www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ፓርላማ አባላትን “እግዚአብሄር ኢትዮጵያን በበረከቱ ይጠብቃት” መባሉ አሳቃቸውያሳዝናል! (ደረጀ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ፓርላማ አባላትን “እግዚአብሄር ኢትዮጵያን በበረከቱ ይጠብቃት” መባሉ አሳቃቸውያሳዝናል! (ደረጀ)

By   /   October 18, 2012  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ፓርላማ አባላትን “እግዚአብሄር ኢትዮጵያን በበረከቱ ይጠብቃት” መባሉ አሳቃቸውያሳዝናል! (ደረጀ)

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 13 Second

የትናንቱን የፓርላማ ውሎ አላየሁትም ነበር። ስብሰባውን በኢቲቪ የተከታተለ ጓደኛዬ፤ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ንግግራቸውን ሲጨርሱ<< እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን በበረከት ይጎብኛት>> በማለታቸው አፈ-ጉባኤውን አባ ዱላን ጨምሮ የፓርላማ አባላቱ እንደሳቁ በፌስ ቡክ ገጹ አስነበበን ። “ በዚህ እንዴት ሊስቁ ይችላሉ?”ብዬ ቅሬታዬን ስገልጽ ሌለኛው ጓደኛዬ፦< ..የሳቁትኮ “..በበረከት ይጎብኛት” የሚለውን አባባል- ከአቶ በረከት ስምዖን ጋር አያይዘውት ነው>> ብሎ በማስፈገግ አረጋጋኝ። አሁን ቪዲዮውን ሳየው ግን የሳቁት የንግግሩ ቅኔነት ገብቷቸው ሳይሆን፤ የእግዚአብሔር ስም በመጠራቱ እንደሆነ ተረዳሁ።
ያደጉትና የሰለጠኑት አገሮች ዶላራቸው ላይ፦We Trust in God እያሉ ሲጽፉ፤ እነ አባ ዱላና መሰሎቻቸው፦ <እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርካት>በሚል ንግግር መንጋጋቸው እስኪታይ ይስቃሉ።ልብ በሉ! ሰውን እያመለኩ ያሉ ደካሞች ናቸው በእግዚአብሔር ስም መጠራት የሳቁት። ይሁን እንጂ ቅሬታዬ “ለምን አሜን አላሉም?” ከሚል የመነጨ አይደለም። አለማመን ወይም በፈለጉት ማመን መብታቸው መሆኑን አውቃለሁ። እያልኩ ያለሁት ፤ብብቱን እንደኮረኮሩት ሰው የእግዚአብሔር ስም ሲጠራ፤ ምን አስገለፈጣቸው ነው?
<<የሮማው ፈረስ ካሊጉላ-በንቀት ልቡ የሰባ፦

ታዛዥና ተጋላቢ-ፈረሱን ፓርላማ አስገባ፣
ከዚያን ዕለት ጀምሮ-ፈረሶች ወንበር ለመዱ፣
ለማመን ማየት ካሻችሁ-እኛ አገር ፓርላማ ሂዱ>> ያለው ማን ነበር?
እነሆ ቪዲዮው፦
http://www.amharictube.com/musicvideo.php?vid=21a52302b
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 18, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 18, 2012 @ 7:56 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar