www.maledatimes.com ማለዳ ወግ የተገፊ ዜጎች ድምጽ ከሳውዲ አረቢያ | መንግስት ሆይ የተገፊ ዜጎችን የምሬት ድምጽ ስማ – ነቢዩ ሲራክ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ማለዳ ወግ የተገፊ ዜጎች ድምጽ ከሳውዲ አረቢያ | መንግስት ሆይ የተገፊ ዜጎችን የምሬት ድምጽ ስማ – ነቢዩ ሲራክ

By   /   June 12, 2017  /   Comments Off on ማለዳ ወግ የተገፊ ዜጎች ድምጽ ከሳውዲ አረቢያ | መንግስት ሆይ የተገፊ ዜጎችን የምሬት ድምጽ ስማ – ነቢዩ ሲራክ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 50 Second


==================================
*የሳውዲ የምህረት አዋጅ ሊጠናቀቅ ቀናት ሲቀሩት
* ከአፍታው እረፍት የመለሰኝ እውነት
* መንግስት ሆይ የተገፊ ዜጎችን የምሬት ድምጽ ስማ

ከአፍታው እረፍት የመለሰኝ እውነት …
========================
ላለፉት ጥቂት ቀናት የአፍታ እረፍት ለማድረግ ከዚህ ገጼ ገለል ብዬ መቆየቴ እውነት ነው ። የሚያነውን እውነት እየሰማሁ እንዳልቆስል በሚል እንጅ እረፍት የአረቡ ሀገር ስደት በግድ ጀሮን ይዘው ደፍነውት እንኳ የመከራ እንገግልቱ መረጃ ጀሮን በጥሶ ይሰማል ፣ በግድ ካልተጨፈኑና ካልደነቆሩ የሚታይ የሚሰናው ስላምና እረፍት የሚሰጥ ስደት አይደለም ። ከአፍታው እረፍት የመለሰኝ እውነት ይህው እውነት ነው: ( እረፍት ላይ ብሆንም ይህንን የተገፊ እህቶቸን የአደራ ድምጽ መልዕክት ተቀብዬ ዝም ማለት አለተቻለኝም 🙂 ዝምታው በራሱ አመመኝና ወደ ቀድሞው ይዞታዬ ተመልሸ ስለ ተበደሉት ፣ ስለተገፉት ወገኖቸ ድምጽ እሆን ዘንድ ተመልሻለሁ ! ወደ ቀድሞው ይዞታዬ ስመለስ የማራምደው አቋም የቀደመውን ነው ፣ የቀደመው አቋመፀ ደግሞ ሁሌም ከተገፊዎች ጎን መቆም ነው ! እናም ወደ መካከልኛውና ምሰራቃዊ የሳውዲ ክፍል በአንድ በኩል ፣ እዚሁ ጅዳ ከባቢ በሌላ በኩል የደረሱኝ ሁለት መረጃዎች ቀልቤን ስበውታል ። በተለይም ከወደ ሪያድ መካከለኛው ምስራቅ የሳውዲ ክፈል ባለች አንዲት ከተማ የማቆያ እስር ቤት ሆነው የሚሰቃዩ እህቶቸን ድምጽ መሰማት አለበትና እሱኑ በማሰማት እጀምረዋለሁ !

የሳውዲ የምህረት አዋጅ ሊጠናቀቅ ቀናት ሲቀሩት ..
=================================
የሳውዲ የምህረት አዋጅ ሊጠናቀቅ የቀሩት ጥቂት ቀናት ናቸው ። በእስካሁኑ ሂደት ከሳውዲ አረቢያ ይወጣል ተብሎ የሚገመተው ህጋዊ መኖሪያና የስራ ፈቃድ የሌለው የውጭ ዜጋ እየወጣ አይደለም ። አንድ ሚሊዮን የውጭ ዜጋ ይወጣል ተብሎ በሳውዲዎች ቢገመትም እስካሁን የወጣው የውጭ ዜጋ 100 ሽህ ስለመድረሱ መረጃ የለም ። ወደ ሀገራቸው መመለስ ከማይፈልጉ ዜጎች መካከል ኢትዮጵያውያን ቀዳሚ ከሚባሉት ተረታ እንገኛለን ። ከጅምሩ በኢትዮጵያን ተጓዦች የታየው ዳተኝነት ወደ መጨረሻዎቹ ቀናት የስራ ስምምነት መፈራረም መሰማት መነቃቃት ፈጥሮ ተስተውሏል ። አሁን አሁን ወደ ሃገር ለመመለስ የሚያስፈልገውን የመውጫ ቪዛ ለመውሰድ ያለው ውጣ ውረድና በስምምነቱ ዙሪያ ዝርዝር መረጃ አለመውጣቱ ተጓዡን ከመመለስ ገታ ያደረገው ይመስላል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ አደጋው የከፋ ነው በሚል መጠነ ሰፊ የቅስቀሳ ስራ በመስራት ላይ ነው። ነዋሪው ግን ሳውዲዎች ያደረጉንን ያድርጉ ያለ ይመስላል ፤ የመንግስትን ቅስቀሳ መስማት የፈለገ አይመስልም ።

መንግስት ሆይ የተገፊ ዜጎችን የምሬት ድምጽ ስማ …
===================================
ይህ በእንዲህ እንዳለ በምስራቅ የሳውዲ ከፍል ከአራት አመት በፊት በኮ ንትራት የገቡ እህቶች መብታችን ተገፈፍን ደመወዛችን ተቀማን ፤ መብታችን አስጠብቃችሁ ወደ ሀገር አስገቡን “ በሚል ቅሬታቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ ። ዳሩግን ተገፊ ዜጎች በእስር ላይ እና በየሆስፒታሉ ሆነው የመንግስት ያለህ ቢሉም ሰሚ ያገኙ አይመስልም ! ለዛሬው ያቀናበርኩትን መረጃ ያድምጡት ። ላልሰሙ ያስሙ ፤ መንግስት ሆይ የተገፊ ዜጎችን የምሬት ድምጽ ስማ በማለት ለሚመለከታቸው እንዲደርስ አሰራጩት !

እስኪ ቸር ይግጠመን !

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 3 ቀን 2009 ዓም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on June 12, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 12, 2017 @ 10:28 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar