www.maledatimes.com ‹‹ነጋዴዎች ስንባል ቀጣፊዎች ነን፡፡ ይህ ባህሪ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ያለ አይደለም፤መንግሥት አንዳንዴ ዓይኑን ቢጨፍንልን ጥሩ ነው፤›› ሼክ አል አሙዲ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

‹‹ነጋዴዎች ስንባል ቀጣፊዎች ነን፡፡ ይህ ባህሪ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ያለ አይደለም፤መንግሥት አንዳንዴ ዓይኑን ቢጨፍንልን ጥሩ ነው፤›› ሼክ አል አሙዲ

By   /   October 5, 2012  /   Comments Off on ‹‹ነጋዴዎች ስንባል ቀጣፊዎች ነን፡፡ ይህ ባህሪ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ያለ አይደለም፤መንግሥት አንዳንዴ ዓይኑን ቢጨፍንልን ጥሩ ነው፤›› ሼክ አል አሙዲ

    Print       Email
0 0
Read Time:11 Minute, 2 Second

ሼህ መሃመድ አላሙዲ በከፍተኛ ደረጃ ቀረጥ በመጠየቃቸው ሕወሃት ላይ ጥርስ ነክሰዋል:; ሁለመናቸውን ወድ ብኣዲን በመገልበጥ አዲስ የቢዝነስ ስልት ፈጥረዋል ::•    ነጋዴዎች ስንባል ቀጣፊዎች ነን•    መንግሥት ዓይኑን ቢጨፍንልን ጥሩ ነው

•    መንግሥትን የንግዱን ነገር ለእኛ ይተውልን
ሼክ መሐመድ አል አሙዲ በኢትዮጵያ ውስጥ መዋለ ነዋያቸውን ካፈሰሱባቸው ፕሮጀክቶች ትልቁ ያሉትን የጦሳ ብረታ ብረት ፋብሪካ ገንብቶ ለማስረከብ ከመረጡት የጣሊያን ኩባንያ ጋር ለመፈራረም ባሰናዱት ዝግጅት ላይ፣ በቅርቡ የተሾሙትን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ በርካታ ባለሥልጣናት የተገኙ ሲሆን፣ መንግሥት ለንግዱ ኅብረተሰብ ማድረግ የሚጠበቅበትንና የንግዱ ኅብረተሰብ ከመንግሥት የሚጠብቀው ነው ያሉትንም አዋዝተው ተናግረዋል፡፡
የጦሳ ብረታ ብረት ፋብሪካን ለመገንባት የጀርመን፣ የብራዚልና የቻይና ኩባንያዎች መወዳደራቸውን በንግግራቸው መጀመርያ ላይ የገለጹት ባለሀብቱ፣ የጣሊያኑ ኩባንያ በቻይና ዋጋ የአውሮፓ ቴክኖሎጂን ይዞ በመቅረቡ 13.7 ቢሊዮን ብር የሚፈጀውን ፋብሪካ ሙሉ ለሙሉ ገንብቶ ቁልፉን እንዲያስረክብ መምረጣቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

‹‹ወደ ፀጉር አስተካካይ ከመሄድህ በፊት መቀስ አያያዙን እየው፤›› የሚለውን የዓረቦች አባባል የጠቀሱት ሼክ አል አሙዲ፣ የጣሊያኑ ኩባንያን የመረጡበት ምክንያትም አያያዙ ስላማራቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ቀጠል አድርገው የተናገሩት ግን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና በትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን መሪነት ሥነ ሥርዓቱን ለመከታተል ለተገኙ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን የሚመለከት ይመስላል፡፡ ከባለሥልጣናቱ መካከል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን፣ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አቶ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስትር አቶ መኩሪያ ኃይሌ፣ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው ጐበዜ፣ አቶ አዲሱ ለገሰ፣ አቶ ስብሐት ነጋና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡

‹‹የመለስ ዓላማና ዕቅድ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ መለስ መንገዱን ጠርጐልናል ከእኛ የሚጠበቀው መሮጥ ብቻ ነው፤›› ያሉት ሼክ አል አሙዲ፣ ከመለስ ሕልፈት በኋላ የተፈጠረውን ክፍተት በሰላማዊ መንገድ መሙላት በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታም ገልጸዋል፡፡ ‹‹ጀግኖች ናችሁ፡፡ ቃሉን ያከበረ ድርጅት ወደኋላ የማይል ነው፡፡ መሪ መፍጠር የሚችል ነው፤›› ሲሉ ኢሕአዴግን አሞካሽተዋል፡፡

በመቀጠል የተናገሩት በቅርብ ቀናት ሊተገብሩ ስላሰቧቸው ፕሮጀክቶች ሲሆን፣ ቀጠል አድርገው የተናገሩት ግን ፖለቲካዊ ትርጉሙ አመዝኖ የታየ ይመስላል፡፡ ‹‹ነጋዴዎች ስንባል ቀጣፊዎች ነን፡፡ ይህ ባህሪ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ያለ አይደለም፤›› ያሉት ሼክ አል አሙዲ፣ ‹‹መንግሥት አንዳንዴ ዓይኑን ቢጨፍንልን ጥሩ ነው፤›› በማለት ቀልድ መሰል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በባህር ዳር ከተማ ለማስገንባት ያሰቡትን የዘይት ፋብሪካ ከአሥር ቀናት በኋላ ከተመረጠው የእንግሊዝ አገር ኩባንያ ጋር እንደሚፈራረሙ፣ የጂንስ ፋብሪካና የኤሌክትሪክ ገመዶች (ኬብሎች) ፋብሪካን ለማቋቋም በጥረት ላይ እንደሆኑም ጨምረው አስረድተዋል፡፡

‹‹መንግሥትን የምለምነው የንግዱን ነገር ለእኛ እንዲተውልን ነው፤›› በማለት መንግሥት በንግዱ እንዳይፎካከር በመጠየቅ፣ በመሠረተ ልማት ግንባታ፣ ሰላምና ፀጥታ በማስከረበር ላይ ቢበረታ መልካም ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የጦሳ ብረታ ብረት ፋብሪካን ለመገንባት የተመረጠው ዳኔኤሊ የተባለው የጣሊያን ኩባንያ ሲሆን፣ ፋብሪካውን ለመገንባት 36 ወራትና 764 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም 13.7 ቢሊዮን ብር ይፈጃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ 1.35 ሚሊዮን ቶን መጠን ያላቸው የተለያዩ ብረቶችን በዓመት ያመርታል ተብሎ ሲጠበቅ፣ ይህንን ለማምረት 16,800 ኪዩቢክ ሜትር ውኃ በሰዓት በፋብሪካው ማሽነሪዎች ውስጥ መተላለፍ ያለበት ሲሆን፣ 260 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትም መሠረታዊ ፍላጐቱ ነው፡፡

 

 

 

ማሳሰቢያ፤በዌብሳይታችን ላይ ለሚወጡ ማናቸውም ጽሁፎች ቀዳሚ የሆነ የዌብሳይታችንን አርትኦት ስራን ለማክበር ሲባል በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በማለዳ ታይምስ የመረጃ ማእከል ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የማለዳ ታይምስ የመረጃ ማእከል ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዌብሳይቱን  ጠቋሚ (አመልካች ) (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.maledatimes.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን(የማለዳ ታይምስ ህግና ደንብ በንግድ በተመዘገቡበት ሁለት አገሮች የረቀቀ ሲሆን በሁለቱም አገሮች አንድ አይነት የሆነ አሰራር ይዞ ይከተላል ።ይህንን ህግ ማንኛውም ሰው መቅዳት የማይችል መሆኑን እንገልጻለን።ንብረትነቱ እና ህገ ደንቡ የማለዳ ታይምስ ብቻ ነው!)፡፡ይህ ካልሆነ ግን በህገ ደንባችን መሰረት አስፈላጊውን የህጋዊ ጥያቄ ለማቅረብ የምንገደድ መሆኑን እንጠቁማለን::በዚህ አጋጣሚ በግለሰብ ለሚላኩ ጽሁፎች ሁሉ ተጠያቂው ስሙ የተገለጸው ግለሰብ እንጂ የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ሃላፊነቱን እንደማይወስድ እናሳስባለን ::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 5, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 5, 2012 @ 2:44 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar