www.maledatimes.com የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር ከመልስ ይልቅ ጥያቄ ይበዛዋል። ቴዎድሮስ ዳኜ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር ከመልስ ይልቅ ጥያቄ ይበዛዋል። ቴዎድሮስ ዳኜ

By   /   October 16, 2016  /   Comments Off on የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር ከመልስ ይልቅ ጥያቄ ይበዛዋል። ቴዎድሮስ ዳኜ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 19 Second

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር ከመልስ ይልቅ ጥያቄ ይበዛዋል። አብዛኞቹ “ክልክል”የተባሉት ነገሮች ድሮም ክልክል ናቸው። የቀረው ነገር ተጨማሪ ማብራሪያ ካልተሰጠበት ትልቅ ውዥንብር መፍጠሩ አይቀርም። ድሮም ክልክል ከነበሩትና ከሚያከራክሩት ነገሮች ውስጥ

አንዳንድ ምሳሌ፦
አንቀፅ 10. ሀይማኖታዊ፣ ባህላዊና ህዝባዊ በዓላት ላይ ቅስቀሳ ማድረግ
ሀይማኖታዊ ተቋማት ውስጥ በሚደረጉ ስብከቶችና ትምህርቶች ሀይማኖታዊ አስተምህሮት ከማድረግ ውጪ በህዝቦች መካከል መጠራጠርና መቃቃርን የሚፈጥር፣ በህብረተሰቡ ላይ ስጋት የሚፈጥር፣ ሁከትና ብጥብጥ የሚቀሰቅስ ቅስቀሳ ማድረግ የተከለከለ ነው።
– ይህ ውዥንብር ይፈጥራል .. ለመሆኑ “አገራችን አሁን ያለችበት ሁኔታ አስጊ ነው፣ ጸሎት ያስፈልገናል” ብሎ በመንፈሳዊ ትምህርት መካከል መናገር በህብረተሰቡ ላይ ስጋት ይፈጥራል ተብሎ ይወሰዳል?
___________
አንቀፅ 8.በመሰረተ ልማቶችና ሃይማኖታዊ ተቋማት ላይ ጉዳት ማድረስ
በግል ፣ በህዝብና በመንግስት ማናቸውም ተቋማት፣ በመሰረተ ልማት፣ በኢንቨስትመንትና በሌሎች የልማት አውታሮች እንዲሁም በሃይማኖታዊ ተቋማት ላይ በማንኛውም መንገድ ጉዳት ማድረስ ወይም ዘረፋ መፈፀም የተከለከለ ነው።
– ይህ ድሮስ ይፈቀድ ነበር እንዴ? እንዲህ ዓይነት ድሮም የማይፈቀዱ (በህገመንግስቱም ይሁን በወንጀል ህጉ የተከለከሉ) ብዙ ነገሮች እዚህ አዋጅ ውስጥም ገብተዋል። ምን የተለየ ነገር ይዘዋል?
___________
ይህኛው ደግሞ በጣም አደገኛ ነው።
አንቀፅ 22. በልማት አውታሮችና መሰረተ ልማቶች ላይ የሚሰነዘር ጥቃት
የኢኮኖሚ አውታሮች፣ መሰረት ልማትና የኢንቨስትመንት ተቋማት፣ የእርሻ ልማቶች፣ በፋብሪካዎች እና በመሰል ተቋማት አካባቢ ከቀኑ 12 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋት 12 ሰአት ድረስ ከተፈቀደለት ሰራተኛ በስተቀር ማንኛውም ሌላ ሰው መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፣
ከላይ በተመለከቱት ቦታዎች የሰዓት እላፊውን ተላልፎ በተገኘ ማንኛውም ሰው ላይ የጥበቃ ውይንም የህግ አስከባሪ አካላት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።
>>= አብዛኛው ህዝብ እግረኛ በሆነበት አገር፣ የመኖሪያና የመስሪያ ቤት ሰፈሮች ድሮውኑም ተለይተው የተሰሩ ይመስል፣ ማንም ሰው ከፋብሪካ አጠገብ፣ ከመንግስት መስሪያ ቤት አጠገብ፣ ከአንድ ንግድ ተቋም (ኢንቨስትመንት ተቋም) አጠገብ ቤቱ ሊሆን እንደሚችል ግልጽ ነው። ማንም ሰው በአንድ ፋብሪካ ወይም ከተጠቀሱት በአንዱ በኩል ሳያልፍ ቤቱ አይደርስም። አንድ ፋብሪካ አጥር ጥግ ላስቲክ ወጥረው የሚኖሩም አይጠፉም። እና ማታ ላይ ተፍ ተፍ እያለ ቤቱ የሚገባ ሁሉ ሊተኮስበት ነው? ከዚህ ይልቅ አንደኛውን ሙሉ የሰአት እላፊ ሳይሻል አይቀርም።
___________
ይህኛውስ ምን ማለት ነው?
አንቀፅ 2. ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ማድረግ
በሽብር ከተሰየሙ ድርጅቶች እና ከፀረ ሰላም ቡድኖች ጋር ማናቸውንም ግንኙነት ማድረግ፣
የአሽባሪ ድርጅቶችን የተለያዩ ፅሁፎች መያዝ ማሰራጨት፣ አርማቸውን መያዝ ወይም ማስተዋወቅ፣
የቴሌቪዥን ወይም የሬድዮ ፕሮግራምን መከታተል፣ የኢሳት፣ የኦ.ኤም.ኤን. እና የመሳሰሉትን የሽብርተኛ ድርጅቶች ሚዲያዎችን ማሳየት፣ መከታተልና ሪፖርት ማድረግ የተከለከለ ነው።
– እነዚህ “የመሳሰሉት” ሚዲያዎች እነማን ናቸው? እገሌ ይህን ይሰማል፣ እገሊት እንትንን ከፍታለች እየተባለ አገር ሊታመስ ነው ማለት ነው።
______________
አንቀፅ 6. በስፖርት ማዘውተሪያዎች አድማ ማድረግ
በስፖርት ማዘውተሪያ ማእከላት ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ የሆኑ ሁከቶችን፣ ብጥብጦችን መፍጠር የተከለከለ ነው።
– ዳኛው በአድልዎ ፍጹም ቅጣት ምት ቢሰጥና የዚያ ቡድን ደጋፊዎች በብስጭት ረብሻ ቢፈጥሩ፣ ይህን ህግ ተላለፉ ማለት ነው?
_____________
አንቀፅ 16. የሀገርን ሉዓላዊነት፣ ደህንነት፣ ህገመንግስታዊ ስርዓት የሚጎዳ ተግባር መፈፀም
ማንኛውም ሰው ከውጭ መንግስታትም ሆነ ከውጭ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሀገር ሉአላዊነት፣ ደህንነትና ህገ-መንግስታዊ ስርዓትን ሊጎዳ የሚችል ግንኙነትና የመልዕክት ልውውጥ ማድረግ የተከለከለ ነው፣
ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የሀገርን ዑአላዊነት፣ ደህንነት እና ህገመንግስታዊ ሥርዓቱን ማናቸውም ጋዜጣዊ መግለጫ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሚዲያዎች መስጠት ክልክል ነው።
– የፖሊቲካ ድርጅቶች አባሎቻችን ታሰሩ ወይም ተገደሉ ብለው ጋዜጣዊ መግለጫ ቢሰጡ ይህን ህግ ጣሱ ማለት ነው?

ሰላሳውን አንቀጽ በማብራራት ብቻ ስድስት ወሩ የሚያልቅ ይመስለኛል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on October 16, 2016
  • By:
  • Last Modified: October 16, 2016 @ 11:41 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar