የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለገዥው መንግስት እንደልቡ የመግደል ፣ የመጨፍጨፍ እና የማሰር መብት ያጎናጽፋል፡፡ እስካሁን የነበረውን ጭፍጨፋ ህጋዊ ሽፋን ያጎናጽፈዋል፡፡ በህገ መንግስቱ መሰረት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲታወጅ ሃገሪቱ ከገዥው ቁጥጥር ውጭ ስትሆን ሲሆን መንግስት የህግ ቡድን አቋቁሞ እርምጃው ኢሰብአዊ መሆኑን ይቆጣጠራል፡፡የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኢሰብአዊ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ሰው በታሰረ በአንድ ወር ውስጥ ለቤተሰቡ እንዲታወቅ ይደረጋል ይላል፡፡ ጭፍጨፋው ህጋዊ ሽፋን ተሰጥቶት ህወሃት እድሜው ለማራዘም ንጹሃን መጨፍጨፉን አጠናክሮ የሚቀጥልበት አዋጅ ወጥቷል ፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ በፊትም በአጄ አካባቢ የተገደሉትን ወጣቶች ስም ዝርዝር ይዘናል እንደሚከተለው ቀርቦአል ።
1, kilaashii sa’id
2, Tibbeessoo Aabbuu
3, Aabbuu waashoo
4, Shaashoo Duulaa
5, Milkeessoo Gammadii
6, maammiraa Hasana
7 Gammadoo Gammachuu
8 Nigusee Tusaa
9 Roobaa Waaree
10 Tukee maammaa
11Tashoomee Abdallaa
12 Tashoomee Badhaasoo
13 Abbattoo Shubbee
14 Destaa Tattagaa
15Nuuraa Quufaa
16 Saaddoo Arsee ባለፈው ሃሙስ መአጋዚ ጦር የተገደሉትን እንዚህን ወጣቶች መሰዋእትነት ወደ ሌላ ነገር ጥለን በጊዜአዊ የአደጋ ጥሪው ላይ ትኩረት አናደርግም፣ትኩረታችን ወያኔን ከስልጣን ማውረድ እና ኢትዮጵያ በፍትሃዊ አስተዳደር እንድትተዳደር ፍላጎታችን ነው ሲሉ በሃገር ውስጥ ያሉ ፣የንቅናቄው አካላት ገልጸዋል ።
በአወዳይ እየተደረገ ያለው ጦርነት የዚሁ አካል መሆኑንም ጠቁመዋል፣በምእራብ ሸዋ ሃረርጌ እና ድሬዳዋ፣ እንዲሁም በጉጂ ዞን በጌድዮ አካባቢ ያለው ይሄው የሃገራዊ ነውጥ መቼም ቢሆን ህዝብን አንድ የሚያደርግ እንጂ የሚከፋፍል አይደለም ሲሉ አክለው ገልጠዋል ።
Average Rating