በትላንትናው ዘገባችን መሰረት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ወረታው ዋሴ ስለሺ ፈይሳ ወይንሸት ሞላ እና ብሌን ታስረዋል ብለን መዘገባችን ይታወሳል ሆኖም ግን ፣ዛሬ በተላከልን የይስተካከልልን መረጃ መሰረት የታሰሩትን ሰዎች ስም ዝርዝር አስተካክለን ስናቀርብ ላደረግነው ስህተት በአክብሮት ይቅርታ እንጠይቃለን ።
የሰማያዊ ፓርቲ አባላቶች ከታሰሩት መካከልም እያስፔድ ተስፋዬ ፣ብሌን መስፍን ፣እና አወቀ ተዘራ ፣ያለምንም መጥሪያ ከያሉበት በማፈን ወስደዋቸዋል፣ይህንንም የተደረገው በቅርቡ የታወጀውን አዋጅ አስመልክቶ መንግስት በሚፈልገው መልኩ ፣ያለመጥሪያ ሰዎችን ለምርመራ እፈልጋለሁ እያለ እንደሚያስር እና እንደሚያንገላታ ገልጸዋል ፣ይህም አዋጅ ለዚህ መንግስት አውጭነቱ ያሰጉኛል የሚላቸውን ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የድርጅት አባላቶችን በእስር በማስገባት ለማሽመድመድ እንዲቻለው ነው ሲሉ ከሰማያዊ ፓርቲ የተላከልን አጭር የመልእት መግለጫ ያመለክታል ።
![blue party logo](https://i0.wp.com/www.maledatimes.com/wp-content/uploads/2013/09/blue-party.jpg?resize=211%2C239&ssl=1)
blue party logo
በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያየለ የመጣው የመንግስት አፈና እና እንቢተኝነት በህዝቡ ቆራጥ አቋም ፣ሊፈነዳ ባለ ወቅት መንግስት ፍርሃቱን ለማንገስም ሆነ ያለበትን ጭንቀት የሚተነፍስበት ሲያጣ በዜጎች ላይ ዱላ እንደሚያበዛ ይታወቃል ፣ይህንንም በምርጫ 97ም ሆነ ከዚያም በፊት እና በሁዋላ በነጻው ህዝብ ላይ የተደረገውን አፈና የምንዘነጋው አይደለም ሲሉ አክለው ገልጠዋል።
የማለዳ ታይምስ አዘጋጆች እና ዘሃበሻ በትላንትናው እለት ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን ።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating