0
0
Read Time:43 Second
ሙሉቀን ተስፋው
በደሴ ከተማ የመንግሥት አስተዳደር አካላት በነፍስ ወከፍ ዐሥር ሺህ (10000.00) ብር በመቀበል በወሎ ዩንቨርሲቲ አቅራቢያ ቀለም ሜዳ በተባለው አካባቢ ቦታ ተሰጥቷቸው ቤት የሠሩ ሰዎች ዛሬ ቤቱ እንዲፈርስ በመደረጉ ነው በሕዝብና በመንግሥት የጸጥታ አካላት መካከል ግጭት የፈጠረው፡፡
የደሴ ከተማ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ሕገ ወጡን የቤት ማፍረስ ሥራ የተቃወመ ሲሆን በመካከል የወያኔ የታጠቁ ወታደሮች 5 ሰዎችን አቁስለዋል ብሏል የደረሰን ሪፖርት፡፡ ጉዳዩን የተከታተሉ ሰዎች እንደነገሩን ከሆነ በጥይት የተመቱት ሰዎች የሆስፒታል ክትትል ቢደረግላቸውም አስጊ ሁኔታ ላይ ያሉ አሉ ተብሏል፡፡ ከተመቱት ሰዎች መካከል የእስልምና እምነት አባቶችም አሉበት ተብሏል፡፡ በተያያዘም በዚሁ በቀለም ሜዳ የ6 ሰዎች ቤት በአፍራሽ መኪና የፈረሰ ሲሆን የሕዝብ ቁጣ ከፍተኛ በመሆኑ የሌሎች ግለሰቦች ቤት ከመፍረስ ድኗል ለጊዜው፡፡ ነገ ተጨማሪ የወያኔ አፍራሽ ግብረ ኃይል ይመጣል በመባሉ ሕዝብ በተጠንቀቅ ላይ እንደሆነም ለማወቅ ችለናል፡፡
በሌላ በኩል በኮምቦልቻ ፍርድ ቤት አንድ የወያኔ አቃቢ ሕግ ችሎት ላይ በጥይት ተስቷል ተብሏል፡፡ አቃቢ ሕጉ በሐሰት ወጣቶችን የሚያሳስር በመሆኑ ነው እርምጃ ሊወሰድበት የነበረው፡፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating