www.maledatimes.com ኤጀንሲው የታላቁ ሩጫ ሀብት ለሌሎች ይተላለፋል እንጂ አይወረስም አለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኤጀንሲው የታላቁ ሩጫ ሀብት ለሌሎች ይተላለፋል እንጂ አይወረስም አለ

By   /   October 7, 2012  /   Comments Off on ኤጀንሲው የታላቁ ሩጫ ሀብት ለሌሎች ይተላለፋል እንጂ አይወረስም አለ

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 13 Second

ሪፖርተር

ሃይሌ ገብረ ስላሴ የተማመነበት ነገር አለን ? ወይስ እሱው እራሱ የካድሬ አባል ሆኖ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ይሆን እንዲህ ደፍሮ የወያኔ አስተዳደርን ለመናገር የቻለው ካለበለዚያ ግን ይህንን የታላቁን ሩጫ ንብረት የተባለውን ይወረሳል ሲባል አሜን ብሎ ሊቀበል ይችል ይሆናል እንጂ አይወረስም ብሎ ጣቱን አይቀስርም ነበር ለማንኛውም ከሪፖርቱ አጠቃላይ ይዘቱን እንመልከት ።መልካም ንባብ ማለዳ ታይምስ

‹‹የታላቁ ሩጫ ሀብት ይወረሳል መባሉ ስፖንሰሮችን አስደንግጦብናል›› አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ

በዮሐንስ አንበርብር

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ የታላቁ ሩጫ ሀብት ለሌሎች በጎ አድራጊዎች ይተላለፋል እንጂ አይወረስም አለ፡፡

ሪፖርተር የታላቁ ሩጫ ሀብትና ንብረት ሊወረስ ነው በማለት ባለፈው ሳምንት ያወጣው ዘገባ፣ የዘንድሮውን ታላቁ ሩጫ ስፖንሰር ያደረጉ ድርጅቶችንና ተሳታፊዎችን አስደንግጦ ሰንብቷል ሲል አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ገለጸ፡፡ የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት የሥራ ሒደት ባለቤት አቶ አሰፋ ተስፋዬ በሪፖርተር ላይ የወጣው ዘገባ የተዛባ መሆኑን ገልጸው፣ የድርጅቱ ሀብትና ንብረት ለሌሎች ይተላለፋል እንጂ አይወረስም ብለዋል፡፡

ታላቁ ሩጫ ‹‹አይ አም ራኒንግ ፎር ኤ ቻይልድ›› በሚል ዓላማ ከዋናው ሩጫ ቀደም ብሎ የሚከናወነውን ሩጫ ለማስተዋወቅ ባለፈው ሐሙስ በሒልተን ሆቴል ባዘጋጀው መድረክ ጐን ለጐን፣ የሪፖርተር ዘገባ በስፖንሰሮች ላይ የፈጠረውን መደናገጥ ለማረጋጋት ተጠቅሞበታል፡፡

አትሌት ኃይሌ ለንባብ በበቃው ዘገባ ላይ የታላቁ ሩጫ ሀብትና ንብረት ‹‹እንዳይወረስ›› ወይም በኤጀንሲው አባባል ‹‹እንዳይተላለፍ›› ለማድረግ ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጋር በውይይት ላይ መሆኑን መናገሩ የሚታወስ ሲሆን፣ በሐሙሱ የሒልተን ሆቴል መድረክ ላይም ቢሆን ዘገባው ሐሰት ወይም የተዛባ ነው አላለም፡፡

ለሪፖርተር ጋዜጣ የመጀመርያው ዘገባ አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ አሰፋ ተስፋዬ ግን፣ ‹‹ዘገባው ከርዕሱ ጀምሮ የተዛባ መረጃን ለማስተላለፍ ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ ነው፤›› ሲሉ ትችታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

ሀብትና ንብረቱን መንግሥት ሊወርሰው ነው የሚለው ርዕስ ተገቢ እንዳልሆነና መንግሥት የማንንም የበጐ አድራጐት ድርጅት ንብረትና ሀብት እንደማይወርስ በመጥቀስ፣ በሕጉ መሠረት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችን ንብረትና ሀብትን በማጣራት፣ ለሌሎች ተመሳሳይ በጐ አድራጐት ድርጅቶች አልያም መጠነኛ መመሳሰል ላላቸው በጐ አድራጊዎች እንደሚተላለፍ ገልጸዋል፡፡

ታላቁ ሩጫ ትርፍ በሚያስገኝ ሥራ ላይ ተሰማርቶ መገኘቱን ኤጀንሲው ባረጋገጠ ወቅትም፣ የድርጅቱ ኃላፊዎችን በማወያየት ጥሩ መግባባት ላይ መድረሱን አቶ አሰፋ የገለጹ ሲሆን፣ ሀብትና ንብረቱ በምን ሁኔታ ለሌሎች ድርጅቶች ይተላለፍ በሚለው ሐሳብ ላይ ገና ውሳኔ እንዳልተሰጠ ተናግረዋል፡፡

አትሌት ኃይሌ ታላቁ ሩጫን በአትራፊ ድርጅትነት ለማስመዝገብ የተጀመረው ጥረት በጥሩ መስመር ላይ እንደሚገኝ ለታዳሚዎች ተናግሯል፡፡ ገንዘብ በባንክ የተቀመጠው  ምናልባት ስፖንሰር ባይገኝ ውድድሩን ለማስቀጠል ይጠቅማል በሚል ሲሆን፣ ታላቁ ሩጫ በማንኛውም ምክንያት ሊቆም እንደማይችል በእርግጠኝት እምነቱን ጠቁሟል፤ ‹‹ታላቁ ሩጫ ለሚቀጥሉት 100 ዓመታት ይቀጥላል፤›› በማለት፡፡

ባለፈው ሳምንት የሪፖርተር ዘገባ ላይ ግን ሀብትና ንብረቱን ከተነጠቀ ታላቁ ሩጫን ለማስቀጠል ችግር ውስጥ እንደሚገባ መናገሩ የሚታወስ ነው፡፡ አቶ አሰፋ በዚሁ መድረክ ላይ እንደተናገሩት፣ ኤጀንሲው ከታላቁ ሩጫ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ በጐ አድራጊ ድርጅት ባለመኖሩ፣ በተለያዩ አካባቢዎች በመገንባት ላይ ለሚገኙ የአትሌቲክስ መንደሮች ሀብትና ንብረቱን ለማስተላለፍ ዕቅድ እንዳለ ነገር ግን ሙሉ ውሳኔ እንዳልተሰጠበት ተናግረዋል፡፡

ታላቁ ሩጫም እንደ አዲስ ሥራውን ሲቀጥል ከባዶ መነሳት እንደሌለበት የኤጀንሲው እምነት እንደሆነና ትንሽ እርሾ ገንዘብ ለመስጠት ዕቅድ መኖሩን ከጠቆሙ በኋላ ይህም ውሳኔ እንዳላገኘ አስረድተዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 7, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 7, 2012 @ 6:24 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar