www.maledatimes.com የተባበረችውን ኢትዮጵያን በጋራ እንገነባለን ገለታው ዘለቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

     የተባበረችውን ኢትዮጵያን በጋራ እንገነባለን                                             ገለታው ዘለቀ

By   /   November 2, 2016  /   Comments Off on      የተባበረችውን ኢትዮጵያን በጋራ እንገነባለን                                             ገለታው ዘለቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 12 Second

cropped-cropped-Maleda-Times-Logo-1-e1478022333437.jpg

 

በቅርቡ በአንድ የኦሮሞ ወገኖች ስብሰባ ላይ አንድ ሰውየ ኦሮምያ ሰላም የምታገኘው ኢትዮጵያ ስትፈራርስ ነው ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት አለ ተብሎ ሲራገብ እያየን ነው። እኔ በግሌ የዚህን ሰው ተልእኮ ለመረዳት ቅንጣት ጊዜ አልወሰደብኝም። ከራሱ ከወያኔ በቀጥታ መልእክት እየተቀበለ የሚሰራ የወያኔ ተቀጣሪ ነው ወይም እያጃጃሉ በስልት የሚጠቀሙበት ሰው ነው። አለቀ።

 

ይህንን ለማለት ያስቻለኝ ነገር እንደሚታወቀው ይህ መንግስት ገና ሲመሰረት ጀምሮ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያስችለው መሳሪያ  ህዝባዊ ድጋፍ አይደለም። በዚህ ጎጠኛ የፓለቲካ አስተሳሰቡና በሙስና ድር በተፈጠረ ሥርዓት ምን ጊዜም ሰፊ ህዝባዊ ድጋፍ አገኛለሁ ብሎ አያስብም። ይህንን መንግስት በሚገባ ያውቃል። ይህን ስርዓት እድሜ ይቀጥልለታል ተብሎ የሚታሰበው ስልት ቅራኔ ነው። ለዚህም ነው መንግስት ከህገ መንግስቱም በላይ አብዮታዊ ዴሞክራሲን የሚያራግበው። ምክንያቱ ቅራኔዎችን እየፈጠረ በዚያ ቅራኔ መሃል ነው ስርዓቱ ህልው የሚያገኘው። በኢትዮጵያ ውስጥ ቅራኔ ሲፈልጉ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት የመደብ ቅራኔን ማንሳት ስለማይችሉ ቅራኔውን የመሰረቱት በአለፈ የሃገሪቱ መጥፎ ትዝታዎዥ (past bad memories) ላይ ነው። ያለፈውን የታሪክ ትውስታ በነባራዊው እውነት ላይ እየጨማመሩና እያራገቡ ሲያስፈልግም እንደ አኖሌ አይነት ሃውልት እያቆሙ ቅራኔን ማራገብ ነው። በዚህ ጊዜ ፓለቲካው በብሄር ላይ ስለቆመ ያለፈ የታሪክ ግድፈት ለቅራኔ መሰረት ሲሆን ያን ያለፈ ችግር ወደ አንድ ብሄር በማላከክ ቅራኔው ሲራገብ አቅጣጫው በቀጥታ ወደ ብሄር ግጭት ይሄዳል። በዚህ መሰረት ወያኔዎች ቅራኔውን ሲያራግቡ በተለይ ሁለቱ ብዙ የሰው ሃይል ያላቸው አማራና ኦሮሞ ቅራኔ ውስጥ ይገባሉ የሚል ስልት ይዘው ነው። የታሪክ ቅራኔው በብሄር ፓለቲካ ከባቢ ውስጥ ሲግል ይህ ቅራኔ በቀጥታ ወደ ብሄር ግጭት ይዞራልና ነው። ይሄ ስልት የወያኔ የስልጣን መሰረት ተደርጎ የሚወሰድ ነው። በሌላ በኩል ያለው ቅራኔ ደግሞ መድብለ ፓርቲውን የአንድነት ሃይልና የብሄር ሃይል በመፍጠር እነዚህን ሃይላት ማናቆር በየብሄሩ አክራሪ ብሄርተኞችን በማፍራት ከአንድነት ሃይሉ ጋር እንዲናቆሩ ማድረግና የየብሄሩ አክራሪ ሃይላት እርስ በርስ እንዲነቃቀፉ ማድረግ ነው። እነዚህ ሃይላት በቀላሉ ስለማይገናኙ ይህ የፓለቲካ ቅራኔ የስልጣን መሰረቴ ነው ብሎ ህወሃት ኢህአዴግ በጣም ያምናል። ቅራኔዎች በብሄርና በመድብለ ፓርቲው አካባቢ ሲበዛ ከእኔ ላይ ገለል ይላሉ ነው ስልቱ።

 

መንግስትን ህዝባዊ መሰረት የሚያጎናፅፈው ተመራጭ የፓለቲካ አስተሳሰብ ባይኖረንም ግን ቅራኔ መብዛቱ አንድን ጠባብ ቡድን በኢኮኖሚው ዘርፍ እስክንለውጥ ድረስና የበላይነቱን እስክናቆናጥጥ ጊዜ ይሰጠናል ብለው የስርአቱ ዋናዎች በሃይል ያምናሉ።

 

ታዲያ ይህ ስልት ባለፉት አመታት የተጠቀሙበት ቢሆንም በቅርቡ የተነሳው ህዝባዊ ንቅናቄ የዚህን መንግስት የስልጣን መሰረት የሆነውን የብሄር ቅራኔ መቀመቅ እያወረደው ነው። አማራውና ኦሮሞው ማዶ ለማዶ እየሆኑ ደምህ ደሜ ጉዳትህ ጉዳቴ ነው እያለ አስገራሚ ህብረት ሲያሳዩ መንግስት እጅግ ደንግጧል። ለምን ካልን ከፍ ሲል ያልነው ስርዓቱ በቅራኔዎች ላይ የተመሰረተ ሲሆን ህዝቡ እነዚህን መሰረቶች መናድ ስለጀመረ ነው። ስለዚህ ይህ ህዝባዊ ድጋፍ የሌለውና ቅራኔዎች ላይ ተንጠልጥሎ ያለ መንግስት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ሊወያይ የሚችለው ነገር ይህን ቅራኔ እንዴት እናድስ? የስልጣናችን መሰረት እየተናደ ነውና እንዴት እንደገና ቅራኔውን እናራግብ የሚል ነው። ያለ ጥርጥር በቅርቡ በኦሮሞ ተወላጅ ወገኖቻችን ስብሰባ ላይ ያንን ከሃዲ ቀስቅሰው ኢትዮጵያን እናፈርሳለን በል ሲሉ ያ ሰው ይህንን ሲል ቀበል ብለው መነጋገሪያ እንዲሆን አደረጉ። አንዳንድ የዋሆች ወያኔን ትተው ወይኔ የሚፈልገውን ቅራኔ ወዲያው ያዙለት። ወያኔ ይህ ቅራኔ ሲነሳ እፎይ እላለሁ አስቀየስኩ (divert አደረኩ) ይላል።

 

የሚገርመው አንዳንድ የዋሆች ሰውየው የሚናገረውን መንፈስ እንኳን ላይመረምሩ ይችላሉ። እርግጥ ነው ባለፉት ጊዚያት ወያኔዎች ያልሆኑ አንዳንድ የኦሮሞ ተወላጆች ሪፈረንደም ያስፈልጋል ይሉ ነበር። ይህ ሰው የሚለው እኮ ኦሮምያ ሰላም ትሆን ዘንድ ኢትዮጵያ መፈራረስ አለባት መበታተን አለባት ነው። ይህንቃል በማየት ብቻ ንግግሩ የሆነ ሃይል ከሁዋላው እንዳለ ያሳያል። በመገንጠል የሚያምኑም እንዲህ አይናገሩም። ቃሎቹ ራሳቸው ለሶሻል ሚዲያ ዋና ጉዳይ እንዲሆኑ በወያኔ የተቀመሙ ናቸው። ይህንን መገምገም አለብን። በሌላ በኩል ይህ ሰው ሲናገር ጭብጨባ ነበር። የወያኔን ስልት ከ25 አመት በሁዋላ ያልተረዳ ካለ ያሳዝናል። በየመድረኩ ህዝብ የማይወደውን ነገር መናገር ሲሹ በስብሰባው መሃል እዚያና እዚያ ፈንጠር እያሉ ጥግ እየያዙ ካድሬዎች ይቀመጡና ጭብጨባና ፉጨቱን ያግሉታል። ይሄ ብዙ ጊዜ የሚያደርጉት ነገር ነው። በአጠቃላይ ይህ ኮንፈረንስ ብዙ የኦሮሞ ልጆች በሃቅ ለሃገራቸው መላ ለመሻት የኦሮሞን ህዝብ ትግል ለመደገፍ የተነሱ ሰዎች እንዳሉበት ሁሉ ወያኔም ጥሩ መድረክ ያገኘበት ጉባኤ ነበር። ስብሰባው ዴሞክራሲያዊ መሆን እንዳለበት አምናለሁ ነገር ግን እንዲህ አይነት አገር አፈርሳለሁ የሚል ወንበዴ ሲነሳ ይሄንን ሰው አውጥቶ መጣል እንጂ ዝም ማለት አይገባም። ወያኔዎች ውጭ አገር ሲመጡና ስብሰባ ሲጠሩ ለምን ስብሰባቸውን አክቲቪስቶች ይበጠብጣሉ? አገር እያፈረሳችሁ ነው በሚል አይደለም? እንዲህ አይነቱ የወያኔ ቅጥረኛ በአንድ ስብሰባ ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ሲል እንዴት ዝም ይባላል?።  አንድ መዘንጋት የሌለብን ነገር በሚመጣው ህዳር ወር ላይ በሚኖረው ስብሰባ ላይ እንዲሁ ኢትዮጵያ ትፍረስ የሚሉና የሚያጨበጭቡ ካድሬዎች መዘጋጀታቸውን እንጠብቅ። አዘጋጆቹም ሃሳብ በነፃነት እንዲንሸራሸር ማድረጉን ሳይዘነጉ ለፍተው ያዘጋጁትን መድረክ የወያኔ መፈንጫ እንዳያደርጉ መጠንቀቅ አለባቸው። ሌላው መሰረታዊ ነገር መታወቅ ያለበት ዲያስፓራው ያለው ሚና ሃገር ቤት ያለውን ትግል መደገፍ ነው። ህዝቡ ህብረትና ትብብርን ሲያሳይ ኢትዮጵያን እናፈርሳለን የሚል ሃይል ከመጣ ከወያኔ ሌላ ከቶ ማን ይሆናል። ዲያስፓራው ይህንን ህብረት ማየትና በገንዘቡ በዲፕሎማሲው መደገፍ እንጂ የህዝቡን ትግል ለማናጋት ቢሰራ ተቀባይነት አያገኝም። በተረፈ እነዚህ ኢትዮጵያን እናፈርሳለን የሚሉ ሃይላት ከወያኔም በላይ የምንዋጋቸው መሆናቸው መታወቅ አለበት። በስንት የኦሮሞ ጀግኖች ደምና አጥንት የተገነባችን አገር በአባቶች መቃብር ላይ ቆሞ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ የሚል ሃይል የኦሮሞ ልጆችን መሳደብ ነው። ሁላችንን መሳደብ ነው። ከዚህ በተረፈ የወያኔን ስልቶች ሁል ጊዜም አንዘንጋ። ለምን ዝንጉ እንሆናለን?። እነሱ እኮ ስራቸውን እየሰሩ ነው። አንድ ጊዜ የጉዳይ ማስቀየሻ ስልታቸውን ካወቅን በሁዋላ እንደገና መታለል የለብንም። የቅራኔ መሰረቶቻቸውን በህብረት መስበራችንን መቀጠል አለብን። እነሱ በየጊዜው እያጠኑ የሚሰሩልንን የማስቀየሻ  ጉዳዮች ስናብጠለጥል እነሱ ጊዜ አገኙ ማለት ነው። ለወያኔ መንግስት ውሎ ማደር ወሳኝ ነው። ራእይ የላቸውም። ነገር ግን ትግሎች በዘገዩ ቁጥር የጀመሩት ቢዝነስ ይዳብራል ከሚል ነው። ተቃዋሚውን ህዝቡን ትግሉን ማዘግየት ዋና የስልጣን ዘመን ማራዘመያ መሳሪያዎች ናቸውና ኢትዮጵያውያን በህብረት በፍጥነት ትግላችንን እንቀጥል። አሁን የተቋቋመው ኮማንድ ፓስት በውጭ አገር በሚኖረው ትግል ላይ የሚኖረው ሴራ እንደዚህ አይነት ድራማዎችን እየሰሩ ሃይልን ህብረትን መበተን ነው። ይህንን አንዘንጋ። የኦሮሞ ወገኖችም የሚመጣው ስብሰባችሁ የተሳካ እንዲሆን እመኛለሁ።

 

 

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

geletawzeleke@gmail.com

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on November 2, 2016
  • By:
  • Last Modified: November 2, 2016 @ 1:29 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar