www.maledatimes.com አገራቸውን ጥለው በፈረጠጡት በወያኔው ባለስልጣን አቶ ጌታቸው በላይ ላይ ህወሃት እርምጃ እወስዳለሁ ሲል ገለጸ…..መክዳታቸውንም አመነ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አገራቸውን ጥለው በፈረጠጡት በወያኔው ባለስልጣን አቶ ጌታቸው በላይ ላይ ህወሃት እርምጃ እወስዳለሁ ሲል ገለጸ…..መክዳታቸውንም አመነ

By   /   October 5, 2012  /   Comments Off on አገራቸውን ጥለው በፈረጠጡት በወያኔው ባለስልጣን አቶ ጌታቸው በላይ ላይ ህወሃት እርምጃ እወስዳለሁ ሲል ገለጸ…..መክዳታቸውንም አመነ

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 35 Second

የግል ተቋማት ሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው በላይ ከአገር እንደወጡ አለመመለሳቸውን ምንጮች ገለጹ፣ ኤጀንሲው በሥራ ገበታቸው ላይ በአጭር ቀን ውስጥ ካልተመለሱ ዕርምጃ እወስዳለሁ ብሏል፡፡

የቀድሞ የገቢዎች ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ጌታቸው በላይ፣ በመቀጠልም የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕውሓት) ኢንዶውመንት የሆነው ኤፈርት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ በመሆን እስከ ቅርብ ጊዜ አገልግለዋል፡፡ ከዓመት በፊት ደግሞ የግል ተቋማት ሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሾመው ነበር፡፡

በዚህ መሥሪያ ቤት ባደረጉት የአንድ ዓመት ቆይታ ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ከግል ተቋማት ሠራተኞች እንዲሰበሰብ ያደረጉ ሲሆን፣ ድርጅቱን በሚገባ በማዋቀርና በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ እንዲሆን በማድረግም ይታወቃሉ፡፡ ይሁን እንጂ ባልታወቀ ወይም ለጊዜው ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ልጆቻቸውንና ባለቤታቸውን ይዘው አሜሪካ መግባታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ፍሎሪዳ ውስጥ በመኖር ላይ እንደሚገኙ የሚናገሩት የቅርብ ምንጮች፣ ከዚህ በኋላ ወደ አገር ቤት በመመለስ በሥራ ገበታቸው ላይ የመገኘት ፍላጎት እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡

የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ውቤ፣ ‹‹የማውቀው በእረፍት ላይ መሆናቸውን ነው›› ብለዋል፡፡

አቶ ጌታቸው የወሰዱት የዓመት እረፍታቸውን ሲሆን የተሰጣቸው የእረፍት ጊዜ ከተጠናቀቅ ከወር በላይ ሆኖታል፡፡ ይሁን እንጂ ከድርጅቱ ኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ወይም ወደ ሥራ ገበታቸው ያልተመለሱበት ምክንያት እስካሁን አለመግለጻቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡

‹‹እስካሁን ወደ ሥራ ገበታቸው ያልተመለሱበት ምክንያት ግልጽ ባይሆንም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይመለሳሉ ብለን እናምናለን፡፡ ይህ ካልሆነ ግን አስፈላጊውን አስተዳደራዊ ዕርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን፤›› ሲሉ አቶ ደረጀ ገልጸዋል፡፡

ኤጀንሲው ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም ከጽሕፈት ቤታቸው ለኤጀንሲው የተላከ ነገር እንደሌለ አቶ ደረጀ ተናግረዋል፡፡

አቶ ጌታቸው በላይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ሲያገኙ ከኦስትሪያ ቪዬና በስታትስቲክስና በኢኮኖሚክስ የማስትሬት ዲግሪያቸውን ይዘዋል፡፡

ላለፉት 16 ዓመታትም በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በማገልገል ልምድ ሲያካብቱ፣ ለአምስት ዓመታት የገቢዎች ሚኒስትር በመሆን ሠርተዋል፡፡

በምኒልክ ሳልሳዊ 

 

 

 

ማሳሰቢያ፤በዌብሳይታችን ላይ ለሚወጡ ማናቸውም ጽሁፎች ቀዳሚ የሆነ የዌብሳይታችንን አርትኦት ስራን ለማክበር ሲባል በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በማለዳ ታይምስ የመረጃ ማእከል ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የማለዳ ታይምስ የመረጃ ማእከል ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዌብሳይቱን ጠቋሚ (አመልካች ) (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.maledatimes.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን(የማለዳ ታይምስ ህግና ደንብ በንግድ በተመዘገቡበት ሁለት አገሮች የረቀቀ ሲሆን በሁለቱም አገሮች አንድ አይነት የሆነ አሰራር ይዞ ይከተላል ።ይህንን ህግ ማንኛውም ሰው መቅዳት የማይችል መሆኑን እንገልጻለን።ንብረትነቱ እና ህገ ደንቡ የማለዳ ታይምስ ብቻ ነው!)፡፡ይህ ካልሆነ ግን በህገ ደንባችን መሰረት አስፈላጊውን የህጋዊ ጥያቄ ለማቅረብ የምንገደድ መሆኑን እንጠቁማለን::በዚህ አጋጣሚ በግለሰብ ለሚላኩ ጽሁፎች ሁሉ ተጠያቂው ስሙ የተገለጸው ግለሰብ እንጂ የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ሃላፊነቱን እንደማይወስድ እናሳስባለን ::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 5, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 5, 2012 @ 2:14 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar