By Zelalem Gebre
የአፍሪካ ህብረት ወደ አሜሪካ ለሚጓዙ አፍሪካውያን ዜጎች እና ባለስልጣናቶች በአሜሪካ ጉዳይ ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
ተቀማጭነቱን በአዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት ድርጅት በሰሜን አሜሪካ በፖሊሶች እና በጥቁር አሜሪካውያን ላይ በሚፈጸመው ግድያን አስመልክቶ በሰፊው በሃገሪቱ ላይ እየተዛመተ ነውእና በየትኛውም አቅጣጫ ስትጓዙ ጥንቃቄ ይገባችኋል ሲል ሃተታውን ጀምሮአል ።
ቁጥራቸው በዛ ያሉ የጦር መሳሪያ ያልያዙ ጥቁር አሜሪካኖችን ግድያ በየእለቱ እየተሰፋፋ ከመምጣቱም በላይ ለህዝቡ ሃይል እና ቦታ ሊሰጠው እንደሚገባ ፣እረፍትም ኣሜሪካ ፖሊስ ሊሰጣቸው እንደሚገባ በማተት በቻርሎቴ (ሰሜናዊ ካሎራይና) ውስካንስን (ሚልዋኪ) ዳላስ ቴክሳስ እና ታላላቅ ከተሞች እና ስቴቶች እየተፈጸመ ያለው ግድያ ውጤቱ እየተዛመተ ስለሆነ ተጓዦች ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸውል ሲሉ አትተዋል
የአፍሪካ ህብርት በጣም የተወሰነ የአደጋ ጊዜ የሚሆን አገልግሎት በአሜሪካ የሚሰጠው አገልግሎት በጣም ጥቂት በመሆኑ ተጓዦች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል መጭውም የአሜሪካ ፕረዚዳንታዊ ምርጫ የሚካሄድበት ወቅት በመሆኑ አሜሪካ ከፍተኛ ዝግጅት እና ትኩረት እያደረገች ስለሚሆን አሁንም የአድን ወራት ያህል የቀረው የፕረዚዳንታዊው ምርጫ እስኪጠናቀቅ የአፍሪካ አምባሳደሮች ጉዞአቸው ጥንቃቄ የተሞላበት ይሁን ሲሉ አትተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህ ተቀማጭነቱን በአዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት በሃገሪቱ ኢትዮጵያ ላይ ወያኔ መንግስት የሚፈጸመውን አሰቃቂ ግፋዊ ጥቃት ግን ከምንም ሳይቆጥረው ከ6 ወር አንድ ጊዜ በሚደረግ በጥቁር እና ነጭ የግድያ ሁኔታ ላይ ትኩረቱን ስቦታል ።
በቢሾፍቱ በአንድ ቀን ውስጥ ከ750 በላይ ንጹሃን ዜጎች በጥይት ፣ገደል በመግባት እና ብቢሾፍቱ ወንዝ በመስጠም የሚታወቅ ሲሆን በመላው አለም መገናኛ ብዙሃን ትኩረትም እንደሳበ ግልጽ ነው ።
ሆኖም ለአፍሪካውያኖች ቆሜአለሁ የሚለው የአፍሪካ ህብረት በአፍሪካ ህዝብም ሆነ በኢትዮጵያን ዜጎች ላይ የማላገጥ ስራ እንደሰራ ያሳያል ።
671
Average Rating