www.maledatimes.com “ኢትዮጵያ አገራችንን እና ህዝቧን እግዚአብሄር በበረከት ይጎብኛት “ ወይስ ታላቁ የህዳሴ መሪን ማቹን መለስን እግዚአብሄር ይጎብኝ “?ይትኛው ይልቃል ?(ማለዳ ታይምስ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“ኢትዮጵያ አገራችንን እና ህዝቧን እግዚአብሄር በበረከት ይጎብኛት “ ወይስ ታላቁ የህዳሴ መሪን ማቹን መለስን እግዚአብሄር ይጎብኝ “?ይትኛው ይልቃል ?(ማለዳ ታይምስ)

By   /   October 19, 2012  /   Comments Off on “ኢትዮጵያ አገራችንን እና ህዝቧን እግዚአብሄር በበረከት ይጎብኛት “ ወይስ ታላቁ የህዳሴ መሪን ማቹን መለስን እግዚአብሄር ይጎብኝ “?ይትኛው ይልቃል ?(ማለዳ ታይምስ)

    Print       Email
0 0
Read Time:18 Minute, 9 Second

ማለዳ ታይምስ እግዚአብሄር ታላቅ ነው ምስጋናውም እጅግ ከሁሉም በላይ የላቀ ነው !ዛሬ በስልጣን ትእቢት ልባቸው የተሞሉ ሰዎች ግን ብእግዚአብሄር ቃል ሲሳለቁ ማየታችን አሳፋሪ ሆኖ ማየታችን ያለንበትን ዘመን እንድናይ ያመላክተናል ።የቀድሞዎቹ ነገስታት ቅድሚያ የአምላካቸውን እግዚአብሄር ስም በማንሳት እጅ መንሻቸውን በማቅረብ ፣እንዲሁም ስርአተ ጸሎታቸውን በምግባራቸው አድርገው ስራቸውን ሲጀምሩ እና ሲጨርሱ ስናስተውል ኖረናል ።ዛሬ ግን ይህ ሁሉ ተለውጦ በስይጣን አምላኪዎች የተሞሉበት ፓርላማ የአምላክ እግዚአብሄር ስም ሲነሳ መሳቅ መሳለቃቸው ምን ይሉት ይሆን ?

በእርግጥ ለብሄራዊ ጥቅማቸው የተሞሉ እና ለእርሱ ብለው ግዞተኞች የሆኑት እነዚሁ የፓርላማ አባላቶች በአምላክ ስም ቢሳለቁ ማን ከቁብ ሊቆጥራቸው ይችላል።ይህ በእጃቸው የሚገኘውን የጥፋት ሃይል እንደ እንቁ የጠበቁት እነዚሁ የአሻንጉሊት ሰዎች በትላንትናው ታሪካቸው ስናስታውሳቸው ከጥንቆላ ህይወት ጋር የተዛመዱ እንደነበሩ በእርግጠኝነት ልናስታውስ እንችላለን ።ባሳለፍነው ሁለት አመታት ውስጥ በጠንቋዩ ታምራት ስራ ላይ ከፍተኛ ተዋናይ በመሆን ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት ሰዎች ውስጥ በብዛት ይቀርብ የነበረው መረጃ የአርቲስቶች ብቻ እንደነበር ይታወሳል ።ገንዘብ የነበራቸው የእነ አትሌት ሃይሌ ገብረ ስላሴ ለታምራት ገለታ ያደርጉት የነበረው  የግብር ስራ ፣የእነ አቶ ሼክ መሃመድ አላህሙዲ ጉዳይ በሱዳኑ ጠንቋይ መለከፍ፣የነአቶ በረከት ፣አፈ ጉባዔ ስዳዊት ዩሃንስ ፣አዜብ ፣እና ሌሎችም በጥንቆላ መረብ ተተብትበው ስልጣናቸውን ለማራዘም ሲውተረተሩ የነበሩት እነዚሁ የሰይጣን ጉራጆች አገራችን ኢትዮጵያ ላይ ያውም በቅዱስ መጸሃፍ ውስጥ በክብር ቃል የተቀመጠችው ኢትዮጵያ “ኤዞጵ”በግሪከኛው ቃል ምን ያንሰናል የአምላካችንን ክብር እግዚአብሄር ስም በሄድንበት ቦታዎች ሁሉ ብናነሳ ?ነው ወይስ የሚተላለፍው የውሸት አጀንዳ ስለሆነ የሚያመልኩት ጣኦት ተቆጥቶ ቁጣ እንዳያመጣባቸው ፍራቻቸው ይሆን ሳቃቸው ለጣኦታቸው ማስደሰቻ ትርጉም ሊሰጠው የሚችለው?

አንድ ወዳጄ በፌስ ቡክ እንደለጸችልኝ ከሆነ ደግሞ እንዲህ በማለት የኢትዮጵያ ሰው ሳቁን ተርጉሞታል ትላለች ይህችው ወዳጄ

1ኛ የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን የፕሮቴስታንት እምነት ለመናቅ ተፈልጎ ነው ሁለተኛ በአሁን ሰአት ላይ አገሪቱ እየተመተመራች ያለችው በአቶ በረከት ስምኦን ስለ ሆነ ያለው ስለዚህ እርሱም የተናገረው “ሃገራችንን ኢትዮጵያን በበረከት ይጎብኛት ነው”ይህ ማለት በረከት በቀጥታ አገሪቱን እየመራት እንደሆነ ለማስተላለፍ የሞከረበት አጭር የቅኔ ቅል ናት ብላኛለች እና እናንተስ ምን ትላላችሁ?

Ethiopia – “God Bless Ethiopia” quote brought the biggest laugh at the Parliament

 

 

ያስታውሱት ይሆን አንድ ወቅት ላይ ገንዘብ አበዛልዎታለሁ እያለ አታለለን ያሉትን ሱዳናዊ  እንዴት አድርገው የአምልኮ ጣኦታቸው አድርገውት ያመልኩት እንደነበር እና በሸራተን አዲስ ውስጥ ትልቅ የማረፊያ ስፍራ ተሰጥቶት የነ አቶ በረከት ጉዳይ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ የወደፊት እጣፈንታቸው ሲተነተን እንዲሁም የሼኩንም ብር ሆነ ለእነርሱም ብር ይትረፈረፍላቸው ዘንድ ከእንደ ነበር እና እግሩ ስር ተደፍተው ሲያለቅሱ መክረማቸውን የማይጠፋቸው ስንቶቹ አሉ?በወቅቱማ ጉዳዩ እንዲህ ነበር ፡ይህ ሱዳናዊ ታዞ የመጣው እና ጥቆማ የደረሳቸው በደቡብ ሱዳኑ አስተዳዳሪ በኩል ሲሆን ልኡክነቱ ለአቶ ስዩም መስፍን የጤና ጉዳይ ያውቃል ተብሎ እና የእዚህ ሰው ኮቴ አዲስ አበባን እንደረገጠ እሳቤውን ሁሉ ቀይሮ ጥሩ ገንዘብ ሊሰራባቸው እንደሚችል ጥናቱን በመንገድ ላይ እንዳለ ያጠናቅቃል ከዚያም ቀዳሚውን ህመምተኛውን ስዩም መስፍንን ማግኘት ሲሆን እሳቸውን ካገኘ በኋላ የመጀመሪያው እረፍቱ እንዲሆን የተፈቀደለት በሂልተን ሆቴል ተደብቆ እንደነበር ይታወሳል ።ከዚያም አልፎ ሼኩን ጥሩ የባህላዊ ሃኪም እንዳገኙ አማክረው ለጊዜው የሚሆነው ማረፊያ በሂልተን መሰጠቱን ሲገልጹላቸው እሳቸውም ለኑሮአቸው ብልሃት ወሮታ ለመክፈል እንዲያስችል በማለት በሸራተን እንዲቀመጥ አደረግዋል።ይህ ሰው የሰዎቹን ማንነት በደንብ ካጠና በኋላ ስለራሱ የተቀላጠፈ ስራ ሲያወራቸው ሁሉም እውነት መስሎአቸው እና የዚህች አለም ሁሉ ሃብት እና ንብረት የራሳቸው ለማድረግ የተጠሙት ባለስልጣናት በሙሉ ወደዚህ ሱዳናዊ ጋር ጎረፉ ሁሉም እጅ መንሻቸውን ሰጡ ወርቅ አምባር አጠለቁ ፣እንቁ ሰጡ ፣ብር አንበሸበሹት ሁሉንም ተራ በተራ ወደ ሃገሩ የሚያሻግረው ይህ ሱዳናዊ በተሰጠው የጥበቃ ሰራተኛ በኩል በኢትዮጵያ ፖስጣዎች ድርጅት ብቻ ነበር ።ከዚያም አልፎ የገንዘብ ማብዛትን ጥንቆላ ተያያዘላቸው ፣እነርሱም ከአምላካቸው በላይ ሰገዱለት ፣በወይን ፍሬ ሰከሩ እራሳቸውንም እረሱ ለሎችንም ወዳጆቻቸውን ሁሉ አምጥተው በዚሁ ስራ አጠመቋቸው ለምሳሌም ያህል እንደ እነ አርከበ እቁባይ ፣ገነት ዘውዴ ተሾመ ቶጋ የዚሁ ድራማ ተዋንያን ሆነው ነበር ።ከዚያም ጣእማቸው ሲያልቅ እና ሁሉም ነገር እንዳልሆነ ሲያውቁት ይህንን ሰው ክስ መሰረቱበት ከዚያ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቅርብው እንዲፈረድበት ብለኑ አስበውም በፖሊስ ፕሮግራም እንዲታይ ተደረገ ።ነገር ግን የሱዳኑ የአስተዳዳሪ ይሄ ሰው ከደሙ ንጹህ ነው እናንተ የምትወነጅሉት የሃሰት ነው በማለት ሚሲዮኖቻቸውን ልከው እንዲለቀቅ እና ወደ ሱዳን ድንበር መልሶ ዘልቆ እንዲገባ አደረጉት ።እንዲህ ያሉ ወገኖች ሃገሪቷን ለመምራት ትልቁን ሰይጣናዎ ጣኦት እያመለኩ ዛሬ የአምላክ ስም ቢጠራ ምን ይደንቃቸዋል?የእነርሱ አምላክ ሌላ አይደለምን ? ስለዚህ በህዳሴ ስም ለሚያመልኩት ሟቹ አምላካቸውስ ስግደን አያደርጉም …አረ ከሰሞኑ ደግሞ ከሰማነው እናጫውታችሁ … የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እግር ኳስ ውጤትን አስመልክቶ የተለያዩ መረጃዎችን ከህዝቡ ሲያሰማን ሰነበተ እናልዎ ከሰዎቹ መካከል ምን ተባለልዎት”ይህ የአቶ መለስ ትልቅ ታሪክ ነው እርሳቸውንም የሚያኮራ ነው አሁንም በስራቸው ይኮራሉ “አሉልዎ እውነት እርሳቸው መንፈሳቸው ፣ወይንም እስትንፋሳቸው ከስጋቸው ሳትላቀቅ ነው እንዴ የተቀበሩት ወይስ በሙታን መንፈስ ኩራታቸውን ለአድናቂ ህዝቦቻቸው በእንባቸው ሻምባኝ ለተራጩላቸው ደሃ ወገኖቻቸው ትላንት በጥይት አረንቋ ላረገፏቸው ወገኖች ታላቅ ኩራት ሆነው እስከዘላለም ድረስ እና እስከ ምጽአተ ትንሳዔ ድረስ አብረዋቸው ይዘልቃሉ ነው ወይስ በሶስተኛው ቀናቸው እርሳቸውም እንደ ክርስቶስ ተነስተው አርገዋል እንዲህ ውዳሴ ከህዳሴ የተባለላቸው  ፧

ዘመን ዘመን ሆኖ ዘመንን ሳይሽረው

የኢትዮጵያም አምላክ ከፍዳ ሳይጥለው

ከትቢያ ከተተው መለስ ላያደርገው

የትላንቱን ጨቋኝ የባለ ራእዩን ሰው

የእፉኝትን ልጅ እባብ  የባቡን ልጅ እባብ

እንዲህ አይነቱን ሰው እንዲ እያወደሱ እና እያቆለጳጰሱ ማኖር እና እነርሱም ዘመናቸውን ማራዘም የወደዱት የወያኔ ትቢያዎች እና ጀሌዎች በአምላክ ስም መሳለቃቸው ምንድን ነው  ?ምን ሊባልላቸው ይፈልጉ ነበር ? “ኢትዮጵያ አገራችንን እና ህዝቧን እግዚአብሄር በበረከት ይጎብኛት “ ወይስ ታላቁ የህዳሴ መሪን ማቹን መለስን እግዚአብሄር ይጎብኝ “?ይትኛው ይልቃል?

“የተማረ ሳይሆን የተባረከ መሪ አምላክ ይስጠን” ቴዲ አፍሮ

አሁንም እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ !

አመሰግናለሁ !

 

ማሳሰቢያ፤በዌብሳይታችን ላይ ለሚወጡ ማናቸውም ጽሁፎች ቀዳሚ የሆነ የዌብሳይታችንን አርትኦት ስራን ለማክበር ሲባል በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በማለዳ ታይምስ የመረጃ ማእከል ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የማለዳ ታይምስ የመረጃ ማእከል ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዌብሳይቱን  ጠቋሚ (አመልካች ) (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.maledatimes.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን(የማለዳ ታይምስ ህግና ደንብ በንግድ በተመዘገቡበት ሁለት አገሮች የረቀቀ ሲሆን በሁለቱም አገሮች አንድ አይነት የሆነ አሰራር ይዞ ይከተላል ።ይህንን ህግ ማንኛውም ሰው መቅዳት የማይችል መሆኑን እንገልጻለን።ንብረትነቱ እና ህገ ደንቡ የማለዳ ታይምስ ብቻ ነው!)፡፡ይህ ካልሆነ ግን በህገ ደንባችን መሰረት አስፈላጊውን የህጋዊ ጥያቄ ለማቅረብ የምንገደድ መሆኑን እንጠቁማለን::በዚህ አጋጣሚ በግለሰብ ለሚላኩ ጽሁፎች ሁሉ ተጠያቂው ስሙ የተገለጸው ግለሰብ እንጂ የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ሃላፊነቱን እንደማይወስድ እናሳስባለን ::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 19, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 19, 2012 @ 9:20 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar