www.maledatimes.com በሎንዶን ሦስት አሸባሪዎች ሰባት ሰዎች ገድለው፣ ፵፰ ካቆሰሉ በኋላ በፖሊስ ተገደሉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በሎንዶን ሦስት አሸባሪዎች ሰባት ሰዎች ገድለው፣ ፵፰ ካቆሰሉ በኋላ በፖሊስ ተገደሉ

By   /   June 19, 2017  /   Comments Off on በሎንዶን ሦስት አሸባሪዎች ሰባት ሰዎች ገድለው፣ ፵፰ ካቆሰሉ በኋላ በፖሊስ ተገደሉ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 8 Second
ምንጭ ኢትዮጵያ ዛሬ
London Bridge Attack, on June 3, 2017.
የታጠቁ የእንግሊዝ ፖሊሶች አሸባሪዎችን ሲያድኑ። (የፎቶ ምንጭ: Daily Mail)

ኢዛ (እሁድ ግንቦት ፳፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. June 4, 2017)፦ ቅዳሜ ከምሽቱ አራት ሰዓት በኋላ፣ በሎንዶን እምብርት በሚገኘው የሎንዶን ድልድይ አካባቢ ሦስት ጀሃዲስት አሸባሪዎች ሰባት ሰዎችን ገድለው አርባ ስምንት ሰዎችን ካቆሰሉ በኋላ፣ በእንግሊዝ ታጣቂ ፖሊሶች ተገደሉ።

የሎንዶን ጥቃት፣ ጁን ፫፣ ፳፻፲፯
በእንግሊዝ ፖሊሶች የተገደሉትና አሸባሪዎች ናቸው ከተባሉት ውስጥ የሁለቱ አስክሬን። (የፎቶ ምንጭ: Daily Mail)

እነዚህ ሦስት አሸባሪዎች ነጭ ቫን መኪና (ከኋላው መስታወት አልባ መለስተኛ አውቶቡስ፣ ዕቃ መጫኛ ሚኒባስ) ሎንደን ድልድይ አካባቢ ከምሽቱ አራት ሰዓት በኋላ መንገደኞች ላይ እየነዱ ጉዳት ካደረሱ በኃላ፣ ”ብራውት ገበያ” ሲደርሱ ከመኪናው በመውጣት አስራ ሁለት ኢንች በሚሆኑ ጩቤዎች በአካባቢው የነበሩ በርካታ ሰዎችን ወግተዋል።

የሎንዶን ጥቃት፣ ጁን ፫፣ ፳፻፲፯
የሽብርተኞች ጥቃት ሰለባ ከሆኑት ውስጥ በቃሬዛ ወደ አንቡላንስ እየተገፋ ሲወሰድ፣ እንዲሁም በጥቃቱ ሰዎች በከፍተኛ ድንጋጤ ተውጠው። (የፎቶ ምንጭ: Daily Mail)

በወቅቱ በሥራ ላይ የነበረና የተጎዱ ሰዎችን በመርዳት ላይ የነበረ የእንግሊዝ ፖሊስ ባልደረባ በጩቤ ከተጎዱት መሃል ሲሆን፣ ጉዳቱ ለሕይወቱ እንደማያሰጋው ታውቋል።

የሎንዶን ጥቃት፣ ጁን ፫፣ ፳፻፲፯
ብራውት ገበያ ከሚገኘው ዊትሼፍ ፐብ ደጃፍ ላይ ከተገደሉት ጂሃዲስቶች ውስጥ አንዱ የአርሴናል የእግር ኳስ ማልያን የለበሰ እና የውሸት ቦምብ መታጠቁን የሚያሳይ ፎቶግራፍ። (የፎቶ ምንጭ: Instagram / fried_chicken)

ሦስቱ አሸባሪዎች በራሳቸው ላይ ቦንብ የሚመስል ታጥቀው የነበሩ ቢሆንም፣ ቦምቡ የውሸት (አርቲፊሺያል) እንደነበር የእንግሊዝ ፖሊስ ገልጧል።

በያዝነው የአውሮፓውያን ዓመት (፳፻፲፯) ውስጥ ይኽኛው በእንግሊዝ ላይ የተፈጸመው የአሸባሪዎች ጥቃት ሦስተኛው እንደሆነ ይታወቃል። የመጀመሪያ ጥቃት ባለፈው ማርች ፳፪ በሎንዶን ዌስትሚንስትር የደረሰው ሲሆን፣ ሁለተኛ ደግሞ ሜይ ፳፪ የተፈጸመው የማንቸስተሩ የቦምብ ጥቃት መሆናቸው አይዘነጋም።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on June 19, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 19, 2017 @ 1:16 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar