0
0
Read Time:38 Second
የቀድሞ አንድነት ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ፤ አሁን ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት ፤ አቶ ነገሠ ተፋረደኝ በማዕከላዊ ታስረው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል ። – አቶ ነገሠ በትላንትናው ዕለት ፣ አራዳ ጊዬርጊስ ቤተ የክርስቲያን፣ እብስተ መና ካፊ ውስጥ በደህንነቶች ክትትል ይደረግባቸው እንደነበር አብሯቸው የነበረ የዓይን ምስክር የገለፀ ሲሆን፤ ደህንነቶቹ በተንቀሳቃሽ የእጅ ስልካቸው ፎቶ ግራፍ ካነሳቸው በኋል ፤ ከካፊው ወጥተው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ፣ መንገድ ላይ አስቁመው ይዞቸዋል ። አቶ ነገሠ የታሰሩበት ምክንያት እስካሁን ያልተገለጸ ሲሆን ፣ይህ መረጃ ይፋ እስከ ሆነበት ሰዓት ድረስ በማዕከላዊ ታስረው ይገኛሉ።
ያለ ፍርድቤት ትእዛዝ እና ደህንነቶች በፈለጉበት ወቅት የሚፈለገውንም ሆነ የማይፈለገውን ሰው ፣እነርሱ ባሰኛቸው እና ስልጣኑ በማይፈቅድላቸው መንገድ ፣ግለሰቦችን ጭምር በማስቆም ችግር እንደሚፈጥሩ ተገልጾአል ፣ የመንግስትን ስልጣን ያለአግባብ በማዋል ከፍተኛውን ጫና በሃገር ላይ ከሚያደርሱት ደህንነቶች መካከል የኢትዮጵያዎቹ ደህንነቶች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ !!
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating