www.maledatimes.com ምዕራብ ሸዋ ከተላኩት የመከላከያ ሠራዊት አባላት መካከል ከአንዱ የተላከ አጭር መልዕክት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ምዕራብ ሸዋ ከተላኩት የመከላከያ ሠራዊት አባላት መካከል ከአንዱ የተላከ አጭር መልዕክት

By   /   June 19, 2017  /   Comments Off on ምዕራብ ሸዋ ከተላኩት የመከላከያ ሠራዊት አባላት መካከል ከአንዱ የተላከ አጭር መልዕክት

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 27 Second

ምዕራብ ሸዋ ከተላኩት የመከላከያ ሠራዊት አባላት መካከል ከአንዱ የተላከ አጭር መልዕክት: “ለተከበራችሁ የኢትዮ/ጦር ሀይል አባል ለሆናችሁ የኦሮሞ ተወላጆች አጭር መልዕክት”

እንደሚታወቀዉ የማንኛዉም ሀገር ጦር ኃይል ታክ እንደሚገልፀዉ የመከላከያ/የጦር/ ሀይል የሀገርን ዳር ድንበር መከላከል የህዝቦችን ደህንነት ያለአድልዎ መጠበቅና በተነደፈዉ ሕገ መንግስት በመመራት በህግና ደንብ መሠረት ለዜጎች /ሀገር ታማኝነት ማረጋገጥ ነዉ፡፡


በመሆኑም ቀደም ስል በቀ/ኃ/ሥ/መንግስት ዘመን የጦር ኃይል አባላት ምንም እንኳን የገዢዉ መደብ ታማኝና የጥቅም ታጋራዎች ቢሆኑም ለዘመናት የነበረዉን የአንድ ብሐሄር ጣምራ የፖለቲካና የእኮኖሚ ጭቆና ስለገባቻዉ ከሠፍዉ ጭቁን ሕዝብ ጎን ተሠልፈዉ በትግል ታርክም ግምባር ቀደም ከነበሩት ከታማሪዎች ፤ ከአርሶ አደሮችና ከሲቪክ ኅ/ሰብ ጋር በመሆን የወቅቱን ጥያቄ ላንዴና ላመጨራሻ እንድመለስ መደረጉ ይወሳል፡፡


ይሁን እንጅ እያደር ሥልጣን በጣማቸዉ ብልጣብልጥ ወታዳራዊ መኮንኖችና አንድንድ መሽጦ ምሁራን ሐቀኞቹን የሕዝብ ልጆችን በመፍጀት በተባባሰዉ አስተዳደራዊ ጭቆናና አፈና የተነሣ በሕዝቡ ትግል እና ሕዝባዊ ወገንተኝነት ባላቸዉ የሠራዊት አባላት እንድሁም በሌሎችም ታጋዮች ከፍተኛ መሥዋዕትነት ግዙፉ የደርግ መንግስትም ተሸነፈ ፤ተወገደ፡፡


በመሆኑም ዛሬም መልኩን ለዉጦ በወረቀት ላይ ባማረ በተግባር በከሠረ ግልባጭ ዲሞኪራሲ ሥም በመጠዉ በአንድ መጥራግያ አዛሪ አናሳ ብሄር በላይነት በተቀቀመዉ መንግስት ብሄር ብሄረሰቦችን በመርገጥ ላይ ይገኛል፡፡ ከዝህም አድልዎ ፤ብዝባዛና ሞት (Genocide) ከበዛበት ብሄር አንዱ የኦሮሞ ብሄር ነዉ፡፡


ይኸዉም ያልነቁ ወይም እየወቁ ለታርክና ለትዉልድ ሣይሆን ለሆዳችዉና ለግዜያዊ ምቾት ያደሩ ካሀዲ ባንዳ የራሱን ወገን በገዛ ሀብቱ በመግዛት በማጥፋት ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም በዚህ የጥፋት መልዕክተኞች ሠራዊት

የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች የሕዝባቸዉን ዲሞክራሲያዊና ሁላንታናዊ ሰብዓዊ ስብዕና ከመገፈፍም አልፎ ምሁሮቻቸዉ፤ወጣቶቻቸዉና አርሶ አደሮቻቸዉ ባዶ እጀቸዉን ለመብታቸዉ ሲጮሑ በየቦታዉ ተገድላዉ አስክሬናቻዉ እንደዉሻ ሬሣ የትም ሲጣል ብሎም ቀብር እንኳ ስከለከሉ ማየታችዉ እናም እነርሱ ራሳቸዉ (ወታደሮቹ ማለት ነዉ) ለማን ዘብ ቁመዉ ብሎም ሕይወታቸዉን ገብረዉ ማንን እንደሚያኖሩ አለመለያታቸዉ እጅግ እጅግ የሚያስደነግጥ ከመሆን አልፎ የወያኔ አጋዚ ሠራዊትን ታይቴዋል፡፡

እንደዚሁም ሌላዉ አሣፋሪ ተግባር የገዛ አባቱና እናቱን ሀንጡራ ሀብት ሲዘሪፍ፤ ወንድምና እህቱን እንደዚሁም ይህችን ሀገር ያቆዩዋት አዛዉንቶች በየመንደሮቻቸዉ በአገዚ ከመገረፍ አልፎ መረሸናቻዉን እያዩ አለመላወሳቸዉ ሲታይ እጅግም ያሳፋራል፡፡

ጠመንጃ ይዞ ክብርን አጥቶ ከመኖር ለሀቅ ብሎ በዲንጋይና ዱላ ተፋልሞ ሞት ለማይቀርላት ሕይወት መሰዋትነትን ከፍሎ በታሪክ መዝገብ ላይ መኖርን የመሠለ ታላቅነት የለም፡:

ለዚህም ሙስጠፋ ሁሴን ቡቱጂ በጀግንነት ከተመዘገቡት አርበኞች አንዱነዉ፡፡ ስለዚህ ዓላማቢስ ደቃቃ ገኛ ሠራዊት ከመሆን በራሳቸሁ(ቸን) ላይ ለሚደርሰዉ የራስን፤የአልባሳት፡የት/ትዕድል፡የሹመት፡የመኖሪያቤት፡የምደባቦታእናሌሎችጥቅማ ጥቅሞች በአድልዎ ሲወረወርላቸዉ(ልን) የላቀ ወታደራዊ ዲሲፒሊን ከመሰላቸዉ(ለን)ለሕሊናዎ ለሰባዊነትም ያስቸግራል፡፡

ይህንስል የዚህ ታላቅ ታጋይ ሕዝብ የትግል ታሪክ ከንክኖኝ ቖጭቶኝእናአበሳጭቶኝነዉ፡፡

በመሆኑም የኦሮሞዉ ወታደር ከአጋሮቹ የኩሽልጆች(ወታደሮች) ጋር በመተባበር እንዲያስቡበት እንጂ በርካታ ጀግኖችም እንዳሉት ይታወቅልኝ፡፡ ሌላዉቢቀር ከቅማንት አርሶአደሮችና አጋርወታደሮቻቸዉ ብዙመማር ይጠበቅባቸዋል ነበር፡፡
እኔም የዚሁ ጭቆና ተጋሪ የሆንኩ የኩሽ ዘርሐረግ የደቡብተወላጅ የሆንኩና ትናንትምዛሬምሆነ ነገ በትዉልድ ወገኖችናበሌሎችም የኢተ/ሐዝብ ላይ በየተራዉ የሚፈፀምም እየተፈፀመም ላለዉጭቆና ለፍትሕዊነት ከጎናችሁ እቆማለሁ፡እታገላለለዉ፡እተጋለዉ፡ እሞታለሁ ባይ ነኝ፡፡

ስለሆንም እነዚህን አስመሳይ ዲምክራቶች መስሪ የአፔሪያሊስቶች ተጎታች /አሽከሮች/ የትናንት መጥረግያ አዛሪ ማይምንና ችግር ሥላጣን ያስጨበጥቸዉ ዘአጥ ሠዎችን በማስወገድ አስቀያሚ የባርነትታሪክ በጋራ በመለወጥ የሕዝባችን ቁሳዊ ዕላቂት ለመታደግ የማንኛዉም ሀገራዊ ኀላፍነት የሚሰማዉ ሰራዊት ኀላፊነት ቢሆንም በተለይም የብሁኃኑ ኦሮሞ ሠራዊት አባል ታሪካዊ ትግልን ጠይቁዋል፤፤
ለዚህም ሹመትና ሽልማት ማንነቱን ላላስከዳዉ(ያልለወጠዉ)ቆራጥ ብ/ጀ/ ከማል ገልቹ እና መሰሎቹ ይኽን ታሪክ የስሩት፡ ይናገሩ፡ ይፃፉት፡ ያስተላልፉት
እላለዉ፡፡

ታላቁ ፈላስፋ ሶቅረጠስ ‹‹ችግር ከሚያስከትሉ(ከሚፈጥሩ) ነገሮች ነፃ ለመሆን ዛሬ መሞት እንደሚሻለኝ ይታየኛል››ያለዉን በማስታወስ
መልዕክቴን እቁዋጫሌሁ፡፡
ድል ለሀቀኞች!!
ወደ ምዕ/ሸዋ ከተላኩት መከ/ሠራዊት አንዱ ነኝ።’

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on June 19, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 19, 2017 @ 2:27 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar