www.maledatimes.com በአማራ ክልል 35 አይነት ለጤና አደገኛ ኬሚካሎች ህብረተሰቡ ወደ ሚጠቀምባቸው ወንዞችና መስኮች እንደሚለቀቁ ተገለጸ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በአማራ ክልል 35 አይነት ለጤና አደገኛ ኬሚካሎች ህብረተሰቡ ወደ ሚጠቀምባቸው ወንዞችና መስኮች እንደሚለቀቁ ተገለጸ

By   /   February 27, 2017  /   Comments Off on በአማራ ክልል 35 አይነት ለጤና አደገኛ ኬሚካሎች ህብረተሰቡ ወደ ሚጠቀምባቸው ወንዞችና መስኮች እንደሚለቀቁ ተገለጸ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 3 Second

ዘርይሁን ሹመቴ

በኮምቦልቻ በደብረብርሃንና በተለያዩ የአማራ ከተሞች የሚኖሩ በርካታ ህዝቦች ከፋብሪካ በሚወጣ አደገኛ የኬሚካል ልቀት በመተንፈሻ ችግር በሽታ መጠቃታቸው ተገልጸ።

ከፋብሪካዎቹ በሚለቀቁት መርዛማ ኬሚካሎች ምክንያት ለፈውስ አልባ በሽታ የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መሆኑንም መረዳት ተችሏል።

የአማራ ክልል መስተዳድር ባህርዳር

ከፍተኛ ጉዳት እያስከተሉ ያሉት የቆዳ ፋብሪካዎች በባህርዳር፣ መርሳ፣ ሃይቅ፣ ኮምቦልቻና ደብረብርሃን ከተሞች የሚገኙ ሲሆን፣ ሁሉም ፋብሪካዎች አገር አቀፍ እና አለማቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ደረጃን በመተላለፍ የሚያፈሱት ኬሚካል ለበርካታ ሰዎች እና እንስሳት ህመምና ሞት ምክንያት እየሆኑ ይገኛሉ።

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከቆዳ ፋብሪካዎች የሚወጡ ኬሚካሎች የልቀት መጠናቸው ከፍተኛ በመሆኑ በአከባቢው የሚኖሩ ህዝቦች ለካንሰር፣ የዘረመል ለውጥ፣ ለአእምሮ ዝግመት፣ ለአካል መዛባት ፣ ተጣብቆ የመወለድና ለባህሪ ለውጥ ችግር ተጋላጭ ይሆናሉ።

በአማራ ክልል የተቋቋሙት ስድስቱ ፋብሪካዎች ደካማ የኬሚካል ማከሚያ መሳሪያ እና አያያዝ ያላቸው መሆኑ በጥናት ተረጋግጧል።ፋብሪካዎቹ ከሚያመነጩት በካይ ተረፈ ምርት ውስጥ ተጣርቶ ወደ አከባቢው የሚለቀቀው 35 በመቶው ብቻ እንደሆነና አንዳንዶች ደግሞ ምንም ማጣሪያ የሌላቸው መሆናቸው ታውቋል::

በደብረ ብርሃን ከተማ ከሚገኘው የጥቁር ዓባይ ቆዳ ፋብሪካ በሚወጣ ብናኝና ሽታ በመጠቃታቸው ልሳናቸው እስከ መዘጋት የደረሱ ነዋሪዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን እንዳረጋገጠ ትንሳኤ ሬዲዮ ዘግቧል።

በመተንፈሻ ችግር በሽታ የተጠቁትንም በርካቶች እንደሆኑ ከየስፍራዎቹ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የቆዳ ፋብሪካዎች ከ35 አይነት በላይ ለጤና አደገኛ የሆኑ ኬሚካሎችን ህብረተሰቡ ወደ ሚጠቀምባቸው ወንዞችና መስኮች እንደሚለቀቁም ታውቋል።

ችግሩ እንዲፈታ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ አቤት ቢሉም መፍትሄ የሚሰጣቸው አካል እንዳላገኙ ይናገራሉ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on February 27, 2017
  • By:
  • Last Modified: February 27, 2017 @ 10:55 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar