www.maledatimes.com የክቡር አርቲስት ተስፋዬ አበበ(ፋዘር) 72ኛ ዓመት የልደት ቀን በዓል በብሄራዊ ቲያትር አዳረሽ በልዩ ድምቀት ይከበራል። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የክቡር አርቲስት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) 72ኛ ዓመት የልደት ቀን በዓል በብሄራዊ ቲያትር አዳረሽ በልዩ ድምቀት ይከበራል።

By   /   October 5, 2012  /   Comments Off on የክቡር አርቲስት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) 72ኛ ዓመት የልደት ቀን በዓል በብሄራዊ ቲያትር አዳረሽ በልዩ ድምቀት ይከበራል።

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 48 Second
በኪነጥበብ ህይወት ውስጥ አያሌ የኪነ-ጥበብ ባለ ሙያዎችን በማፍራት እና ለዘመናት አንቱ የተባሉ ስመ ጥር የኪነጥበብ ስራዎችን በመስራት በማፍራት የሚታወቁት አቶ ተስፋዬ አበበ (ፋዘር ) 72 አመታቸውን ለማክበር በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ከባልደረባችን ገጣሚ ሜሮን አባተ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።ነገ ዕለተ ቅዳሜ ላለፉት 39 ዓመታት በርካታ የጥበብ ወዳጆችን ያለምንም ክፍያ በኪነት፣በትወና በድምጻዊነት እንዲሁም በተለያዩ ጥበብ ነክ ሙያዎች አሰልጥኖ ብቁ ባለሙያ በማድረግ የሚታወቀው የአርቲስት ተስፋዬ አበበ ኪነጥበባት በጎ አድራጎት ማህበር 39ኛ ዓመት ምስረታ በዓሉን እንዲሁም በርካታ አርቲስት ወጣቶችን በጽናት በማፍራት ላይ ያሉት የክቡር አርቲስት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) 72ኛ ዓመት የልደት ቀን በዓል በብሄራዊ ቲያትር አዳረሽ በልዩ ድምቀት ይከበራል። ከፍተኛ እውቅና ያላቸው ወዳጆቻቸው እና የኪነጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም በኪነጥብቡ ዙሪያ ትምህርትን በማስተማር ለቁምነገር ያበቋቸው ልጆቻቸው በሙሉ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።የአቶ ተስፋዬ አበበ ከቀድሞዎቹ ስራዎቻቸው መካከል በከፍተኛ የሚወደሱባቸው እና የሚታወሱባቸው ታሪካዊ የስነጽሁፍ ስራዎቻቸው እስካሁን ድረስ ሳይነጥፉ በክብር ስማቸውን በክብር ቦታ ላይ እንደያዙ የሚታወስ ሲሆን በተለይም የድርሰት ሥራዎች
  • የወሬ ፈላስፋ
  • አስራሁለት እብዶች በከተማ
  • ጸረ-መናፍስት
  • የንጋት ኮከብ
  • የጥቁር ድምጽ
  • ባሻ ዳምጤ
  • ቀይ ማጭድ
  • ታጋይ ሲፋለም
  • ቀዩ መነጽር

እንዚህን የመሳሰሉ ድርሰቶቻቸውን ከሰው ልብ እንደማይርቁ የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ሳይጠቁም አያልፍም። ለፋዘር ተስፋዬ አበበ እንኳን ለ72ኛ የልደት በአልዎ አደረሰዎት እያልን በ39 አመታት ያፈሯቸውን ፍሬዎች አሁንም በድጋሚ ልምልመው እንዲያዩዋቸው እድሜዎን ያርዝምልን እንላለን የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል።

አቶ ተስፋዬ አበበ በአሁኑ ሰአት ብዙ የልጅ ልጆችን ያፈሩ ሲሆን በከፍተኛ ደረጃ በኪነጥበብ ውስጥ ጠልቆ የሚታወቀው የአርቲስት ቴዎድሮስ ተስፋዬ አባት ናቸው ።

Meet Artist Tesfaye Abebe (Father) and Tewodros Tesfaye – Part 2

FenoteTbeb

 

Submitted by: www.maledatimes.com
ማሳሰቢያ፤በዌብሳይታችን ላይ ለሚወጡ ማናቸውም ጽሁፎች ቀዳሚ የሆነ የዌብሳይታችንን አርትኦት ስራን ለማክበር ሲባል በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በማለዳ ታይምስ የመረጃ ማእከል ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የማለዳ ታይምስ የመረጃ ማእከል ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዌብሳይቱን  ጠቋሚ (አመልካች ) (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.maledatimes.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን(የማለዳ ታይምስ ህግና ደንብ በንግድ በተመዘገቡበት ሁለት አገሮች የረቀቀ ሲሆን በሁለቱም አገሮች አንድ አይነት የሆነ አሰራር ይዞ ይከተላል ።ይህንን ህግ ማንኛውም ሰው መቅዳት የማይችል መሆኑን እንገልጻለን።ንብረትነቱ እና ህገ ደንቡ የማለዳ ታይምስ ብቻ ነው!)፡፡ይህ ካልሆነ ግን በህገ ደንባችን መሰረት አስፈላጊውን የህጋዊ ጥያቄ ለማቅረብ የምንገደድ መሆኑን እንጠቁማለን::በዚህ አጋጣሚ በግለሰብ ለሚላኩ ጽሁፎች ሁሉ ተጠያቂው ስሙ የተገለጸው ግለሰብ እንጂ የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ሃላፊነቱን እንደማይወስድ እናሳስባለን ::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar