www.maledatimes.com መንግሥት ሃይማኖታዊ መልዕክቶችን የሚከለክል ሕግ ሊያወጣ ነው:: ዝርዝር ይዘት ያለው ረቂቅ ሕግ ተዘጋጅቶ እየተጠና ነው :: - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

መንግሥት ሃይማኖታዊ መልዕክቶችን የሚከለክል ሕግ ሊያወጣ ነው:: ዝርዝር ይዘት ያለው ረቂቅ ሕግ ተዘጋጅቶ እየተጠና ነው ::

By   /   October 5, 2012  /   Comments Off on መንግሥት ሃይማኖታዊ መልዕክቶችን የሚከለክል ሕግ ሊያወጣ ነው:: ዝርዝር ይዘት ያለው ረቂቅ ሕግ ተዘጋጅቶ እየተጠና ነው ::

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 23 Second

በአገሪቱ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፉና ሃይማኖታዊ ግጭቶችን እየፈጠሩ ነው የሚባሉ ማናቸውም ሃይማኖታዊ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ ምስሎች፣ ጥቅሶች፣ ድምፅን የሚበክሉ የጐዳና ላይ ስብከቶችና መዝሙሮች፣ ከሕዝባዊ ቦታዎች የሚከለክል አዲስ ሕግ አውጥቶ በሥራ ላይ ለማዋል እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መንግሥት አስታወቀ፡፡ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች የሚመለከቱት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ሃይማኖት ጥልቅና ጥንቃቄ የሚያሻው ጉዳይ በመሆኑ፣ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጥልቀት እየመረመረው መሆኑንም ገልጿል፡፡

በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አበበ ወርቁ በተለይ እንደገለጹት፣ መንግሥት በአሁኑ ጊዜ ሃይማኖታዊ መልዕክት ያላቸውን ይዘቶች በተመለከተ፣ የአምልኮ ሥርዓት ምን መምሰል እንዳለበትና የድምፅ ብክለትን ጨምሮ የሚፈጠሩ ችግሮችን ከሕዝባዊ ቦታ እንዴት ማራቅ እንደሚቻል፣ ሕግ እንደሚያስፈልግ ከምንጊዜውም በላይ እያሰበበትና እየተዘጋጀ ነው፡፡

“በማናቸውም አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንደ ታክሲ፣ ሆቴሎች፣ ሕዝባዊ ተቋማትና አደባባዮች ላይ የሚለጠፉ ሃይማኖታዊ ነክ መልዕክቶችን፣ ሕዝብን ከሕዝብ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ሊያጋጩ የሚችሉ በኤሌክትሮኒክስ የሚተላለፉ መልዕክቶች በሙሉ በሕግ ተደንግገው የሚከለከሉበት ሥራ በመሠራት ላይ ነው፤” ብለዋል አቶ አበበ፡፡

“የሃይማኖት ጉዳይ ጠለቅ ያለ ነገር ስለሆነ ጠለቅ ያለ ሕግና ደንብ ያስፈልገዋል፡፡ ስለሆነም የአዋጁንና የደንቡን ይዘት እያዘጋጀን ለሚመለከታቸው አካላት እያሳየን ነው፡፡ የድምፅ ብክለትን በተመለከተ አዋጁና ደንቡ በማውጣት ሥርዓት ለማስያዝ እየተሠራ ነው፤” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

“ለምሳሌ ታክሲዎችንና ሆቴሎችን ብናይ የሕዝብ ተቋማት እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ አገልግሎታቸውም ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች መሆኑ እየታወቀ በውስጣቸው የአንድን ሃይማኖት ፍላጐት ብቻ የሚያንፀባርቁ መልዕክቶች ይተላለፍባቸዋል፡፡ እነዚህ አገልግሎቶች የሕዝብ መጠቀሚያ እንጂ የማንም ሃይማኖት ተከታይ መጠቀሚያ ብቻ መሆን የለባቸውም፡፡ በእነዚህ ቦታዎች የሚለጠፉ መልዕክቶች የአንዱን ሃይማኖት ከፍ አድርገው የሌላውን ማንኳሰስ የሚታይባቸው ነው፡፡ በመሆኑም ከፈቃድ አሰጣጥ ጀምሮ ሕዝብን ከሕዝብ ሊያጋጩ በማይችል ሁኔታ አገልግሎት እንደሚሰጡ መታሰብ አለበት፤” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በምንሊክ ሳልሳዊ 

 

ማሳሰቢያ፤በዌብሳይታችን ላይ ለሚወጡ ማናቸውም ጽሁፎች ቀዳሚ የሆነ የዌብሳይታችንን አርትኦት ስራን ለማክበር ሲባል በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በማለዳ ታይምስ የመረጃ ማእከል ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የማለዳ ታይምስ የመረጃ ማእከል ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዌብሳይቱን ጠቋሚ (አመልካች ) (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.maledatimes.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን(የማለዳ ታይምስ ህግና ደንብ በንግድ በተመዘገቡበት ሁለት አገሮች የረቀቀ ሲሆን በሁለቱም አገሮች አንድ አይነት የሆነ አሰራር ይዞ ይከተላል ።ይህንን ህግ ማንኛውም ሰው መቅዳት የማይችል መሆኑን እንገልጻለን።ንብረትነቱ እና ህገ ደንቡ የማለዳ ታይምስ ብቻ ነው!)፡፡ይህ ካልሆነ ግን በህገ ደንባችን መሰረት አስፈላጊውን የህጋዊ ጥያቄ ለማቅረብ የምንገደድ መሆኑን እንጠቁማለን::በዚህ አጋጣሚ በግለሰብ ለሚላኩ ጽሁፎች ሁሉ ተጠያቂው ስሙ የተገለጸው ግለሰብ እንጂ የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ሃላፊነቱን እንደማይወስድ እናሳስባለን ::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 5, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 5, 2012 @ 2:24 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar