www.maledatimes.com አንባቢያን ሆይ! እኳንም በድጋሚ ተገናኘን By Temesgen Desalegn - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አንባቢያን ሆይ! እኳንም በድጋሚ ተገናኘን By Temesgen Desalegn

By   /   October 6, 2012  /   Comments Off on አንባቢያን ሆይ! እኳንም በድጋሚ ተገናኘን By Temesgen Desalegn

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 29 Second

By Temesgen Desalegn
አንባቢያን ሆይ! እኳንም በድጋሚ ተገናኘን
ፍትህ መታተም ካቆመች ሶስት ወር አለፏታል፡፡ የተቋረጠውን ህትመት ለማስቀጠልም ለወራት ጣርን ግና ‹‹ፍትህ ጋዜጣ›› በሚል ለመመለስ ዛሬም ድረስ አልቻልንም፤ ጥርታችን ነገም ይቀጥላል፤ በዚህ መካከል የተላያዩ አመራጮችን ስናፈላልግ ስለነበረ አራት ጊዜ ታትሞ የተቋረጠ ‹‹አዲስ ታይምስ›› የተሰኘ መፅሄት አገኘን፣ ከተደጋጋሚ ድርድር በኋላ መፅሄቱ በፍትህ አሳታሚ ስር ይጠቃለል ዘንድ ከመግባባት ላይ ደረስን፤ እነሆም በዛሬው ዕለት መፅሄቷ ሁሉንም የፍትህ ባልደረቦች እና ተጋባዥ ፃሃፊዎች (ተወዳጁን ያሬድ ጥበቡን እና ፕሮፈሰር ጌታቸው ኃይሌን) አካታ በድፍን ኢትዮጵያ ተበትናለች ፡፡
የመፅሄቷ ርዕሰ አንቀፅ ‹‹ተመልሰናል!›› ይላል፤ ከርዕሰ አንቀፁ ላይ ጥቂት ልጭልፍላችሁ፡-
….ከመጽሔት ስያሜነት እና ከቅርፅ ውጪ አንባቢዎች በዚህች መጽሔት እና በተወዳጇ ፍትህ ጋዜጣ መሀከል አንዳችም ልዩነት እንደሌለ እንደሚገነዘቡ እናምናለን፡፡ በፍትህ ጋዜጣ የምትከታተሏቸው ፀሐፊዎችም ሆኑ የየፀሐፊዎቹ ሙግቶች ከዚህ ዕትም ጀምሮ በአዲስ ታይምስ መጽሔት በኩል ታገኛችኋላችሁ፡፡ እናም በዚህች መጽሔት ላይ እንደሁልጊዜውም ለሀገራችን እና ለህዝባችን ይጠቀማሉ ብለን በምናምናቸው ጉዳዮች ላይ ካለአንዳች ፍርሃትና ማንገራገር መፃፋችንን እንቀጥላለን፡፡ ካለአንዳች ፍርሃትና ማንገራገር መረጃዎችን እናስተላልፋለን፡፡
‹‹ፍትህ ጋዜጣ›› መስዕዋት የሆነችውም ያለፍራቻ በዘገበችው ዜና መሆኑም ይታወቃል፡ ፡ ምንአልባትም ዜናን አማርጦ የመስራት ወይም የሚደፈርና የማይደፈር ጉዳይን ለይትን መስራት ብንመርጥ ኖሮ ‹‹ፍትህ››ን የሚያህል ዋጋ አንከፍልም ነበር፡፡ ፍትህንም በዚህ መልኩ አናጣትም ነበር፡፡ ሆኖም ደጋግመን እንፅፍ እንደነበረው ምንግዜም የምንቆመው ከእውነት እና ከህዝብ ጋር ነውና በዛን አስቸጋሪ ወቅት፣ ሚዲያው በተፈተነበት ወቅት ያለአንዳች
መወላወል ቃላችንንአክብረን አቋማችንን አሳይተናል፡፡ እናም ምንም እንኳ የተነጠቅንው ህልማችንን ቢሆንም፣ ምንም እንኳ የከፈልነው ዋጋ የመረረ ቢሆንም ለቃላችን እና ለእውነት መገዛታችን ዛሬ አንገታችንን እንዳንሰብር አድርጎናል፡፡
በወቅቱ ለፍትህ መታገድ ምክንያት የነበረው ዜና ከአንድ ወር በኋላ በራሱ ፍትህን በአፈነው ኋይል ይፋ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በእነዛ ወሳኝ ቀናት፣ በእነዛ የፈተና ቀናት፣ በእነዛ የቁርጥ ቀን ህዝብን የሚያሳስት መረጃ ሲያስተላልፉ የነበሩ ጋዜጦች ዛሬ አንገታቸውን ሰብረው ይቅርታ እየጠየቁ ነው፤ ይቅርታ ያልጠየቁት ደግም ይቅርታ ይጠይቁ ዘንድ ግዴታቸው ነውና እንጠብቃለን፡፡ ይቅርታ የጠየቁትንም ከዚህ በኋላ ይህን
ስህተት አይደግሙ በሚል ቀናነት የይቅርታ ቃላቸው ዋጋ ያገኝ ዘንድ ምኞታችን ነው፡፡ የፍትህን የእውነት መንገድ ይከተሉ ዘንድ፣ የፍትህን አርዕያ ይከተሉም ዘንድ እንምኛለን፡፡
(አዲስ ታይምስን በፍትህ ድረ-ገፅ www.fetehe.com መከታተል ይችላሉ)
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 6, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 6, 2012 @ 9:22 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar