www.maledatimes.com ወንዙን የሚያሻግር ጥቂት ምክር (ተመስገን ደሳለኝ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ወንዙን የሚያሻግር ጥቂት ምክር (ተመስገን ደሳለኝ)

By   /   October 19, 2012  /   Comments Off on ወንዙን የሚያሻግር ጥቂት ምክር (ተመስገን ደሳለኝ)

    Print       Email
0 0
Read Time:11 Minute, 1 Second

ወንዙን የሚያሻግር ጥቂት ምክር (ተመስገን ደሳለኝ)

(ተመስገን ደሳለኝ፣ “ከመለስ በሁዋላስ?” በሚል ርእስ ካቀረበው ፅሁፍ የመጨረሻው አንቀፅ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ምን አልባት ድፍረቱ ካላቸውከህወሓት እና ብአዴን ‹‹የስልጣን እገታ›› ወደ አርነት የሚመሩየፖለቲካ መንገድ ማግኘት ላይቸገሩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በዋናነትየአጋቾቹ ጉልበት በሰራዊቱ እና በደህንነት ላይ የተመሰረተ መሆኑንአጢነው ‹‹የጠቅላይ ሚኒስቴር መንበራቸው››ን ስልታዊ ሆነውመጠቀም ከቻሉ ወንዙን ለመሻገር አይቸገሩም፡፡

በአናቱም አቶ መለስ ደህንነቱን እና ሰራዊቱን ሙሉ በሙሉ በግላቸውከመቆጣጠራቸው በፊት (ከ1983ዓ.ም. -1993 ዓ.ም.) የ‹‹ጉልበተኛ ጓደኞቻቸውንአቅም›› ያፍረከረኩት መንግሥታዊ ስልጣናቸውን በመጠቀም በመሆኑ ከእሳቸውስልት (ከመለስ አጠገብ ሆኜ ብዙ ተምሬአለሁ እንደሚለት) ትምህርት ወስደው ከሆነለብልህነታቸው እና ለአርቆ አሳቢነታቸው አድናቆት አለኝ፡፡
እንዲሁም ሕገ-መንግሥቱን በሚገባ ለመተግበር ከቆረጡም በራሱ በህገ- መንግስቱጡንቻቸው ከተገዳዳሪዎቻቸው ሊበረታ የሚችልበትን ዕድል አያጡም፡፡ ይኸውምበህገ መንግሥቱ ‹‹የመከላከያ መርሆች›› በሚል በአንቀጽ 87፣ በቁጥር 1 ላይ፡- ‹‹የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔሮች የብሔረሰቦች እና የህዝቦችን ሚዛናዊተፅዕኖ__ ያካተተ ይሆናል›› የሚለውን ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡ እናም ይህ አንቀጽይከበር ዘንድ ሠራዊቱ የብሔር ተዋፅኦን እንዲጠበቅ ‹‹የመዋቅር ማስተካከያ›› ካደረጉከሕገ-መንግሥቱ ይልቅ ለፓርቲ ታማኝ በሆነው ሠራዊት ላይ ድንገት ደርሰው የሀይልሚዛኑን ማመጣጠን አይከብዳቸውም፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ የተጠቀሰውየህገ-መንግሥቱ አንቀፅም ድጋፍ ይሰጣቸዋል፡፡

በእርግጥ ይህንን ማድረግ ‹‹ራስንም ማደን›› መሆኑ የሚገባን አቶ መለስ ህይወታቸውካለፈ በኋላ እና ተተኪያቸው ከመመረጡ በፊት በእሽቅድምድም ለ34 ኮሎኔሎችየተሠጠውን የብርጋዴል ጄኔራልነት ማዕረግ ከህጋዊነቱ አንፃር ስናየው ነው፡፡ምክንያቱም ህገ-መንግሥቱ የጄኔራል ማዕረግ በምን መልኩ ሊሰጥ እንደሚገባውይደነግጋል፡፡ ‹‹የፕሬዘዳንቱ ሥልጣንና ተግባር›› በሚለው ክፍል አንቀጽ 71 ቁጥር 6ላይ እንዲህ ይላል፡- ‹‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በህግ በተወሰነው መሠረትከፍተኛ የውትድርና ማዕረጎችን ይሰጣል›› ኃይለማርያም ሊያነሱት የሚችሉት ጥያቄም‹‹የ34ቱ ጄኔራሎች ሹመት በማን አቅራቢነት የተካሄደ ነው?›› የሚል ይሆናል፡፡ሆኖም ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚጠበቅባቸው ጥያቄ ማንሳት ብቻ ሳይሆን ከሹመቱአንድምታ ተነስተው በሰራዊቱ ለመጠቀም የሚሞክረው ኃይል ምን ያህል ደፋርእንደሆነ መረዳትም ይኖርባቸዋል፡፡ (በነገራችን ላይ ይህን ሹመት በህወሓት እናበብአዴን መካከል ተከሰተ ከተባለው ከስልጣን ፉክክር ጋር የሚያያይዙት የፖለቲካተንታኞች አሉ) ሌላው ኃይለማርያም ስልጣናቸውን ከዕገታ ነፃ ሊያወጡ የሚችሉበትአማራጭ ከፓርቲው ይልቅ (በይበልጥ) መንግሥታዊ ስርዓቱን በመጠቀም ሊሆንይችላል፡፡ እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት እጅግ ጠንካራ እናሚሊተራይዝድ ሆኖ የተዋቀረ ነው፡፡ ይህን የሚያውቅ መሪ ደግሞ ከላይ እስከ ቀበሌድረስ ማዘዝ የሚቻልበትን ልማድ በሚገባ ይተገብራል፡፡ ይህን ዓይነቱን መንግሥታዊመዋቅር የወረሱት አቶ መለስም በ1993ቱ ክፍፍል ወቅት ተገዳዳሪዎቻቸው በፓርቲህገ-ደንቦች አጥረው ሊያቆሟቸው ሲሞክሩ እርሳቸው ግን ይህን ተሻግረውመንግስታዊ መዋቅሩን በመጠቀም (ለስዬ ፍርድ ቤትን እንደተጠቀሙት) የሃይልትንቅንቁን ተሻግረዋል። ኃይለማርያምም ይህን ሊያደርጉ የሚችሉበት ዕድል ሊኖርይችላል፡፡ እርግጥ ነው ይህን ማድረግ የሚችሉት ጥቂት ዓመታት ሀገሪቷን መምራትሲችሉ ብቻ ነው፡፡ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ወንዙን መሻገር ከቻሉ ደግሞ ገላጣው ሜዳላይ ይደርሳሉ፡፡ ተጨማሪ የመለስን ስልትም ያገኛሉ፡፡ መለስ ከዚህ በፊት የውስጣዊኃይል መደላደላቸውን ከፓርቲ ፓርቲ ሲቀያይሩ ሚሊተሪውን እና ደህንነቱንም እንዲሁእያፈራረቁ የተጠቀሙበትን ማለቴ ነው፡፡
በአናቱም ሊጫኗቸው የሚሞክሩትንም እንዲሁ መለስ እንዳደረጉት ‹‹ግራ-ዘመምጠባብ ብሄርተኞች ናቸው›› የምትል ካርድ ለምዕራባውያኑ ማሳየት ይችላሉ(ምዕራባውያኑ ኃይለማርያምን Pragmatic፣ ነባሮቹን ደግሞ ማቻቻል የማያውቁከሚሉት አንፃር) እንግዲህ መጪዎቹ ጊዜያቶች ለኃይለማርያምም ሆነ ለነባር ታጋዮቹፈታኝ ይሆናሉ ብሎ መገምት አያስቸግርም፡፡ ከምንም በላይ እንዲህ ዘግይቶም ቢሆንኢህአዴግ የእኛን የዜጎቹን ድምፅ መስማት ቢጀምር እጅግ የተሻለ እንደሆነምማስታወስ ያሻል፡፡
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 19, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 19, 2012 @ 9:06 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar