በኖርዝ ኢስተርን ኢልኖይስ ዮኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጥናት እና ምርምርም ተቋም ውስጥ በተካሄደው የአፍሪካ መሪዎች የዝር ጅምላ ግድያን አስመልክቶ በተለያዩ አፍሪካ አገራቶኦች እንዴት ዘርን ያመላከተ የጅምላ ግድያ እንደ ተከናወነ ገልጸዋል ።
የመጀመሪያውን ገለጻ በሁቱ እና ቱሲ ስለነበረው ከተማሪውች ጥናታዊ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን ከማለዳው ጀምሮ የተለያዩ ተማሪዎች እና ምሁራኖች የግላቸውን አስተያየት እና ጥናታዊ ስሁፎችን አቅርበው ለህዝቡ የመወያያ መድረክ ፈጥረዋል ።
በአፍሪካ በተለያዩ ሃገራቶች በተለያዩ ጊዜያቶች የቀረቡት የዘር ማጥፋት ወንጀል ከፍተኛ ቁጥርን ይይዛል ሲሉ ጥናቶች ሲያመለክቱ ከነዚህም ውስጥ ሩዋንዳ ቀዳሚነቱን ይዛ ትገኛለች ።
እስከዛሬ ድረስ ከቅኝ ግዛት ያልተላቀቁት አፍሪካ ሃገራቶች በተለያየ የአስተዳደር ጭቆና ከፍተኛውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በራሳቸው ዜጎች እንዲፈጸምባቸው ከተለያዩ የአውሮጳ ሃገራቶች ጫና እንደሚደረግባቸው ተጠቁሞአል።በሌላም በኩል በሩዋንዳ ከተደረገው ጭፍጨፋ እንደሚያመለክተው ከሆነ ፣ጭፍጨፋው ከመካሄዱ 3 አመታት ቀደም ብሎ የቋንቋ መለወጥ እና ህዝብን በተለያየ ጎራ ማየቱ ክፍተኛውን የግድያ ጫና እንዲኖር አድርጓል ሲሉ የአፍሪካ ጥናት እና ምርምር ተመራማሪ ገልጸዋል።
የሩዋንዳ ተወላጅ የሆነችው ጄኒም በ1972 በሃገሯ የተፈጠረውን የዘር ማጥፋት በግልጽ ምን አይነት እንደነበር እና እንዴት ከዚያ አሰቃቂ የጅምላ ግድያ እንደተረፈች የገለጸች ሲሆን ፣ እንዴት በባህል በህዝብ እና በሃገር እንዴት አይነት የዘር ማጥፋት እንደተካሄደ በጥልቀት ማወቅ እና ለማወቅ መጣር እንዳለብን አመክራ ትገልጻለች ፣በተለይም ብዙ አይነት የዘር እና የቋንቋ ተናጋሪ ባለበት በዚህ ሰፊ አለም ላይ በተለያዩ አጋጣሚዎች ልናውቃቸው የምንችላቸውን ነገሮች ጠልቀን እንዴት በአፍሪካ ሃገራት ላይ የጅምላ ግድያ ተከናወነ ብለን ጥልቅ የሆነ ምርምር ማድረግ አለብን ብላ ትጠቁማለች ።
በሌላ በኩልም የዚሁ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነችው ወጣት ሳራ እንደ ባህር በጥልቅ በሆነው የአፍሪካ አገር ላይ የሚካሄደውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በሰፊው በአፍሪካ መካሄዱን እና በዚሁ አገር ብዙ ነገሮችን ማካለል እና ማጥናት እንደቻለች ገልጻለች ።
በናጀሪያ ስለተካሄደውም የጅምላ ግድያ አስመልክቶም የካቶሊክ ቶዮሎጂ እና የሳይኮሎጂ ጥናት ተመራማሪ እና የአፍሪካን ጥናት ተቋም ሰፊ ዘገባ ለማቅረብ ሞክረዋል ።
በቀጣይም የኢትዮጵያው የሰበአዊ መብት ተከራካሪ እና አክቲቪስት ኦባንግ ሜቶ በአሳለፍነው 25 አመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለተካሄደው የዘር ማጥፋት ወንጀል እና እንቅስቃሴውን አስመልክቶ በ4 ፡15 እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል
Average Rating