www.maledatimes.com ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ሃብታሙ አያሌው በእስር ቤት ያሉት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ሰበአዊ መብታቸው ያሳስበናል ህልውናቸው ያስጨንቀናል! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ሃብታሙ አያሌው በእስር ቤት ያሉት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ሰበአዊ መብታቸው ያሳስበናል ህልውናቸው ያስጨንቀናል!

By   /   June 6, 2017  /   Comments Off on ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ሃብታሙ አያሌው በእስር ቤት ያሉት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ሰበአዊ መብታቸው ያሳስበናል ህልውናቸው ያስጨንቀናል!

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 28 Second

ተጻፈ በዘለአለም ገብሬ  ፮/፮/፩፯

በመጀመሪያ እንደማንኛውም ሰው ፣ ሰላምታዬን ላቅርብ !

ይህንን ግልጽ ደብዳቤ ለመጻፍ ያነሳሳኝ በዛሬው እለት ተለቆ የነበረውን የቪዲዮ ምስልህን በህዝብ እይታ እንዲቀርብ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃኖች እንዲለቀቁ ከተደረጉ በኋላ ፣ለተናገርካቸው ነገሮች ምናልባት ሰፋ ያለ እና ዘርዘር ያለ ሃሳብ መስጠት ባልችልም   ሆኖም ግን በጋዜጠኞች ጉዳይ ላይ ባነሳሃው ስድብ አዘል አስተያየት ስላልተዋጠልኝ እና ጋዜጠኛው በእስር ቤት ውስጥ ስትማቅቅ ለአንተ ስለ አንተ ቀን ከለሊት ሲጮህ የነበረ እና ስለ አንተ የድህንነትም ሆነ ፣የእስርቤት ውሎ፣ እንዲሁም የፍርድ ቤት የክትትል  ጊዜያትንም አስመልክቶ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይል ሲዘግብልህ ፣ሲጮህልህ ፣በመላው አለም ላለው ህዝብ ሲያሰማልህ የነበረ ፣መገናኛ ብዙሃን ነው ።

ሆኖም ግን የእናት ጡት ነካሽ መሆን ባይገባህም የእናት ጡት ነካሽ መሆንህን አንድ በአንድ እንዴት እንደሆነ የሚያውቀው ያውቀዋል ፣ ትላንት አንተ ስትታሰር ሰለአንተ የጮኸውን የመረጃ ማእከል ሁሉ ትንንሽ መንግስት ሆነዋል ብለህ አንደበትህን ሞልተህ ስትወርፋቸው ምንም አልሰቀጠጠህም ፣ ምክንያቱም አላማህ ሌላ እንደሆነ የተረዱት ጋዜጠኞች ምናልባት የምትሄድበት የፖለቲካ መንገድም ሆነ በገንዘብ እና  ሌሎች ተጓዳኝ ጉዳዮች የምትሄድበት የጥቀሙኝ መንገድ ሊያስኬድ እንደማይችላቸው ስለአወቁት መሆኑን ሳትረዳው የቀረህ አይመስለኝም።

ቁንጽል ሃሳብ ፩ 

እንደምሳሌ የተወሰኑ ነገሮችን መጥቀስ ካስፈለገ ፣ ወደ አሜሪካም እንድትመጣ ከጣሩት ሰዎች እና ዋነኛው ሰው አቶ አልዩ የተባሉት ግለሰብ እንደሆኑ ጠንቅቅቀህ ታውቀዋለህ ፣ ይህም በዚህ ሳለ ለህክምና የሚወጣውን ወጭዎች በሙሉ ፣ለሰላም እና ፍቅር ለሃገር አንድነት እና የህይወት ማዳን ስራ ፣ትጋቱን በማሳየት የማይሰለቸው የአውሮጳ ፣ካናዳ፣ስካንዲኔቪያን ሃገራት ስደተኞች እንዲሁም አውስትራሊያ፣ደቡብ አፍርካ እና በሌሎች ያሉ አለማት ያሉትን ስደተኞች በማስተባበር፣ያንተን ጤንነት ያስቸነቃቸውን ውድ ኢትዮጵያኖችን ከጉሮⶂቸው ላይ በመንጠቅ የአንተን ህይወት እንዲታደጉ በአውሮጳምም ፣አሜሪካም እስራኤልም ሆነ በሌላው አለማት ያሉት የነጻ ጋዜጠኞች መገናኛ ብዙሃኖች ብዙ አትተዋል ፣ብዙ ነገሮች ተጽፈው አንተን የምትድንበትን መንገድ ሲያሰሉ ከርመዋል፥ለዛሬም እንድትደርስ ካደረጉት ድርጅቶች ትልቁን ድርሻ ዛሬ እንደ እናትህ ጡት ነክሰህ ከንፈር ያስመጠጥክባቸው እነዚሁ ጋዜጠኞች ናቸው ።

 

ቁንጽል ሃሳብ ፪

ከእነ አቶ አልዩ ጋር በስፖንሰር አድራጊነት ስትመጣ የነበረው ሃላፊነት በእነርሱ ላይ ስለነበር ፣እያንዳንዳቸውን አስፈላጊ ነገሮች በእነርሱ በኩል መሟላት እንደሚገባው ስለሚያምኑ አንተን ለማሳከምም ሆነ ከእስር ቤት ስለወጣህ የሞራል ጉዳቱ እንዳይከፋብህ ለማድረግ ፣እነርሱ በሞራልም በአካልም በገንዘብም ትልቅ ድጋፍ በማድረግ እና በማስደረግ ጫናውን መፍጠራቸውን ገልጫለሁ ፣ሆኖም ግን በሰሜን አሜሪካ ሰለ አለው የፖለቲካ መናፈስ እና አዝማሚያው የማያዋጣ እንደሆነ ጠንቅቀው የተረዱት እነኢህ ግለሰቦች ህክምናህን ጨርሰህ ፣ምን ማድረግ እንዳለብህ ከአንተው ጋር በጋራ ሆነው ሲመክሩ እና ቀጣዩ ያለው በሃገራችን ውስጥ ያለውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሊረዳ የሚችለው እና የታሰሩ ፖለቲከኞችን ፣እንደ እነ በቀለ ገርባንም ሆነ እነ ዮናታን አለበለዚያም ጋዜጠኛ ኤልያስገብሩን እና ፓልደረቦቹን ፣እንዲሁም እስክንድር ነጋን ባሉበት ሊረዱ የሚችሉበት መስመር ለመዘርጋት ፣አንተ በቅርብ ስለመጣህ ይህንን የገንዘብ ማሰባሰብ በአንተ በኩል ስኬት ሊኖረው እንደሚችል ሃሳብ ሲቀርብልህም ሆነ በሰሜን አሜሪካ ስለ አለው የፖለቲካ ንፍሰት ስትነገር ተመልሼ ወደ ሃገሬ ገብቼ በሃገር ቤት ውስጥ ከአሉት ፖለቲከኞች ጋር እታገላለሁ ብለህ ማለትህ እና ከዚያም የገንዘብ ማሰባሰቡ ፕሮግራም እንዲጀመር አሻፈረኝ ብለህ  ማለትህ ምን ይሰማህ ይሆን?

ቁንጽል ሃሳብ ፫

ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በእስር ቤት ላሉት ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች የመረዳቱ ሁኔታ እንዳለ እንዲሆን እና እንዲቀጥል ፣ከህዝብ የተሰበሰበውን ገንዘብ ከአንተ የህክምና ወጭ የተረፈ በመሆኑ ለጋዜጠኞች ሆነ ለፖለቲከኞች ፣እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው ይላክ ስትባል አሻፈረኝ ይህ ለእኔ የተለመነ ገንዘብ ነው ብለህ ፣አንተ ለአላማ ቆሜለታለሁ ለምትለው ህዝብ ለቆሙት ሌሎች አንጡራ የኢትዮጵያ ልጆች እንደሽማ መቅለጥ ያልቻልክ ሰው በገንዘብ ስትሸነፍ እና ፣እነዚሁ የመገናኛ ብዙሃኖች ወደ አሜሪካ አምጥተው ጃኬት እንድትቀይር ስላደረጉህ  በህይወትህ ላይ በእስር ቤት ሳይሆን ከቀድሞ ጀምሮ አብሮህ የነበረውን የኪንታሮት በሽታ ከስርህ እንዲነቀል ጥረት ስላደረጉ ዘለፋውም ለምንስ ሆነ ? ያልሆነ የመዘባበቻ የቃላት ውርወራው ለምንስ አልስፈለገ?

ቁንጽል ሃሳብ ፬

ከዚህም በኋላ በእነ አቶ አልዩ የሚመራውንም ማህበርም ሆነ የገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴ ረግጠህ በመውጣት አንድ ትንሽዬ የ፪፲፻ ዶላር ኮምፒዩተር የገዛልህን ሰው እንዲህ አደረገልኝ እያልክ ስታሽቃብጥለት እና ህይወትህን ለማዳን እንደሻማ የቀለጡልህን ወገኖች ደግሞ ረግጠህ ስታልፍ ማንስ ለህዝብ አቤት አለ ? ማንም አላለም ከጠቀመው እንዲያውም ይሂድ ነበር መልሳቸው ፣ ቀጠል አድርገ ፊትህን በሌላም በኩል ወደ ኢሳት እና ግንቦት ሰባት ፊትህን በማዞር ከሃገር ቤት ካሉት ፖለቲከኞች ጋር አብሬ እታገልለታለሁ ስትል የነበረውን ህዝብ ጥለህ በሰሜን አሜሪካ ቀርቻለሁ ብለህ አውጀህ  ከእነርሱ ጋር የልመና ከረጢትህን ለመዘርጋት እንዳለምክ ሲረዱ ኢሳቶችም ለድርጅቱ ማቋቋሚያ እና ማጠናከሪያ የሚሆናቸውን ገንዘብ ማሰባሰብ እንደሚፈልጉ ሲገልጹልህ አሁንም በድጋሚ አሻፈረኝ ብለህ መሄዱም  ሆነ የገንዘብ ማሰባሰብ ጥቅሙ በግል በመንቀሳቀስ ለመጸሃፍ ማሳተሚያ ያስፈልገኛል ብለህ ማለትህ  እና ዛሬ ለመጸሃፍ ማሳተሚያ ይሆነኛል የምትለውን ገንዘብ ከየዋሁ ህዝብ ለምነህ ከርስህን ልትሞላበት ማሰብህን የነቁ ጋዜጠኞች እና በወቅቱ ይህንን ጉዳይ በጥብቅ በመከታተል፣ በማንኛውም የመረጃ ማእከል እንዲህ አይነቱን ነገሮች ማስተላለፉ ተገቢ ያልሆነ መሆኑን ሲገልጹልህ ፣ዛሬ አንደበትህን አውጥተህ ጋዜጠኞችን ለመሳደብ ቃጣህ ፣ሆኖም ፣እኛ ዛሬ የምናስበው በእስር ላይ ሆነው እድሜ ልክ ስለተፈረደባቸው ንጹሃን ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ፣ ፍርድም ሳይሰጣቸው በፍርድ እጦ የሚንገላትቱትን ንጹሃን ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞች፣ ሲቪክ ሶሳይቲ ፣አክቲቪስቶችን እና ቤተሰቦቻቸውን መታደግ እንጂ የምንፈልገው ፣ ከህዝብ የተለመነ ገንዘብ ለሌሎች ሊረዳ አይገባም ብለን አምቀን ለግል ጥቅማችን የምናውል ሆዳም ጋዜጠኞች አይደለንም ።

አቶ ሃብታሙ አያሌው ፣ ምናልባትም ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ የወያኔ መልእተኛ የሆነው ዳዊት ከበደ (አውራምባ ታይምስ) የቀድሞውም አላማው የስለላ ስራም ይሁን አይሁን ባንረዳውም ዛሬ በገሃድ ተቃዋሚዎችንም ሆነ መገናኛ ብዙሃኖችን እራሳቸውን እስኪያማቸው መናገሩ የማይቀር ሃቅ ሆኖበት ሲሳደብ እናየዋለን ፣አንተም ቀድሞ ስታገለግለው የነበረው የወያኔ መንግስት በዚያው የደህንነት ስራህ እንድታገለግለው በጥሩ ሁኔታ መልምሎህ የመጣህ ይመስል አካሂያድህ የገንዘብ እንጂ የፖለቲካ እና የነጻነት ምርኮ የሆን አትመስልም ፣የኢትዮጵያ ህዝብ ዳቦ እየራበው ነጻነቱን በጣም ከመጠማቱ የተነሳ ዳቦው ቀርቶበት ነጻነቱን የሚሻ ህዝብ እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቀዋለን ፣ታዲያ እንደ አንተ አይነቶቹ ሆድ አደሮቹ ፣በእስር ቤት ውስጥ አብረው ለተንገላቱት ወንድም እህቶችህ ከህዝብ ተለምኖ የተሰጠህን ገንዘብ ለማካፈል አለመሞከርህ እራሱ የትግል ስልትህንም ሆነ ውሳኔህ አለበለዚያም አላማህን ግልጽ አድርጎ ይየሚያሳየን እንደሆነ እገልጽልሃለሁ ፣አንተም የነገው ዳዊት ከበደ እንደምትሆን አልጠራጠርም፣ እኛ ግን ጋዜጠኝነት ስራችንን እንሰራለን ፣ለማንኛውም የፖለቲካ ድርጅቶች አናጎበድድም፣ ማናቸውም ሰዎች ስህተቶችን ሲሰሩ ለማረም እንጥራለን ፣መቅረብ የሚገባው ዜና ሲኖር የዜና አውታሮቻችን መረጃዎችን በስፋት ለህዝባችን ይሰጣል ! የጋዜጠኝነት ስነምግባር ልክ እንደ ፖለቲከኞች በውሸት አረንቋ እየተዘፈቁ ገንዘብ የሚለምኑበት ወይንም የሃገር አንጡራ ሃብትን ዘርፈው በሰው አገር የሚደብቁበት ትልቅ ሰራ ያለው አለመሆኑን ፣በግልጽ እነግርሃለሁ !! አሁንም ወደ ፊትም በግልጽ ስለ እውነት እንሰራለን ፣ስለ እውነት እንታገላለን !

በሰሜና አሜሪካም ሆነ በሌሎች አገራቶች ላይ መጸሃፍ ለማሳተም ብለህ የምትለምነውን እንቃወማለን ፣ንጹሃን በእስር ቤት ውስጥ እየማቀቁ አንተ ያላገኘኸውን እንድል ያላገኙ ብዙ አሉ እና ስለ እነርሱ እንጨነቃለን !!

 

 

 

 

 

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on June 6, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 8, 2017 @ 11:06 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar