ከሰላሳ አራት አመታት በፊት የተጀመርው እና ዛሬ ላይ ኢትዮጵያኖችን አሰባስቦ በየአመቱ በድምቀት የሚከበረው የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ማእከል ከዛሬ አመስት አመታት በፊት ፳፱ ክለቦች የነበሩን ሲሆን – በአሁን ሰአት ፴፩ ክለቦች በአሁን ሰአት ይዘን እየተጓዝን ሲሆን በሌሎች ስቴቶች ያልተደራጁ ክለቦችን ለማደራጀት እጥራለን በማለት በፌደረሽኑ ስር ያሉ የቦርድ አመራር አካላቶች ገለጹ
በዛሬው እለት ከማለዳ ታይምስ ጋር የስልክ ውይይት ያደረጉት እነዚሁ አባላቶች ቀድሞ በነበሩት የተለያዩ የስራ አካላቶች እና የስራ አባላቶች በተለያዩ ወቅቶች የስፖርት ፌደሬሽኑ ከተለያዩ ማህበረሰቦች እና የፖለቲካ ድርጅቶች የደረሰባቸውን ⶻና የገለጹ ሲሆን ፣ባሳለፉት አምስት አመታትም ከተለያዩ ሰዎች የደረሱባቸው ጫናዎች ፣የፖለቲካ ጽንፈኛ አካል እንደያዙ ተደርጎ እንደተያዘባቸው አስታውሰው የገለጹት እነዚህ አባላቶች ዛሬም ይሁን ትላንት አለበለዚያም ወደፊት እኛ ከህዝብ ጎን እንጂ ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ወግኞች ሆነን ልናገለግል አልተነሳንም ብለው ገልጸዋል።
በፌደሬሽኑ ለሚዘጋጁ ማንኛውም ዝግጅቶች በወቅቱ መጥቶ ለሚጠይቅ ስፖንሰር ቅድሚያ እንሰጣለን፣ ድንኳኖችንም ሆነ ሌሎች ነገሮችን ለመግዛት የሚችል ማንኛውም ድርጅት ከድርጅታችን አገልግሎቶችን ለማግኘት በሩ ክፍት ነው ሲሉ አክለው የገለጹ ሲሆን ፣ ከመረጃ ማእከሎች የመንግስትም ይሁን የግል ወይንም የሲቪክ ማህበራቶች የእኛ ድርጅትን ህልውና የማይነካ ከሆነ እና ነጻ እና ገለልተኛ ሆነው ፣ ያለንን ድክመት እና ጠንካራ ጎን ሪፖርት መስራት ለሚችሉ ወገኖች በሙሉ አሁንም በራችን ክፍት ነው ሲሉ ገልጸዋል ።
በሌላም በኩል ከመንግስትም ጋር ይሁን ከፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ምንም አይነት ቅርርብነትም ይሁን ግንኙነት ሊኖረን አይችልም ሆኖም ግን እያንዳንዱ ግለሰብ በሚኖረው የራሱ የሆነ የፖለቲካ አመለካከት ፣ከድርጅቱ ጋር አጣምሮ ሊታይ አይገባውም ስለዚህ ከሁሉም ጋር ለመስራት እኛ ዝግጁዎች ነን ሲሉ ጠቁመዋል። ቀድሞ የነበረው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ለሁለት የመከፍል አላማ አልነበረም በሁለቱ ድርጅት ውስጥ የማዘዝ እና አለመታትዘዝ አላማ ስለነበር እንጂ ለሁለት ተከፍለን አይደለም ፣ በማንኛውም የኢትዮጵያ ችግር ላይ ሰበአዊ መብት ላይ ጥሰት ላይ ሲገልጸው እና ሲታገል የቆየ ነበር ፣ቀድሞም በብዙ የፖለቲካ መንገዶች ሲጠቀስ ቢቆይም እስካሁን ድረስ እንዳይፈርስ አላማውን ይዞ እንዲሄድ ያደረግነው ፣ምናልባትም ወገንተኝነትን ላለማሳየት በመሞከራችን ነው ሲሉ ተናግረዋል ።
የስፖርት ፌደሬሽኑን አመራር እና ውስጣዊ ደንቦችን በጥልቀት ማየት ምናልባትም ሊረዳ የሚችልበት አጋጣሚ የሚኖረው በምን አይነት አጀንዳ የሚራመድ ድርጅት መሆኑን ለማሳወቅ ሊሆን ይችላል ሲሉ የተናገሩት እነዚሁ ግለሰቦች በቀጣዩ ለሚመጡት በአላቶች በሙሉ ህብረተሰቡ ከቦርድ አመራር አካላቶች ጋር በጋራ በመስራት የህዝብ አገልጋይ መሆኑን እንዲያውቁት ሊረዳ ይችላል ብለው ተናግረዋል
በዘንድሮው የሴያትል ስፖርት ፕሮግራም ላይ ፣አትሌት ሊሊሳ ፈይሳ፣ እና የቀድሞ እግርኳስ ተጨዋች በእንግዳነት እንዲጋበዙ ጥሪ የተደረገላቸው ሲሆን አርቲስት ሻንበል በላይነህ ልዩ የክብር እንግዳ ሆኖ እንደሚቀርብ ተጠቁⶁል ።
Average Rating