አሰሪዎቻን ገድለሻል በሚል ክስ የተመሰረተባት ኢትዮጵያዊት በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት በኩዌት ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ ቅጣት የተጣለባት ሲሆን ፣በኩዌት የሚገኘው የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተከክርስቲያን መስተዳድር በወጣቷ እምነት መሰረት ንሰሃ እንድትገባ እና ቃለ ኑዛዜ እንድትሰጥ ከፍረድቤቱ ጋር በመነጋገር የመጨረሻ ቃሏን የተቀበሉ መሆኑን ከፍካት የስደተኞች መረዳጃ ማህበር በኩዌት ያደረሱን ዘገባ ያመለክታል ።
የኢተዮጵያዊቷ ማንነት ለቤተሰብ ደህንነት ሲባል በወቅቱ እንዲገለፅ ባይፈቀድምበተፈረደባት የሞተ ፍርዱ ተፈፃሚነቱ በጣመ አሰቃቂ ከመሆኑም በላይ ለእያንዳንዳችን ዜጎች ከፈተኛ ሰቆቃን እና ፍርሃትን ፈጥሮብናል ሲሉ የገልፃሉ።
በተለይም በአሁን ሰአት ማንመ አይዞአችሁ ባይ በሌለበት እና መንግስትም ለስደተኞች ትኩረት በማይሰጥበት በዚህ አስከፊ ወቅት እንደዚህ አይነቱ እርምጃ መወሰዱ የአረቦች አሰቃቂ እና ገፋዊ እርምጃ እንዲበረታ እና ስደተኞችን ለአላስፈላጊ ወንጀል እንዲገፋፉ ያደርጋል ሲሉ የገለፁ ሲሆን ፣የኢትዮጵያ መንግስት በወጣቷ ክስ ላይ አስመልክቶ የመከላከያ ምስክር ለማቅረብ እንድትችል አለማድረጉም ሆነ ወንጀሉን የፈፀመችበትን ዋነኛ አላማ ምን አይነት አሰቃቂ የሆነ ግፍ ደርሶባት የግድያ ወንጀሉን ለማጣራት አለመሞከሩ እራሱ ለስደተኞች ህልውና የማይሰጥ መስሪያቤት እንደሆነ ያሳያል ሲሉ ገልፀዋል ።የህንንም ለመረዳት በአለም ደቻሳም ላይ ከአመታት በፊት በኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊትበቤይሩት የደረሰውን ግፋዊ ሰቆቃ ማስታወስ እና ኤምባሲውን መውቀስ ተገቢ ነው ሲሉ አክለው ገልፀዋል።
ይህ ዜና የማለዳ ታይምስ ነው ፣መቅዳት ከፈለጉ ምንጭዎን ከመጠቆም አይቦዝኑ ፣የሰዎችንም ስራ ያክብሩ!
Average Rating