www.maledatimes.com ለጋዜጠኛው መታሰቢያ (ከይግዛው እያሱ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ለጋዜጠኛው መታሰቢያ (ከይግዛው እያሱ)

By   /   October 6, 2012  /   Comments Off on ለጋዜጠኛው መታሰቢያ (ከይግዛው እያሱ)

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 15 Second

መታሰቢያነቱ ቃሊቲ እስር ቤት ለሚገኘው ለ”እውነት ” ተሟጋች ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም ፀሀፍት:-

ቢታሰር ቢገረፍ ሲቃይ ቢበዛበት

አጥላልተው አንቋሽሸው ምራቅ ቢተፉበት

ከምንም ሳይቆጥረው ይህን ሁሉ እንግልት

መጻፉን አይተውም ለቆመለት እውነት::

የሰማውን እና በአካል ያየውን

ወይ መጽሀፍ አንብቦ ይበጃል ያለውን

ለህዝብ ጀሮ ማድረስ ምርጫው ስለሆነ

ራሱን አይወድም ሰው ለሰው  ከቆመ::

ሻማ ሆኖ ሊያልቅ በራሱ ወስኖ

ብርሀኑን ሊያስቀምጥ ፋና ወጊ ሆኖ

ስለእውነት ተራኪው የብእሩ አርበኛ

መቸም እረፍት የለው እፎይ ብሎ አይተኛ::

እውነትን አንግቦ ለህዝብ በመቆሙ

ውሸት ሲበዛበት ቢያቅተው መሸከሙ

እገዙኝ አይልም የማይጠቅምን ነገር

በብዕሩ ያርፋል እውነት በመናገር::

ጋዜጠኛም ይሁን ደራሲ ፀሀፊ

ከዚህ ውጭ አይደለም ዝም ብሎ አንገት ደፊ::

ውሸት ስለማይጽፍ ከየትም አምጥቶ

ተሸማቆ አያውቅም ለህይወቱ ፈርቶ::

እውነትን የሚያፍን የእውነት ቀበኛ

መጨፍለቅ ቢያስብም ይህን ጋዜጠኛ

እውነት ግን ህያው ናት አብራ የማትጠፋ

አንድ ቀን ብቅ ምትል ውሸት ሲያንቀላፋ::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar