በኢትዮጵያ ያለው የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ መሔዱ ተጠቆመ፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ መረጃውን ይፋ ያደረገው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ፣ የግንቦር ወር የዋጋ ግሽበት 8 ነጥብ 7 ሆነ መመዝገቡን ገልጿል፡፡ ይህም ካለፈው ሚያዝያ ወር ጋር ሲተያይ፣ በሸቀጦች ላይ የዋጋ ግሽበት መስተዋሉን ያሳያል ብሏል፡፡ የዋጋ ጭማሪው ከየካቲት ወር ጀምሮ እስከ ግንቦት ወር ድረስ በተከታታይ የተከሰተ ሲሆን፣ በሀገሪቱ የንግድ ስርዓት ላይም ቀውስ መፍጠሩ ተጠቁሟል፡፡
‹‹ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ለግሽበቱ መጨመር ምክንያት ነው፡፡›› ያለው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ፣ ‹‹በተለይም ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ እና ማሽላ ዋጋቸው ከፍተኛ ጭማሪ›› ማሳየቱን አስታውቋል፡፡ ጭማሪው በየጊዜው እየተከሰተ መምጣቱ በህዝብ ኑሮ ላይ ጫና ማሳደሩን የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ እንዲህ ዓይነት ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በሚታይበት ሁኔታ ውስጥ፣ ደሞዝ ቢጨመር እንኳን ግሽበቱን ለመቋቋም እንደሚያስቸግር ታዛቢዎቹ ይናገራሉ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ልብስና መጫሚያ፣ የቤት እቃዎች እንዲሁም ማስጌጫዎች ላይም ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መስተዋሉን ከኤጀንሲው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ‹‹ምግብ ነክ ሸቀጦች ግሽበት ካለፈው ሚያዚያ ወር ጋር ሲነፃፀር ከ12 ነጥብ 2 ወደ 12 ነጥብ 3 በመቶ ጨምሯል፡፡›› ሲል በሪፖርቱ ላይ የገለጸው ኤጀንሲው፣ ‹‹ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ግሽበት ደግሞ ሚያዚያ ወር ላይ ከነበረት 4 ነጥብ 6 በመቶ ወደ 4 ነጥብ 7 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡›› ሲል አስታውቋል፡፡
Source: BBN news June 8, 2017
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating