www.maledatimes.com መሪራስ አማን በላይ በስድሳ አምስት ዓመታቸው አረፉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

መሪራስ አማን በላይ በስድሳ አምስት ዓመታቸው አረፉ

By   /   March 4, 2017  /   Comments Off on መሪራስ አማን በላይ በስድሳ አምስት ዓመታቸው አረፉ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 15 Second

ኢዛ (ዓርብ የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Mar. 3, 2017)፦ የተከበሩት ባለታሪክ፣ ፈላስፋ፣ ባለመድኃኒት፣ የነገረ-መለኮት አዋቂ እና የ24 መጻሕፍት ደራሲ የነበሩት መሪራስ አማን በላይ ባደረባቸው ሕመምየካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. ፌብሩዋሪ 17 ቀን 2017) በሎስ አንጀለስ ከተማ በተወለዱ በ65 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ተለዩ።

መሪራስ አማን የተወለዱት መጋቢት ፳፫ ቀን ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. አፕሪል 1 ቀን 1951 ዓመተ ምህረት) ሲሆን፣ የትውልዳቸው ስፍራቸው በለሳ ተብሎ በሚጠራና ጎንደር ውስጥ በሚገኘ አካባቢ ነበር።የአደጉትም በጎንደር እና በጎጃም ውስጥ እንደነበር ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረገጽ ዝግጅት ክፍል የደረሰው ዘገባ ያስረዳል።

ከልጅነታቸው ጀምሮ ትምህርታቸውን የቀሰሙት ከአባታቸው ከመምህር በላይ ድሉ፣ ከአባ ጼሄማ በጎንደር ተክለኃይማኖት፣ ከመሪጌታ መንክር ደብረኤልያስ ጎጃም፣ ከመሪጌታ ጉባኤ በጎጃም ነበር። መሪራስ አማን፤ቅዳሴን፣ ቅኔን፣ ዜማን፣ ብሉይን፣ ሃዲስን፣ የእንጨት አዋጅን (የመድኃኒት እጽዋትን)፣ የሃረግ ስዕልን፣ የኢትዮጵን ታሪክ፣ አቡሻህርን (ባህረሃሳብን) እና ሌሎችንም በአድባራት እና ገዳማት የሚሰጡ የኢትዮጵያትምህርቶችን ተምረዋል። በለተይ በቅኔ፣ በግስ ርባታ እና ሰዋሰው ችሎታቸው በመምህራኖቻቸው እና የትምሀርት ባልንጀሮቻቸው ስማቸው የተጠራ ነበር። በዚህም ምክንያት በጎጃም በይስማ ደጀን በመሪጌታመንክር ዘንድ ቅኔ አስነጋሪ ነበሩ።

ተማሪ ሳሉ እና ትምህርታቸውንም ካጠናቀቁ በኋላ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተዘዋወሩ አያሌ ገዳማትን እና አድባራትን እየጎበኙ በውስጣቸው የአሉትን ምስጢራዊና ጥንታዊ መጻሕፍቶቻችንን ለመመርመር እድልአግኝተዋል።

የ19 ዓመት ልጅ ኹነው ወደ ኑብያ (ሱዳን) ተጉዘው በነበረበት ወቅት በአንድ በፈራረሰ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቤተክተርስቲያን ቅጥር ግቢ በተቀበረ የድንጋይ ሳጥን ውስጥ፣ ምናልባት ኢትዮጵያ ውስጥ የሌሉየኢትዮጵያን ታሪክ ጨምሮ ስለተለያዩ ጉዳዮች የሚዘረዝሩ በግዕዝ የተጻፉ የብራና መጻሕፍትና ጥቅሎች አግኝተዋል። እነዚህን መጻሕፍት ያገኙት የዛሬ 50 ዓመት አካባቢ ነበር። መጻሕፈቱ በግዕዝ የተደረሱ ነበሩ።በእነዚህ መጻሕፍት ላይ ተመርኩዘው ይዘታቸውን እያሳጠሩ ከ24 ያላነሱ መጻሕፍትን አሳትመው፣ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን በእውቀትና በጥበብ አንጸዋል።

መሪራስ አማን በላይ መጽሐፍ ከማንበብና ከመጻፍ በላይ ሌላ ሕይወት አልነበራቸውም። ሲጽፉም እጅግ ፈጣን እንደነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸው ወገኖች ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረገጽ ዝግጅት ክፍል ገልጠዋል።በራሳቸው የተመዘገቡት የመጻሕፍቱም ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው።

  1. ምዕራፈ ሕያዋን ቃለ ሕይወት ዘወንጌላውያን የምሳሌው ምስጢር በሐተታና በትንተና
  2. የጥንትዋ ኢትዮጵያ ትንሳዔ ታሪክ
  3. የሱባ ቋንቋ መዝገበ-ቃላት
  4. መጽሐፈ ብሩክ (ብሩክ ዣንሽዋ)
  5. መጽሐፈ ክቡር
  6. መጽሐፈ ሱባኤ ዘበአማን ካልእ
  7. መጽሐፈ አብርሂት
  8. መክሰተ ምስጢር
  9. መጽሐፈ እንቆአእባን
  10. መጽሐፈ ሠረገላ ታቦር
  11. መርሐ ጽድቅ ወአሚን ወመርሐ ግብር
  12. መጽሐፈ ፈውስ
  13. መጽሐፈ አድህኖት
  14. ብርሃነ ሕይወት ዘበአማን
  1. መጽሀሠይፈ ኃይማኖት ተዋህዶ
  2. ሕይወት እንደገና በሦስት ዐለሞች
  3. በአንድ ሰውነት የሦስት አካላት ምስጢር
  4. መጽሐፈ ኤልያስ ነቢየ እግዚአብሔር
  5. የእውነትን ሕይወት ውደዱ
  6. አፍሪ-ካሁን
  7. ጥበብ ከእውቀት ትምህርት ከልጅነት
  8. የልቤ ወዳጅ የሰው ዘር ልጅ
  9. ጸሎት አሚን ዘበአማን ወጸሎተ ተዋህዶ
  10. ምክር ከእኔ ስማ አንተ ወገኔ

መሪራስ አማን በላይ፣ በሀገር ፍቅር የሚነዱ፣ ለኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ቀናኢ፣ ለኢትዮጵያ እውነተኛ ታሪክ መገለጥና መዛመት የሚተጉ እና በፍቅረ ንዋይ ያልተነደፉ ትልቅ ጠቢብ ነበሩ። ጥበብንለአገራቸው ሕዝብ ለማቅሰም ወደኋላ አይሉም ነበር። ለአገራቸው እስከዛሬ ካበረከቱት በላይ ገና ብዙ አስተዋጽኦ ለማድረግ ቢያቅዱም የማይቀረው ሞት ቀደማቸው። ይህም በመሆኑ፣ ራሱ የእውቀት ዩኒቨርሲቲየሆነ አንድ ትልቅ ሰው ኢትዮጵያ አጥታለች። 3

 

መሪራስ አማን በላይ የስድስት ልጆች አባት ነበሩ። በልጆቻቸው ውስጥ፣ በብርቅዬ መጻሕፍቶቸው እና በሚወዱአቸው ኢትዮጵያውያን ልቦች ውስጥ ይኖራሉ። እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያኑራት ዘንድ የዝግጅት ክፍላችን ይመኛል።ለቤተሰቦቻቸው፣ ለዘመድ ወዳጆቻቸው እና ለመላው አፍቃሪዎቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on March 4, 2017
  • By:
  • Last Modified: March 4, 2017 @ 10:19 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar