www.maledatimes.com የኢትዮጵያን ኣትሌት በቺካጎ ክብረ ወሰን ሰበሩ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያን ኣትሌት በቺካጎ ክብረ ወሰን ሰበሩ

By   /   October 7, 2012  /   Comments Off on የኢትዮጵያን ኣትሌት በቺካጎ ክብረ ወሰን ሰበሩ

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 48 Second

የኢትዮጵያ ኣትሌቶች በክብር ኣሸነፉ ከኣንድ እስከ ሶስት የወጡት ጸጋዬ ከበደ ፈይሳ ሊሊሳ አና ረጋሳ ጥላሁን ሲሆኑ ያሸነፉበት ርቀት  ፪፥0፬፫፰  ፣፫፥0፬፭፪ አና ፪፥0፭፪፰ ሲሆን ኣንድ አና ሁለት የወጡት ማራቶን ሩጮች የኣለም ክብረወሰንን መስበራቸው ክስፍራው የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ሪፖርቱን ኣቅርቦኣል ፥በዛሬው አለት ከማለዳው ፩፥፴ የተጀመረው ይሄው የሩጫ ውዽር ለኢትዮጵያን ኣትሌቶች ጥሩ አና ኣመቺ የኣየር ንብረት የነበረው ሲሆን ፬፫ ዲግሪ ፋራናይት የሆነ ቅዝቃዜ ስለነበርው ይህ ደግሞ ከተወለዱበት አና ካደጉበት ኣገር አንደዚሁም ከኣዲስ ኣበባ የኣየር ንብረት ጋር በመመሳሰሉ በወንዶች ከኣንድ አስከ ሶት ለመውጣት አና በሴቶች የኣንደኝነትን ቦታ ድል ለመቀዳጀት በቅተዋል፤፤በኣሁን ሰኣት በሂልተን ሆቴል ቺካጎ በሚሰጠው የሚዲያ ኮንፈረንስ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ኣትሌቶች በወንዶች በኩል ለኣለም ኣቀፍ ሚዲያ የደስታ ሃሳባቸውን በመግለጽ ላይ የሚገኙ ሲሆን በሴቶች ኣጸደ ደስታ ከ፴ ደቂቃ በፊት ቃለመጠይቅ ኣድርጋለች ፥፥በተመሳሳይ ዜና የቺካጎ ራሃም ኢማኑኤል ድልን ለነቀዳጁት ኢትዮጵያን ኣትሌቶች አና ለማለዳ ታይምስ ኣዘጋጅ ጋዜጠኛ የደስታ መግለጫቸውን ያቀረቡ ሲሆን የኣበባ ጉንጉን ለኣትሌቶቹ ሲያበረክቱ ኣትሌቶቹ ደግሞ ከባንክ ኦፍ ኣሜሪካ የተዘጋጀላቸውን ስጦታ ፊርማቸውን በማኖር ለባንኩ ሃላፊ አና ለቺካጎ ከንቲባ ስጦታ ኣበርክተዋል፥፥ዘላለም ገብሬ ማለዳ ታይምስ ሪፖርት ከቺካጎ ማራቶን ኢሌት

HOME >
Marathon Winners Medal Presentation

Tsegaye Kebede and Atseda Baysa are presented with the winning medals at the 2012 Bank of America Chicago Marathon.

Source:http://www.nbcchicago.com/video/#!//Marathon-Winners-Medal-Presentation/173026791#ixzz28eWp7MMe

በዛሬው እለት የተካሄደው 35ኛው የባንክ ኦፍ አሜሪካ ቺካጎ ማራቶን  40 ሺ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈው ኢትዮጵያውያኖች  የአሸናፊነት ቦታን  ከአንድ እስከ ሶስተኛ ድረስ በወንዶች የአሸናፊነትን ጽዋ ሲጎነጩ በሴቶች ደግሞ የመጀመሪያውን ደረጃ በመያዝ አሸናፊዎች ለመሆን በቅተዋል ። በከፍተኛ ደረጃ አጓጊና ልብ ሰቃይ ሆኖ ያለፈው ይኼው የሩጫ ውድድር ገና በማለዳው 7፡30 ደቂቃ ነበር የተጀመረው ፣የማለዳውን ቅዝቃዜ በመቆጣጠር እና ሃይላቸውን በማቀናጀት ሩጫውን የራሳቸው ለማድረግ የሮጡት ኢትዮጵያኖች በዛሬው እለት በለስ የቀናቸው በወንዶች አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡት የማራቶን ሯጮች የአለም አቀፍ ክብረ ወሰን ሲሰብሩ በተለይ የሁለተኛው ሯጭ የተመዘገበለት የዛሬ 2 አመት በቺካጎ ተወዳድሮ ያሸንፈው እና በኬኒያዊው ሳሚ ዋንጅሩ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በመስበሩ መሆኑ ተገልጾአል።በወንዶች ከአንድ እስከ 3ኛ ደረጃ የወጡት አትሌቶች ስም ዝርዝር እና ሰአታቸው እንደሚከተለው ቀርቦአል።

ጸጋዬ ከበደ 2፡04፡30    ፈይሳ ሊልሳ  2፡04፡52   እና ረጋሳ ጥላሁ 2፡05፡28 ሲያጠናቅቁ

ከአራተኛ ተራ ቁጥር እስከ ሰባተኛ ድረስ ኬንያውያን ተከታትለው ሲገቡ 8 ተራ ቁጥር ላይ ኢትዮጵያዊው ያሚ ዳዲ 9 አሜሪካ እና አስረኛ ተራ ቁጥር ላይ ደግሞ ኢትዮጵያዊው ዳዊት ሻሚ ሆነው ተመዝግበዋል።በሴቶች ደግሞ አጸደ ባይሳ በአንደኛነት ደረጃ ስታጠናቅቅ የገባችበትም ሰአት 2፡22፡03 ሲሆን የዛሬ ሁለት አመት 2ኛ መውጣቷን ለህብር ሬድዮ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን  ኬንያዊቷን የረጅም ርቀት ሯጭን ሪታ ጆፕቶን የቀደመቻት ለአንድ ሰከንድ  አንድ እርምጃ እንደሆነ የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ከስፍራው ዘግቦአል። ይህ የማራቶ ዝግጅት በለንደን ፣ኒውዮርክ ቦስተን እና ቺካጎ በየአመቱ የሚደረግ ታላቅ የማራቶን ውድድር ነው ። ለማለዳ ታይምስ እና ለህብር ሬድዮ ዝግጅት ከቺካጎ ዘላለም ገብሬ …ነኝ።

 

 

ማሳሰቢያ፤በዌብሳይታችን ላይ ለሚወጡ ማናቸውም ጽሁፎች ቀዳሚ የሆነ የዌብሳይታችንን አርትኦት ስራን ለማክበር ሲባል በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በማለዳ ታይምስ የመረጃ ማእከል ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የማለዳ ታይምስ የመረጃ ማእከል ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዌብሳይቱን  ጠቋሚ (አመልካች ) (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.maledatimes.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን(የማለዳ ታይምስ ህግና ደንብ በንግድ በተመዘገቡበት ሁለት አገሮች የረቀቀ ሲሆን በሁለቱም አገሮች አንድ አይነት የሆነ አሰራር ይዞ ይከተላል ።ይህንን ህግ ማንኛውም ሰው መቅዳት የማይችል መሆኑን እንገልጻለን።ንብረትነቱ እና ህገ ደንቡ የማለዳ ታይምስ ብቻ ነው!)፡፡ይህ ካልሆነ ግን በህገ ደንባችን መሰረት አስፈላጊውን የህጋዊ ጥያቄ ለማቅረብ የምንገደድ መሆኑን እንጠቁማለን::በዚህ አጋጣሚ በግለሰብ ለሚላኩ ጽሁፎች ሁሉ ተጠያቂው ስሙ የተገለጸው ግለሰብ እንጂ የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ሃላፊነቱን እንደማይወስድ እናሳስባለን ::

press conferens TSEGAYE KEBEDE

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 7, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 8, 2012 @ 10:50 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar