0
0
Read Time:32 Second
(ዘ-ሐበሻ) ከ700 በላይ ሰዎች በተሰዉበት የቢሾፍቱው የእሬቻ በዓል ላይ መድረክ ላይ ማይኩን ከተናጋሪዎች በመቀማት “ዳውን ዳውን ወያኔ / Down Down Woyane” በማለት ሲያወግዝ የነበረው ወጣት ጉዳይ ብዙዎችን ሲያነጋገር ቆይቶ ነበር:: ይህ ወጣት በሕይወት ይኖር ይሆን? ሲሉ የሚጠይቁ በርካታ ነበሩ:: በተመሳሳዩም የኦሮሞ ሕዝብ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተቃውሞ በወጣበት ወቅት እጆቹን ወደላይ በማድረግ (Say No to The Master Plan) ተቃውሞውን ሲያሰማ ፎቶ ግራፉ በሶሻል ሚድያዎች እና በድረገጾች ላይ በስፋት የሚታየው ወጣት ተቃዋሚ ጉዳይም አነጋጋሪ ነበር:: ዛሬ ከወደ ግብጽ ካይሮ በኦሮሞ አክቲቭስቶች በኩል የተለቀቁ አዳዲስ ፎቶዎች እንደሚያሳዩት ሁለቱም ወጣት ታጋዮች ግብጽ ካይሮ ይገኛሉ:: ይህ መረጃ በብዙዎች አእምሮ ውስጥ ለሚመላለሱ “የት ደረሱ?” ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል ብለን እናስባለን::
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating