ የጎንደር አካባቢ የውኃ ጎተራ(ጋን) በመርዝ ሊበክሉ እንደነበር ሰምተናልና ከተጨማሪ ጥቃት ራሳችንን ለመከላከል ነቅተን መጠበቅ አለብን – በየትም ቦታ ያለን ዜጎች እንጠንቀቅ፤ ሥራም እንከፋፈልና ግዳጃችንን ባግባብ እንወጣ፡፡ ስለዚህ የሚያዙ ንብረቶችን በዐዋቂና ሲቻል በቤት እንስሳት (ሌላ አማራጭ ስለሌለ እንጂ ይህም ያሳዝናል) በመሞከር አገልግሎት ላይ ማዋል ይገባል፡፡ መኪናና የመሳሰሉ ንብረቶችን ግን ለትግሉ ማዋል ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፡፡
ሁለተኛ – የመሣሪያ ችግር ብዙም አንገብጋቢ አይመስለኝም፡፡ ወጣቱ እየተደራጀ የወያኔ ሠራዊት ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈጸም መሣሪያ መቀማት፣ ግምጃ ቤቶችን በግልም በቡድንም መዝረፍ… ስለሚቻል በቀውጢ ሰዓት የመሣሪያ ችግር እስከዚህም ነው፡፡ ችግር ሊሆን ይችል የነበረው የወኔ ማጣት ነበር፡፡ ይህ ችግር ደግሞ የተፈታ ይመስለኛልና መበርታት ነው፡፡ የቆረጠ አንድ ሰው ብዙ ጀብድ ይሠራል፡፡
ሦስተኛ – ጎጃምና ጎንደር ሲጠነክር ሌሎች ዳተኛ ሆነዋል፡፡ ይህ እጅግ አደገኛ ነገር ነው፡፡ ሁሉም መነሣት አለበት፡፡ ችግራችንና ብሶታችን እኩል እንደመሆኑ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከደቡብ እስከ ሰሜን ሁሉም በአንዴ ተነስቶ ወያኔን እስከወዲያኛው መደምሰስ አለበት፡፡ ወያኔዎች የመጨረሻ ፈሪዎች ናቸው፡፡ ሁሉም በአንዴ ቢነሳባቸው ሽንታቸውን እየረጩ ነው በእግር አውጪኝ የሚሸሹት፡፡ በዚህ ይታወቃሉ፡፡ በሀሽሽና በአነቃቂ ዕፆች እየተደፋፈሩ፣ በሳቦታጅና በከሃዲ የደርግ ጦር አዋጊዎች ሸፍጥና በሱዳን ደንቃራና መተት እንዲሁም በጠላት ድጋፍና በሕዝባዊ ኩርፊያ ምክንያት ክፍት ቤተ መንግሥት አግኝተው በቀላሉ መግባት ስለቻሉ ብቻ ጀግኖች መስለዋችሁ ከሆነ ስህተት ነው – እንደዚያ ያለ ወርቃማ ዕድል ባገኝ እኔና ስምንቱ ልጆቼም ኢትዮጵያን መቶ ዓመት ልንገዛ እንችላለን፡፡ ጀግናው በርግጥም ጊዜ እንጂ እነሱ አይደሉም፡፡ ዕንቆቅልሹ ይፈታ፡፡ አፍዝ አደንግዙም ማርከሻው ባፋጣኝ ተፈልጎለት ከእሥራችን እንፈታ፡፡
ስለዚህ በተለይ ወሎና ሸዋ በአፋጣኝ ተነስቶ መንገዶችን መዘጋጋት አለበት፡፡ ብዙ ነገር እንዳያሸሹ የሸዋና የወሎ መንገዶች በቶሎ መዘጋት አለባቸው፤ ሁሉም በያካባቢው ያሉትን መንገዶች ቢዘጋ ብዙ ጉዳት አይደርስም፡፡ አደጋን መከላክል ደግሞከሩቅ ነው፡፡ ከሰንዳፋና ከሱልልታ ጀምሮ መንገዶችን ጥርቅም እያደረጉ በመዝጋት መፈናፈኛ ቢያሳጧቸው ምንም አያመጡም፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ቀላል ነው፡፡ አሥር ቆራጥ ወጣቶች አንድ ኦራል ሙሉ ወታደር ሊማርኩ ይችላሉ፡፡ መጠነኛ ወታደራዊ ሥልጠና ግን ማግኘት ይኖርባቸው ይሆናል፡፡ በተረፈ ግን አንድ ፍልስጥኤም ምን ያህል የጀብድ ሥራ እንደሚሠራ የምናውቅ ሰዎች አንድ ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ከልቡ ከተነሣ ምን ያህል ወደርየለሽ የጀግንነት ተግባር ሊፈጽም እንደሚችል እንገነዘባለን፤ በጎጃምና በጎንደር እያየንም ነው፡፡
አራተኛ – የአዲስ አበባ ከእምቢተኝነቱ ማዕድ አለመሳተፍ ለበጎ ነው፡፡ አዲስ አበባ እስካሁን ብትሳተፍ የክፍለ ሀገራቱ እንቅስቃሴ ይታፈን ነበር፡፡ ስለዚህ በእስካሁኑ ሁኔታ የሸገር መተኛት ብዙም መጥፎ አይመስለኝም፡፡ አዲስ አበባ የመጨረሻው የወያኔዎች ህቃታ መውጫ ናት፡፡ ከአሁን በኋላ ግን ሁሉም በአንዴ በመነሣት ሊረባረብባቸው ይገባል – ጊዜ የለንም፡፡ በሰሞኑ የሕዝብ እንቅስቃሴ አካሄድ ሁሉም ከተረባረበ ወያኔን ለማጥፋት አንድ ወርም በጣም ብዙ ጊዜ ነው፡፡
ማድረግ የሚገባው በሁሉም ሥፍራ ወጥሮ ማጣደፍ ነው፡፡ መቼም እርግጠኛ ነኝ 50 ሚሊዮኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጸረ ወያኔ እንቅስቀሴው በንቃት ቢሳተፍ ይህን ሕዝብ ጨፍጭፎ መጨረስ የሚችል አጋዚ አይኖርም፡፡ እስካሁን የኖሩት በማስፈራራት እንጂ በርግጥም የሚፈራላቸው ኃይል ኖሯቸው አይደለም፡፡ ዛፍ ላይ ወይም ፎቅ ውስጥ ተደብቆ በአጉሊ መነጽር በሚመራ ልዩ ጠብመንጃ የንጹሓንን አናት መበርቀስ የዕይታንና የማነጣጠርን ብልሃት እንጂ ጀግንነትን የሚጠይቅ ትልቅ ሥራ አይደለም፡፡ በዚህ የ“ሥራ” መስክ ቢሰለጥን የ5 ዓመት ሕጻንም ብዙ ጥፋትና ውድመት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ስለሆነም ሁላችንም ሳንፈራ ለጋራ ነፃነታችን በአንዴ ብንነሣ ይሳካልናል፡፡ እኔ መቼም በጎጃምና በጎንደር እንዴት እንደኮራሁ ቃላት አይገልጹትም፡፡ አዲስ አበባ እስኪመጣ በጣም ጓጉቻለሁ፡፡ አንድ አስተባባሪ ኃይል በኅቡዕ ተፈጥሮ ይህ ለጊዜው የሚጎመዝዝ በኋላ ግን የፍሬው ጥፍጥና በልጅ ልጆቻችን እየደመቀ የሚሄድ ተግባር በቶሎ መጀመር ይኖርበታል፡፡
አምስተኛ – በዚህ ሕዝባዊ ትግል የፖለቲካ ፓርቲዎች ጎልቶ አለመውጣት ወይም የአንዳንዶቹ እንደመትረየስ የሚንደቀደቅ አፍ በስማም እንደተባለበት ሰይጣን ጸጥ ረጭ ማለት ለበጎ ነው፡፡ ምክንያቱም ሕዝቡ በትግሉ የሚያመጣውን ነፃነት ከአሁን በኋላ ማንም እንደፈለገ ሊቸረንና ሊነሣን አይችልምና፡፡ እስካሁን የተጎዳነው ሕዝብ ልክ እንዳሁኑ በስፋትና በጥልቀት በባለቤትነትም ስሜት የመራው ሕዝባዊ አብዮት ስላልነበረን ነው፤ በዚህም ሳቢያ የሕዝብን የነፃነት ባለቤትነት ማጣጣም አልቻልንም፡፡ በደርግ መነሻ አካባቢ እርግጥ ነው እንዳሁኑ ባይሆንም የተወሰነ ሕዝባዊ ተሣትፎ እንደነበርና በኋላ ግን የሕዝቡ አብዮት በወታደር እንደተጠለፈ እናውቃለን፡፡ የማይሙ ደርግ የሥልጣን ጠለፋ ስህተት ነበርና ለባሰ ውድቀት ዳርጎን አለፈ፡፡
ወያኔም የተነሣው በአንድ አካባቢ ሕዝብ በመሆኑና መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለማቀፉ የሆነው ሁሉ ሆኖ ለዚህ በቃን፡፡ አሁን ግን የፈጣሪ ተዓምር ተጨምሮበት ባልታሰበ አቅጣጫ በፈነዳ የብሶት ኒዩክሌር ሀገራችን ከነዚህ መርዘኛ የኮብራና የአናኮንዳ እባቦች በቅርቡ ነፃ ልትወጣ የነፃነት ምጥ ተፋፍሞ ይገኛል፡፡ የምትወለደው ነፃነት ለኔም ትጠቅመኛለች የሚል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይተባበርና ካለብዙ መስዋዕትነት እምዬ ኢትዮጵያን “እንኳን ማርያም ማረችሽ” ለማለት እንብቃ፡፡ ሁሉም ወደየኅሊናው ከተመለሰና ከተባበረ ይህ ታሪካዊ ድርጊት እጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡ ከፍርሀት ቆፈን መውጣት ብቻ ነው መፍትሔው፡፡
ስድስተኛ – በዚህ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ለመሣተፍ ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ አናብጅ፡፡ ሙሰኛም ሳይቀር ተጸጽቶና ከልቡ አዝኖ የበደለውን ሕዝብ ለመካስ ቆርጦ ይነሣ፡፡ ክፉ ሥራውን ሕዝብ እንደሚያውቅ ሁሉ በነፃነት ትግሉ የሚያበረክተውን በግልጽ የሚመዘግብለት ሕዝብ የፊትና የአሁን ተግባሩን በማመዛዘን ይቅርታ ያደርግለታልና በካፈርኩ አይመልሰኝ በጥፋት ድርጊቱ አይቀጥል፡፡ ዜጎችም ከከንቱ ብቀላና ከተንኮል አስተሳሰብ እንታቀብ፤ ጤናማ ኅሊና ይኑረን፤ አጥፊ ሲጸጸትም ምሕረት የማድረግ ባህልን እናዳብር፡፡ ሰው የገደለም ቢሆን በእውነት አልቅሶና ሀገሬንና ሕዝቤን በድያለሁ ብሎ በዚህ ወሳኝ ወቅት ወደ ነፃነቱ ጎራ በመቀላቀል ከጥፋቱ ጋር የሚመጣጠን መልካም የነፃነት ተጋድሎ ካደረገ ቢሰዋ እንኳ ሕዝቡ ይቅርታውን ይቸረውና ቀሪ ትውልዱ አንገቱን ቀና አድርጎ እንዲሄድ ምቹ ሁኔታ ይፈጠርለታል፡፡ መጥፎው ነገር ወንጀልን በወንጀል እያደሱ መጓዝ ነው፡፡ ኅሊናችንን እንጠብ፣ የነፍሳችንን መንገድ እናስተካክል፡፡ ተበልቶ ለእዳሪ፣ ተጠጥቶ ለሽንት ለሚሆን የሞተ እህል ውሃ ብለን ዘላለማዊነታችንን ባጭሩ አንቅጨው፡፡ ለእህል ውኃ የሚኖሩ እንስሳት ብቻ እንጂ ሰዎች ሊሆኑ አይገባም፡፡ ከእንስሳትም እኮ ለሰው የሚያዝኑና ለሆዳቸው የማያድሩ እንስፍስፎች አሉ – ለምሣሌ ዶልፊን ለሰው አዛኝና አልቃሽ ነው፡፡ ካሳዘንከው ጅብ እንኳን ሳይበላህ አዝኖልህ ሊምርህ ይችላል፡፡ ሰው እንደወያኔ ከጅብ ካነሰ ምን ይባላል? ከጅብና ከወያኔ ማነስ ትልቅ የተፈጥሮና የሥነ ሕይወታዊ ቀመር ችግር ነው፡፡
ሰባተኛ – አጋዚዎችና አንዳንድ በወያኔ ፍቅር ያበዱ ትግሬዎችን እንዲሁም ከየትኛውም ጎሣ የተገኙ ሆዳም ጅቦችን እንጠንቀቅ፡፡ ፍቅር መጥፎ ነው፡፡ ፍቅር ያሳብዳል፡፡ ፍቅር ሎጂክና ምክንያታዊነትን የማያውቅ ደደብ ፍጡር ነው፡፡ እርግጥ ነው ፍቅር ዓይነቱ ብዙ ስለሆነ ሁሉም ፍቅር በዚህ እኔ በምለው የፍቅር ጎራ ውስጥ ይካተታል ማለት አይደለም፡፡ የዘርና የጎሣ ፍቅር፣ የሆድ ፍቅር፣ በዓላማና በጥቅም ትስስር የሚመሠረት ፍቅር… እጅግ አደገኛ ነውና ወቅቱ እስኪያልፍ አንደበታችንን ሰተር፤ የምንናገረው ከማን ጋር እንደሆነ ማወቅ፣ ፀጉረ ልውጥን መከታተል… ይገባል እንጂ ልባችንን ለማንም ለማናውቀው ሰው ሁላ መስጠት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፤ በሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ክፉ ነገር እንዳንሸምት ጥንቃቄ እናድርግ፡፡
ስምንተኛ – በጥቅሉ ይህች ጊዜ እግዜር የፈቀደልን የሽልማት ጊዜ ናት፡፡ ካልተጠቀምንባት ግን እንደዋዛ ልታልፍ ትችላለች፡፡ ካለፈችን ደግሞ ዳግመኛ ላናገኛት እንችላለን (ሰሜን ኮሪያን ያዬ በነጻነት ትግል አያላግጥም – እያንዳንድሽ ዘላለምሽን የወያኔ ባርያ ሆነሽ ትቀሪያታለሽና ዋ! ብያለሁ፡፡) ይህችን ዕድል ዳግም ካላገኘናት የወያኔን ግፍና በደል በምንም ዓይነት ተዓምር አንችለውም፡፡ የወያኔን የብቀላ ብትር የቻለ ፍጡር እስካሁን በምድር አልተገኘም፡፡ ወያኔ እንኳስ በሕይወት የሚገኝን ፍጡር የሞተን ሰው አጥንትና የዘመናት ዐፅም ከመቃብር ቆፍሮ እያወጣ በጨንገር የሚገርፍ ልዩ የአጋንንት መንጋ ነው፡፡ እነፕሮፌሰር አሥራትን የገደለ … እነሀብታሙ አያሌውን በቁም ስቅል እየገደለ ያለ ዐውሬ ከአሁን በኋላ ስድስት ወር እንኳን ሥልጣን ላይ ቢቆይ በተለይ አንድም ዐማራ በሕይወት አይተርፍም ቢባል ከፈጠጠው እውነታ አኳያ ብዙም ማጋነን አይደለም፡፡ ይህን ሁሉም ይረዳ፡፡ አሁን ደግሞ ዐማራና ኦሮሞ በመቀራረባቸው ምክንያት ወያኔዎች መርዝ እንደበላ ውሻ ጨርቃቸውን ጥለው አብደዋልና ኦሮሞም ሆነ ዐማራ ዕድላችሁ አንድና አንድ ነው – መጥፋት፡፡ ስለዚህ ሁልሽም ይህን የዲያብሎስ ግሪሣ በአንድ ጊዜ ገጥመሽ አስወግጅ፡፡ ስትፎካከሪ ከርመሽ ወያኔ በረዳቶቹ በነዚያ የአጋንንት ጭፍሮች አማካይነት እንደባብ አፈር ልሶ ነፍስ ከዘራ ወዮልሽ፡፡ እነሱም የሚመጻደቁት የድመት ነፍስ እንዳላቸው ስለሚያምኑ ነው፡፡
እነዚያ የዐድዋ ተሸናፊ ሉሲፈራውያን የሩዋንዳ ሕዝብ እርስ በርሱ ከተጨፋጨፈ በኋላ ያለ አንዳች ይሉኝታ በዕብሪት ምን ነበር ያሉት? አዎ፣ እኔ ላስታውስህ – “እንደሚጨፋጨፉ አስቀድመን እናውቅ ነበር!” ነው ያሉት፡፡ ምን ማለት ነው? አልነግርህም፡፡ አልግርሽም፡፡ ግን ጠንቀቅ እንበል፡፡ ትዕቢት የሰይጣን ዋናው መገለጫ መሆኑን ግን እንረዳ፤ ጥጋበኛው ሕወሓትም ትምክህቱንና ዕብሪቱን ያገኘው ከነሱው ከጌቶቹ ነው፡፡ የወያኔን ጌቶች ማመን ቀብሮ ነውና “እገሌ ይደርስልናል” ማለቱ በፍጹም አያዋጣም፡፡
አዳኛችን አንድ ነው – እግዚአብሔር፡፡ ነፃ አውጫችን አንድ ነው – እኛው ራሳችን፡፡ ከሩዋንዳዎች መማር አለብን፡፡ ከሦርያዎች መማር አለብን፡፡ ከሶማያሊውያን መማር አለብን፡፡ ከየመኖች መማር አለብን፡፡ … እነዚህና ሌሎቹም እንደኛው እልከኛ የዘረኝነትና የጎሰኝነት ሾተላይ ገጥሟቸው ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰባቸው እናውቃለን፤ እነማን እንደሚያጨፋጭፏቸውም አሣምረን እናውቃለን፡፡ ለአብነት ነጫጭባዎቹ ቢፈልጉ ሦርያ በአንድ አዳር ሰላም ልታገኝ ትችላለች፡፡ ነገር ግን ወዲያ ማዶና ወዲህ ማዶ ያሉ ከአንድ ግንድ የተገኙ ለይምሰል ግን የማይዋደዱ የሚመስሉ የሉሲፈር ልጆች በእጅ አዙር( ፈረንጆቹ proxy war በሚሉት) እየተዋጉ የመሣሪያ መፈተሻ አድርገዋት ቀሩ – ያሳዝናል – እኛ ግን የደጉ አምላክ ልጆች ነንና ከዚህ ብዙ ልንማር ይገባናል፡፡ ወያኔዎች ደግሞ እንኳንስ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ለትግራይ ክፍለ ሀገር ሕዝብም የማይመለሱ የእፉኝት ልጆች ናቸው – ከሥልጣንና እንደመዥገር ከተጣበቁበት ሀብት አንጻር የሚመጣባቸውን ሁሉ የእናታቸውን ልጅ ሳይቀር በጭካኔ ይገድላሉ፤ ከመግደላቸው በፊት በሚያደርጉበት ዐረመኔያዊ ተግባርም ይዝናናሉ፡፡ ከነዚህ ሰዎች ጋር ድርድር የሚባል ነገር ደግሞ የማይታሰብ ነው፡፡ ወደ መቃብር ካልወረዱና ተራራ እሚያህል ድንጋይ ካልተጫነባቸው ልታምኗቸው አትችሉም፡፡ … ውርድ ከራስ፡፡ በጎሠኝነት ዥዋዥዌ የምትዋልሉ የትግራይ ሰዎች ካላችሁ አቋማችሁን ፈትሹ – ከሚሰምጠው የወያኔ መርከብም ባፋጣኝ ውረዱ – የወያኔ ታይታኒክ መርከብ መስመጫዋ ደርሷልና ሚናችሁን ለዩ፡፡
የተኛችሁ ተነሱ፤ ያንቀላፋችሁ ንቁ፡፡ በዚህ ሰሞን አዲስ አበባን ጨምሮ ሁሉም የሀገራችን ክፍል ለመጨረሻው አርማጌዴዎን ይነሳ፡፡ የወሎና የሸዋ መንገዶች ይዘጋጉ፡፡ ያኔ መሸሻቸው ሁሉ ሲዘጋ የሚሆኑትን እናያለን … የዚያ ሰው ይበለን፡፡ እደግመዋለሁ – ወሎና ሸዋ ከእንቅልፋችሁ ንቁ፡፡ ወለጋ፣ አዋሣ፣ ሐረር፣ ጋሙጎፋ፣ አርሲ፣ ትግራይ፣ አፋር፣ … ሁሉም በአንዴ መነሣትና የማይቀረውን ነጻነቱን መጎናጸፍ አለበት – በራስ የትግል መስዋዕትነት የሚመጣን ነጻነት ደግሞ የሚቀማ ምንም ምድራዊ ኃይል የለም፡፡
ኢትዮጵያ በውድ ልጆቿ ትግል ነፃ ትወጣለች፤ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡፡
Average Rating