በሳዲያጎ ከተማ ነዋሪ የነበረው እና ለረዥም ግዜ በነጻ ፕሬስ ጋዜጠኝነት ያገለገለው፤ ጋዜጠኛ አበራ ወጊበድንገተኛ የመኪና አደጋ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን የሰማነው፤ በጥልቅ የሃዘን ስሜት ውስጥ ሆነን ነው።ጋዜጠኛ አበራ ወጊ… ዛሬ በእስር ከሚገኘው ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር አብሮ ሰርቷል። በተለይም ማዕበልበተሰኘው ጋዜጣ ላይ ዋና አዘጋጅ በመሆን ለብዙ አመታት አገልግሏል።
አቶ አበራ ወጊ የማዕበል ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በነበረበት ወቅት፤ በበሳል ብዕሩ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮችላይ ትኩረት ሰጥቶ ጽፏል። በተለይም በዚሁ የማዕበል ጋዜጣ የፊት ገጽ ላይ፤ “ኢትዮጵያዊነት የቃል ኪዳንማተማችን ነው” የሚለውን መሪ ቃል ያመነጨው፤ አቶ አበራ ወጊ ነበር።ከዚሁ የጋዜጠኝነት ስራው ጋር በተያያዘ፤የታሰረበት እና ለብዙ ስቃይ የተዳረገበት የክስ መዝገብ፤ አነጋጋሪ እና አስገራሚ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ በህግ ስም የተስራውን ግፍ ስለሚያሳይ፤ በዚህ አጋጣሚ ለመጥቀስ እንወዳለን።
ወቅቱ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ውስጥ ውስጡን እየተካሄደ የነበረበት ግዜ ነው። እናም ጋዜጠኛአበራ በድንበር አካባቢ ይደረግ የነበረውን የተኩስ ልውውጥ በዜና መልክ አቀረበ። ዜናውን ተከትሎ… በወቅቱየትግራይ ፕሬዘዳንት የነበሩት አቶ ገብሩ አስራት፤ “በትግራይና ኤርትራ ድንበር፤ እንኳንስ ጦርነት ተነስቶ ክባድ የተኩስ ድምፅ ሊሰማ ቀርቶ፤ የባረቀም ጥይት የለም።” ሲሉ፤ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ደግሞ፤ “በኤርትራእና ኢትዮጵያ ድንበር፤ እንኳንስ ጥይት ጅራፍም አልጮኸም።” በማለት ፓርላማውን ፈገግ አደረጉት።ተከታዮቻቸውም የጦርነት ሰበር ዜና አቅራቢውን፤ ጋዜጠኛ አበራ ወጊን “ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማጣላት፤ የሃሰትዜና አቀረብክ” ብለው አሰሩት።
ጋዜጠኛ አበራ ወጊ፤ በዚህ ዜና ምክንያት እስር ቤት እያለ፤ ውስጥ ውስጡን ሲደረግ የነበረው ጦርነትተጋግሎ ሊደበቅ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደረሰ። እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ግንቦት 4 ቀን፤ 1990 ዓ.ም.በፓርላማ ደረጃ ጦርነቱ ታወጀ። ምንም እንኳን ጦርነቱ ገሃድ ቢወጣም ለአቶ አበራ ወጊ ግን ምህረትአልተደረገለትም፤ ወይም “ለካስ ያቀረብከው ዜና እውነት ነበር።” ተብሎ ይቅርታ አልተጠየቀም። ጦርነቱ ተፋፍሞእያለ፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ መግለጫ እንደ መረጃ ቀርቦም ጭምር፤ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ 2ኛ ችሎትዳኛ ሃጎስ ወልዱ፤ በአቶ አበራ ላይ የአንድ አመት ተኩል እስራት ፈረደበት።
አቶ አበራ ወጊ ከላይ በተጠቀሰው “የኢትዮጵያ ኤርትራ ጦርነት ”ለአንድ አመት ከስድስት ወር ከታሰረበኋላ ሲፈታ፤ “በሌላ ክስ ይፈለጋል” ብለው፤ ከእስር ቤቱ ውጪ የማዕከላዊ ምርመራ ፖሊሶች እየጠበቁት ነበር።ከ’ነዚህ ፖሊሶች በማምለጡ ምክንያት፤ ደህንነቶች ጭምር ጋዜጠኛ አበራ ወጊን ማደን የጀመሩበት አጋጣሚተፈጠረ። በዚህ መሃል ነው የሚወዳት አገሩን፤ ኢትዮጵያን ለቅቆ ለመሰደድ የበቃው።
ጋዜጠኛ አበራ በሳንዲያጎ ከተማ ነዋሪ በነበረበት ወቅት፤ በሃዘን እና በደስታ ከሌሎች ኢትዮጵያውያንአልተለየም። ከኢትዮጵያ ወጥተው በስደት ላይ የነበሩ ጋዜጠኞችን ለመርዳት ይደረግ በነበረው እንቅስቃሴ፤ግንባር ቀደም ተባባሪ፤ ለተቸገሩ ደራሽ እና አጽናኝ ወንድማችን ነበር። ከጋዜጠኝነቱ በተጨማሪ ለኢትዮጵያአንድነት ለቆሙ የሲቪክ እና የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ልባዊ ድጋፍ በመስጠት ይታወቃል።
በመጨረሻም በህይወት በነበረበት ወቅት በቁጭት ከሚናገራቸው ነገሮች ፤ እስር ቤት ውስጥ እያለአስፈላጊ ህክምና ባለማግኘቱ ለተባባሰ የስኳር ህመም መዳረጉን ሁሌም በቁጭት ከሚያነሳቸው ጉዳዮች ውስጥአንዱ ነው። በኋላ ላይ ህመሙ እየባሰበት ሲመጣ፤ ወደ ሆስፒታል ከወሰዱት በኋላ፤ ያልተገባ በሽታ በመርፌእንደተሰጠው፤ ይህንንም ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ በህክምና ማወቁን በቁጭት ይገልጽልን ነበር።
የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዘዳንት የነበሩት፤ አቶ ክፍሌ ሙላት ተጨማሪምስርነታቸውን ሲሰጡ፤ “በአቶ አበራ ወጊ ላይ የተደረገበትን በደል ይህ ብቻ አይደለም። ከእስር ቤት ከወጣ በኋላየነገረኝ አንድ ጉዳይ አለ። ‘አንድ ቀን ለኢትዮጵያ ህዝብ ምስክርነትህን ትሰጥልኛለህ።’ በማለት፤ በእስር ላይ ሳለ ዘርእንዳያፈራ ለማድረግ አሰቃቂ ድብደባ ያደረጉበት መሆኑን ገልጾልኛል።” በማለት ምስክርነቱን ሰጥቷል።በማያያዝም፤ “ሃሳብን በነጻነት በመግለጻቸው፤ ብዙ ግፍ ከተሰራባቸው የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች መካከል አንዱነበር።” በማለት አቶ ክፍሌ ሙላት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል።
ሌሎች በስደት ላይ የሚገኙ የቀድሞ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች፤ አቶ አበራ ወጊ በኢትዮጵያ ነጻፕሬስ ታሪክ ውስጥ ያበረከተውን መስዋዕትነት በማክበር፤ “ስምህ ከመቃብር በላይ ይኖራል” ለማለት፤ ይህንወቅታዊ መግለጫ አውጥተናል። ለወዳጅ እና ዘመዶቹ አምላክ መጽናናትን ይሰጥልን ዘንድ እንማጸናለን።
በህይወት በነበረበት ወቅት ራሱ ጋዜጠኛ አበራ እንዳለው… “ኢትዮጵያዊነት የቃል ኪዳን ማተማችንነው”!
በስደት የሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች።
Average Rating