www.maledatimes.com የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እና የህዝቡ ዝምታ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እና የህዝቡ ዝምታ

By   /   March 30, 2017  /   Comments Off on የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እና የህዝቡ ዝምታ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 4 Second
               

State OF Emergency declare by TPLF

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ብዙዎቻችን የተለያዩ አስተያየቶችን ስንሰጥ ቆይተናል ሆኖም ግን ማህበረሰባችን በሃገሩ ላይ እያለ ዝምታውን የመረጠበት ዋነኛ ምክንያት ለለውጥ የሚያነሳሳው የፖለቲካ ፓርቲ ስለሌለ ሳይሆን ፤ በፖለቲካ ፓርቲዎች ባለመተማመኑ እና ብዙ ጊዜ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጊዜአዊ ስሜታቸውን ከተነፈሱ በኋላ ለሚመጣው ማንኛውም ነገሮች ሃላፊነታቸውን መውሰድ ስለማይፈልጉ እና ለለውጥ ጥረት ስለማያደርጉ ማህበረሰቡም እምነቱን እና የለውጥ ጥረቱን እርግፍ አድርጎ ከተወው አስር አመታትን ይዞአል ። ነገር ግን በየትኛውም ክልል ትክክለኛ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲ አለ ለማለት አያስችልም እንዲያውም ዘርን ከዘር የሚያጋጭ ሃገርን ከሃገር የሚከፋፍል ሃሳብ የያዙ የትየለሌ የፖለቲካ ድርጅቶች አሉ እነዚያም አቋማቸውን እንኳን ለይተውት አያውቁም ፣ከገዥው መግስት ጀምሮ እስከ ክልል መስተዳድር ስር የተዋቀሩት የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ በብሄር የተዋቀሩት ለገዥ መደብነት የሚሯሯጡ ዘረኞች ማለት ነው ።

በተለይም ከምርጫ ፱፯ በኋላ የሚከሰቱት የተለያዩ የተቃውሞ ሰልፎች በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ንጹሃንን እንደ እንሰሳ በመንገድ ላይ በማጋደም ፣ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት በማጥፋት ፣ ያለውን ስርአት እድሜው እንዲራዘም አድርጎታል ። ይህ ደግሞ ትልቁ የፖለቲካ ፓርቲዎች አለመስማማታቸው እና የህዝቡ ስሜት እና የሃገራዊ ፍቅር ሳይሆን የግለሰባዊ የስልጣን እና የመዋእለ ንዋይ የፍላጎት መናር ለመንግስት እንዲጠቅመው አድርጎታል ፣ምን ያህል ፍላጎት እንዳላቸው እና ምን እንደሚፈልጉ ጥቅማቸው ምን እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቀዋል ።
ይህም ብቻም አይደለም ዘር ከዘር ተናክሰው እርስ በእራሳቸው እንዳይስማሙ ያደረጋቸው አንድ የተለየ ነገር ያለ ይመስላል ሆኖም ያ ጉዳይ ሳይሆን ሁሉም የስልጣን ጥመኝነቱን ለየቅል ይዞት ስለተጓዘ እና የሃገሪቱን አንድነት እና የበላይነት ሳያረጋግጡ ቅድሚያ ለእራሳቸው ማንነት ስለሚቀድሙ ይህንን አመለካከታቸውን ደግሞ ከእራሱ ከወያኔ ስር ሆነው ስለሚገለገሉበት እና ወያኔ የቀረጸውን ይህንን የዘረኝነትን አጀንዳ እራሳቸው ስለሚተገብሩት ማናቸውም የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ የሚሆኑበት እና በአንድነት ትግል የሚያካሂዱበት አጀንዳ ሊኖራቸው አይችልም ።
 
ስለዚህ ህዝብ ማለት ሃገር ነው ሃገርም ህዝብ ነው ስለ ህዝብ እና ሃገራችን ካልተቆረቆርን ስለሌላው ነገር ምንም ስሜት ሊኖረን አይችልም ፣ የጋምቤላ ህዝብ ቁስል ካላመመን ፣ስለ ኦሮሞው ልናነሳ አንችልም ፣የሺናሻው መጨቆን ካልገባን ስለ አማራው መበደል ማውራቱ ተገቢ አይደለም እያንዳንዱ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ ዜጋ ነው ሰው ስለ ሃገሩ እና በጠቅላላው ዜጋው የማይቆረቆር ከሆነ ስለ ሃገሩ አያስብም ማለት ነው ። ስለዚህ በተለያዩ አቅጣጫ ለሃገራችን ትግል በየጦር ግምባሩ አለን እያሉ ዲስኩር የሚነፉን የጦር ሃይሎችም ሆነ ፣ እንደ አቀንጭራ ትል ሃገራችንን ከስር መሰረቷ እየመዘመዘ የሚበላት የወያኔ መንግስትም ስለ ሃገራችን ኢትዮጵያ ሳይሆን ስለ ግል ጥቅማቸው እና ስለአለሙለት እና ስለተመኙት አናሳ ብሄራቸው ስሜት የሚገዛቸው ፣የዘመኑ አተላዎች መሆናቸውን እናውቃለን .ስለዚህ የወያኔ መንግስት እንደልቡ የሚፈነጭበት እና እንደ ፈለገው በፓርላማ ውስጥ ህግጋቱን የሚለዋውጠው ሃገሪቱን ወደ አንድ አቅጣጫ የሚለውጥ ሃያል የሆነ የፖለቲካ ድርጅት እና ለህዝቡ እና ለሃገሩ አንድ አቋም ያለው ሰራዊት ባለመኖሩ የተነሳ ስለሆነ ፣የታፈነው የህዝብ ስሜት ቁጣውን ገልጾ በአንድነት እና በህብረት ወደ ቤተ መንግስት የጎረፈ ቀን ዛሬ በዘር እየጠሩ እና እየከፋፈሉ አንተ ኦሮሞነህ አንተ አማራ እንተ እንዲህ ነህ እያሉ ዘሮችን በማሳነስ እና የትግራይ ህዝብ ብቻ ሃያል ነው ብለው የሚያምኑትን እነዚያን የአሞራ ውላጆች ምን ሊደርሱ እንደሚችሉ መገመት አያቅትም ፣ ህዝብም የሃገሩን ምንንነት ጠንቅቆ ስለሚያውቅ እና ስለሚረዳ እንጂ ለሚመጣው የሃገሪቱ ትልቅ ቀውስ እና የእርስ በእርስ ግጭት ክፋቱን ስላጤነው ዝምታን መምረጡ ፣ትውልድን ለማዳን ሲል ዝምታን አሁንም መምረጡ ዛሬ
ስለዚህ ማናቸውም በሃገሩቱም ሆነ በውጭ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ያላቸውን ሰፊ የጥቅም ልዩነቶች ወደ ኋላ በመተው የሃገሪቱን የወደፊት እጣ ፈንታ ብቻ በማስተዋል ፣ሃገሩን ሊረከብ የሚችል ትውልድ እና ነገም የሃገር ተረካቢው ትውልድ የሰላም ተሻጋሪ ትውልድ እንዲፈጥር ዘንድ ፣በየ መንገዱ ከመጮህ እና በነጮች በር ላይ ከማጎብደድ ይልቅ ፣በራሳችሁ ቤት ሰላምን መዝራት የምትችሉት የአንድነት ሃይልን በጋራ በመመስረት እና አላማችሁን አንድ በማድረግ ብቻ ነው ።
የሃገርን እና የህዝብን ክብር እና ሰላም በማያስቡ ጨለምተኛ የመገናኛ ሚዲያዎች ከሚዘሩት የዘረኝነት መንፈስ በመውጣት እና የጋዜጠኝነት ህግ እና ስርአትን በተሞሉ ለሙያቸው ክብር እንጂ ለፖለቲከኞች ጉልበት ያላጎበደዱ ጋዜጠኞችን በማፍራት እውነተኛውን የሃገራችንን መስመር ወ ቀደምቷ ኢትዮጵያ መልሰን አንድነታችንን የምናጠነክርበት የሃገራችንን ሰላም የምንዘራበት የህዝባችንን ደስታ የምንመልስበት ፣ እንዲሁም ለሃያ ስድስት አመታት የተዘራውን የዘረኝነት ክፋት የምናስወግድበት አገር በጋራ መገንባቱ ጠቃሚ ሲሆን ህዝባችንም ይህንን ካመነበት ወደ ትግሉ ጎራ ተቀላቅሎ በአሁን ሰአት ያለውን ሞናርኪ ለማስወገድ ቀላል የሆነ የህዝብ መሳሪያ ልንጠቀም ይገባል ። ይህም ሊሆን የሚችለው በዋሽንገተን ዲሲ አደባባይ ላይ በመጮህ ሳይሆነ በሃገራችን ከህዝባችን ጋር በጋራ በመታገል ለለውጥ መነሳት እና የሚደርሱብንን መከራ እና ስቃይ አብረን በመቅመስ መሆን አለበት ባይ ነኝ !!
ማእላፍ ይርጋ
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on March 30, 2017
  • By:
  • Last Modified: March 30, 2017 @ 12:59 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar