በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ፖሊስ ተጠራ ፣ ህዝበ ምእመናኑን አስኮርፏል
በተለያዩ ጊዚያቶች በችካጎ ስለሚገኘው የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ፣የደረሰውን አሰቃቂ የሆነ የፖለቲካ ክፍፍል ከመንግስት ደጋፊዎች በኩል ማቅረባቸውን ያላስደሰታቸው ምእመናን ጩኸታቸውን ማሰማታቸውን የቀጠሉ ቢሆንም ጥቂት የሆኑ እንቢተኞች እና የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች የሆኑ የሃይማኖት ለዘብተኞች ቤተክርስቲያኗን ሲያተራምሱ ለማየት ችለናል ይህንንም በዘገባችን መዘገባችንም የሚታወስ ነው ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፣በቺካጎ የሚገኘው የሰበካ ጉባኤ አባላት በሙሉ በቅዱስ ሲኖዶሱ መተዳደርም ሆነ በአቡነ ዘካርያስ አስተዳደራዊ ሂደት አለመቀበሉን እና አለመቀበሉን የገለጹት ሙሉ ህዝበ ክርስቲያን በጥያቄዎቻቸው ላይ መልስ እንደሚሹ የጠቆሙ ሲሆን አዲስ ለመጡት ቆሞስም በድጋሚ አቅርበዋል፣ ቆሞሱም ሃሳባቸውን ከመስማት ውጭ አድበስብሰው በማለፍ ማህበረሰቡን ለማረጋጋት ሞክረዋል።
በዛሬው እለት በቤተክህነት ስርአት ምንም ክፋትም ቢሰራ በቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚደረጉ ማናቸውንም ጥፋቶች በቤተክርስቲያን ውስጥ በመተራረም እና በይቅርታ መታለፍ ይገባዋል ተብሎ ቢባልም የወያኔ ደጋፊ የተባሉት እና የቤት ክርስቲያኗን ቁልፍ ቀየሩ የተባሉት ጥቂት ማህበረቦች በዛሬው እለት ፖሊስ በመጥራት ማህበረሰብን ለማደናገር ሞክረዋል ።
ባሳለፍነው ሳምንትም 9 የሚሆኑ የሚተክርስቲያኒቱን አባላት ላይ ክስ መስርተዋል ፣በተለይም የዲያቆን በረከት ጉዳይ ያገባኛል፤ በእሬቻ በአል ላይ የተገደሉት ወገኖቼ ናቸው ጸሎተ ፍትሃት ሊደረግ ይገባዋል ወይንም የህሊና ጸሎት ሊታሰብላቸው ይገባል ያሉ ክርስቲያኖች ፣ክሱ እንደቀረበባቸው ፣ጠቁመዋል ። በቤተክህነት አባላቶችም ጠፋ ለተባለው ገንዘብ ተጣያቂ መሆን ካለብን እንሆናለን ፣ቤተክርስቲያናችን የግል ሳይሆን የህዝብ እና የህብረተሰብ ነው ፣በግል ጥቅም ተነሳስተው ማንኛውንም ሰው መክሰስም ሆነ ማባረር አይችሉም ሲሉ ተደምጠዋል።
በቤተክርስቲያኑ አፍራሽ ጎራ ከተደመጡት አንዷ ግለሰብ እንደተናገሩት ከሆነ ( ስም ላለመጥቀስ ይፈቀድልን) በቤተክርቲያን ምስረታው ወቅት የዛሬ ሰባት አመታት ፊት ለፊት ተቀምጠን እንዳላወራን ዛሬ እሩቅ ለእሩቅ ሆነን ልንከራከር ባልተገባ ፣ በፓትርያሪኩ የተደረገው ነገር ትክክል ነው ስትል የተናገረች ሲሆን ይህንን ሃሳብ ተከትሎ ሁለት የዚሁ ቡድን ተከታዮች ዘሃበሻን እና ማለዳ ታይምስን ሲከሱ ታደምጠዋል።
በቤተክርስቲያናችን ያለው ችግር የቤተክርስቲያናችን ነው በማለት ለማስተባበል ቢሞክሩም እና ማለዳ ታይምስ ሪፖርቱን እንዳይሰራ ለማሳግድ ቢጥሩም ማህበረሰቡ በአዎንታዊ መልኩ የማለዳ ታይምስን እና የዘሃበሻን ሪፖርት ማድነቃቸውን ለማየት ችለናል ፣ይህንንም ለተናገሩት ሰዎች የተቃውሞ ድምጽ ከማህበረሰቡ ቀርቦባቸዋል። ምስጋናውንም ለዘሃበሻ እና ለማለዳ ታይምስ ያቀረቡ ሲሆን አሁንም በትጋት ሪፖርታዡን እንዲሰሩ በአጽንኦት ጠይቀዋል ።
በዲያቆን በረከት ጉዳይ ላይ ስለነበረው ጉዳይም ያነሱት እነዚሁ ግለሰቦች ትክክለኛ ነው ብለው የሚያምኑ ቢሆንም በህገወጥ በቤተክርስቲያኗ ላይ የተከሉት ካሜራም ሆነ ፣የህዝብ የሆነውን ቤተክርቲያን ቁልፍ መቀየራቸው ጥፋት መስሎ እንዳልታያቸውም ተናግረዋል ።
ለግልጥቅማቸው በማሰብ የቤተክርቲያኒቱን ህልውና ለማፍረስ ተነሳሽነት ያጸደቁት እነዚሁ ግለሰቦች በዘሃበሻ እና ማለዳ ላይ በተሰሩት ስራዎች ላይ ትልቅ መከራከሪያ ሃሳብ ቢያመጡም በወቅቱ ዘጋቢው በስፍራው ቆሞ ሪፖርታዥ ለመስራት የሚያመቸውን መረጃ በማሰባሰብ ላይ እያለ እንዲያቆም በቆሞሱ በኩል ሃሳባቸውን በማስተላለፍ እንዲቆም ቢገደድም፣ ጆሮ ይሰማል አኧምሮ ይቀዳል ለዚህም እውነተኛውን መረጃ ይዞ የሚሰሩ ድርጅቶች መሆናቸውን ያሳያል ። ስለ እውነት እንቆማለን ።

የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስትያን ምእመናን በስብሰባ ወቅት ችግሮቻቸውን ለመፍታት ሲተጉ
እራሳቸው በፖለቲካዊ አጀንዳ እየተንቀሳቀሱ ህዝቡን በፖለቲካዊ አጀንዳ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች አሉ በማለት ለብጹእነታቸው እየተናገሩ ያሉት ሊቀመላክ እራሳቸውም ሆኑ ብጹእ አባታችን በዚህች ቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነው የተናገሯትን ነገር ማንኛውም ህዝብ አይረሳምው ፣ትክክለኛውን የፖለቲካ አጀንዳ ይዘው የመጡት እራሳቸው ናቸው ፣ ከእርሳቸው ስር ሆነው የሚያጎብበድዱት በሙሉ ያላቸውን የፖለቲካ አጀንዳ በንጹህ ህዝብ ላይ ማራገፍ ይፈልጋሉ ፣ሆኖም ግን ዛሬ እዚህ መድረክ ላይ የመጣነው በህገ እግዚአብሄር ደንብ ፤ ህግ እና ስርአት መሰረት መስማማት እንድንችል እንጂ ሌል ፖለቲካዊ አጀንዳ ይዘን እንድንመጣ አይደለም የተሰበሰብነው ፣ ቤተክህነታችንን ከአደገኛ ሁኔታ ነገር ማዳን የእኛ ስራ ነው ፣ እናንተ በምትሄዱበት መንገድ ሄደን ሳይሆን የምናድናት ብዙሃኑ በመረጠው መንገድ ነው ሲሉ የቤተክርስቲያኗ አባላት በስብሰባው ላይ ገልጸዋል።
በተለያዩ ነጥቦች ሃሳባቸውን የገለጹት እኝሁ ግለሰብ እንደተናገሩት ከሆነ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖብን ዲያቆኑን እገዳ ተጥሎበት ሳለ ለምን አላቆምከውም ተብሎ ፣ይህንን ዲያቆን እንዳያስተምር አስተዳዳሪያችንን ማስነው ታትረው እንደ እናንተ ከዚህ በላይ ሄደው መስራት የሚችሉበትን ስራቸውን ከፍ ማድረግ በሚገባቸው ቦታ ላይ መቆም በሚችሉበት ሁኔታ እና እድል ላይ እያሉ ፣ቆማ መሄድ ባቃታት ቤተክርስቲያን ላይ አገልግሎቴን እሰጣለሁ ፣አስተምራለሁ ብለው ትጉ ስለሆኑ ፣እርሳቸውን ፣በግል፣ በቡድን እና በተናጠል ይህች ታቦት ታውቀዋለች ፣ስለ እወነት በእውነት የምንነጋገርባት የእግር መረገጫችን የሆነችው ቤተክርስቲያናችን እያወቀችው እርሳቸውን በቡድን ተደራጅተው እርሳቸውን ከዚህች ቦታ ላይ ለማንሳት የሚራመዱ ምቹ ጊዜ እየጠበቁ የሚጓዙ ስዎች መልእክቱን ከብጹእነታወ ጋር አነካክተው ፣ከስልጣናቸው ለማስወገድ ጣሩ ፣ህዝቡ የሚፈልገውን እንጂ የማይፈልገውን ማስቀመጥ አይፈልግም ፣ለእርስዎም ለቆመሱ የሚከፈለው ገንዘብ ከህዝቡ ነው እና እርስዎም ቢኆኑ ከህዝቡ የሚመጣውን ገንዘብ በቀላል እንዳልሆነ ይመልከቱት ፣የሚፈልገውን ያጣ ህዝብ ለማይፈልገው ሰው ገንዘብ የሚያዋጣ ያለ አይመስለኝም ሲሉ ገልጸዋል ።
የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንዴት ሊሰጥ ይችላል ፣ካቴድራል ስለሆነች ቆሞስ ነው የሚያስፈልጋት በለው የሚባለው አስተዳደሩ እና ህጉ እንደዚያ ነው ወይ ፣ ከእኔም ኪስ ከህብረተሰቡም ኪስ ወጥቶ ነው እርስዎን ለማስተዳደር እንዲሹ እና እንዲችሉ የምንከፍልዎት ፣የሃገሩ ህግ ደንብ ስርአት እንደዚያ ነው ሲሉ ቤተክርስቲያኢቱን ለማዳን የሚጥሩ ማህበረሰቦች አሁን ጩኸታቸውን ማሰማት ጀምረዋል ። የማለዳ እና ዘሃበሻ ውድ አንባብያኖች በዚህ ጉዳይ ላይ ተከታታይ ሪፖርት ይዘን ለመቅረብ የምንችል ስለሆነ በስፋት ይከታተሉን ፣ለሚቀጥለው ሳምንት ከእሮብ በኋላ የህግ ባለሙያ አናግረን ቀጣዩን ሪፖርት ለማቅረብ እንሞክራለን ።
በተጨማሪም በዚህ ጉዳይ ላይ በህግ ጥብቅና ለተከሰሱት ዘጠኝ ወገኖች ጥብቅና እንቆማለን ብላችሁ ለምትሉ የህግ ባለሙያዎች የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍሉን ማናገር ትችላላችሁ ። editor@maledatimes.com ኢሜል ያድርጉልን እንመልሳለን ።
ከዚህ በታች ያለውን ዘገባ እንዲመለከቱ እንጋብዛለን ።
የችካጎ ደብረ ገነት ቤተክርስትያን ምጥ ላይ ናት ለምአመናን ጥሪ ኣቀረበች
http://www.zehabesha.com/amharic/?p=69101
Average Rating