በትላንትናው እለት በችካጎ በተካሄደ የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት ላይ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ እና ኢሳትን ካሉበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ እና የመረጃ ፍሰታቸውን በሃገርቤት ላለው ህዝብ ለማዳረስ ጠንክረው በጋራ መስራት አለባቸው በሚል እሳቤ ከኦሮሞ ማህበረሰብ ተወካይ አንደበተ ርእቱ ዶ/ር አወል አልሎ እና ከእሳት አሮ ኤርምያስ ለገሰ የተገኙ ሲሆን ገቢው ለእሳት 6ኛ አመት ክብረ በአል እና ለኦምኒ እንዲሆን መላው በችካጎ ውስጥ የሚገኙት ኢትዮጵያኖች የወሰኑ ሲሆን ማህበረሰቡን ወክለው ዝግጅቱን ካዘጋጁት ውስጥ 10 ኮሚቴዎች መካከል በ9ኙ ውሳኔውን ሲያጸድቅ በአንድ ጽንፈኛ አመለካከት ባለው ግለሰብ ደግሞ ፣በየትኛውም ቦታ ኢትዮጵያን ከነጻነት አወጣለሁ ብሎ በዘመተ የመከላከያ ጦር ባለተገኘበት ሁኔታ ላይ ገንዘቡ ፣ለመከላከያ ሰራዊት መግባት አለበት በሚል ክርክር እና ለሚዲያዎች መቅረብ አለበት በሚለው ሃሳብ ላይ በሰፊ ልዩነት ገቢው መረጃ ለጠማው ህዝብ መረጃን ለሚያቀብሉ ሁለቱ ሚዲያዎች በማለት መወሰኑ ተገልጾአል።
በዚህም ጉዳይ ላይ ሽንፈት የገጠመው ይሄው ግለሰብ ህብረተሰብን ከሚያራርቁ እና አንድነታቸውን አጠናክረው ከሚሄዱ መንገዶች መሰናክልን በመፍጠር ከፍተኛ ጥላቻን በህብረተሰቡ ዘንድ እየዘራ ቢገኝም ማንኛውም ሰው ቦታ ሊሰጠው ያልቻለበት ሁኔታ እንዳለ ማህበረሰቡ ካለው አቋም ተገንዝቦታል።
በመልካም ስነ ምግባር የማይታወቅውን ይህ ግለሰብ ከዚህ ቀደምም ከማለዳ ታይምስ አዘጋጅ ጋር የነበረው አተካራ የነበረው ቢሆንም ማለዳ ታይምስ አዘጋጆች በለዘብተኝነት መተዋቸው ይታወሳል፣ሆኖም እጅ ለእጅ በሚል የግብረ ሰናይ ድርጅት ውስጥ በችካጎ የሚገኙ ወጣቶች ቢያቋቁሙትም በዚህ ግለሰብ እጅ በመውደቅ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ በደረሰ አደጋ $17.000 ወጣቶቹ አሰባስበው ለተጎዱ ወገኖች ቢልክም ከዚያም በሁዋላ በዚሁ ድርጅት ስር የተከናወኑ የሙዚቃ ዝግጅቶች የተሰበሰቡ ገንዘቦች ወዴት ተሰለቡ በሚል ፣አባላቶቹ ይህንን ግለሰብ በመኮነን እጅ ለእጅ የሚለውን የግብረሰናይ ድርጅት ለመበተን በቅተዋል ።
በሌላም በኩል ስለዚህ ግለሰብ አመለካከት ከማለዳታይምስ ለተጠየቀ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ ግለሰብ እንዳለው ለኢትዮጵያ አንድነትም ይሁን ለህዝብ ነጻእት ወይንም ሃገራዊ አንድነትን ያምናል ብለን አናምንም ሲሉ አብረው በግብረሰናይ ድርጅት ውስጥ የሰሩት ግለሰቦችም ሲኮንኑት ተደምጠዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቦታው የተገኙት ኢትዮጵያውያኖች አመዛኙን ኢትዮጵያ የሚል አላማ ያላቸው ሲሆን ማናቸውም በከፋፋይ አመለካከት እና ልዩነት ያልታየ ሲሆን በኦሮሞ ሚዲያ ተወካይም ይሁን በኢሳት ተወካይ በኩል ያለው ፣የኦሮሞውን ማንነት እና የአምራውን ማንነት የሚያንጸባርቅ አንድነት እና ልዩነቶችን አንስተዋል ፣በልዩነቶቹም ላይ አብረው በጋራ መስራት የሚገባቸውን ነገሮች መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ።
በወቅቱ የኢትዮጵያዊነት እና ኦሮሞኒዝም የሚሉት አንኳር ጥያቄዎች ፣የኢትዮጵያ ባንዲራ እና የኢትዮጵያ ባንዲራ ቀዳሚነት የብሄረሰብ ባንዲራ ምን እንደሆነ በልዩነት መረዳት እንዳለበት እና ፣ባንዲራ ሃገርን ሲወክል የብሄር ባንዲራ የመጣበትን ማንነቱን ሊጠቁም የሚችል ስለመሆኑ እና ስለ አመነበት አላማ በመከባበር በጋራ ማስኬድ እንደሚቻል እና ሁላችንም እምነቶቻችንን ከጥላቻ ይልቅ በመቻቻል ማሳለፍ እንዳለብን እና ልዩነቶቻችችንን በመራራቅ ሳይሆን በመቀራረብ እና በመወያየት መፍታት የምንችል መሆኑን ሳይገልጹ አላለፉም ።
በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ይሄ የአንድነት እና የመቻቻል ስራ ቀጥሎ በሌሎችም ስቴቶች የሚጉዋዝ መሆኑን እና በቀጣይም በሚንያፖሊስ የህብረብሄሮችን ያቀፈው ልዩ ፕሮግራም በቀጣይ እንደሚቀርብ እና ከጋምቤላ፣ኦሮሞ፣አማራ፣ ኦጋዴን ሶማሌ እና ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች የሚሳተፉበት የዚህ ፓናል ዲስከሽን ለውጥ ለማምጣት እንደሚችል የማለዳ ታይምስ ሲገልጽ ይህንን ሂደት የጋራ ድላችን አድርገን መሄድ አለብን ብለውም አዘጋጆቹ ያምናሉ ።
በተለያዩ መገናኛ ብዙሃኖች እየተናፈሰ ያለው የጎንዮሽ ጉዞ እና እንደ እነ ሄኖክ የሺ ጥላ አይነቶች ግራ ዘመም አመለካከት ያላቸው ግለሰቦች ከህዝብ ጥቅም ይልቅ የፖለቲካ ፍጆታቸውን ለግለሰብ በማዋል ፣የፖለቲካ መንገዱን አቅጣጫውን ለማሳት በፌስቡክ ያልተዘመረ መዝሙር ሲዘምሩ ታይተዋል ፣ይህ ደግሞ በማንኛውም ማህበረሰብ ላይ ድንጋጤን አይፈጥርም።
Average Rating