
ኢዛ (ዓርብ ግንቦት ፲፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. May 26, 2017)፦ የፌዴራሉ ጠቅላይ አቃቢ ሕግ በኢሬቻ በዓል ላይ ለሃምሳ አምስት ሰዎች መሞት ምክንያት የኾነውን ኹከት እና ብጥብጥ አስነስተዋል ባላቸው የመጀመሪያዎቹ ሁለት ግለሰቦች ላይ ክስ እንደመሰረተባቸው ተዘገበ።
ክስ የተመሰረተባቸው አንደኛው ተከሳሽ አቶ ቱፋ መልካ ”የአገር ሽማግሌዎች በኢሬቻ በዓሉ ላይ ንግግር ሲያደርጉ ማይክ በመቀማት ኹከት እና ብጥብጥ አስነስተዋል” በሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ተከሳሽ አቶ ከድር በዳሶ ደግሞ ”በበዓሉ ላይ ከመድረክ ጀርባ በመሆን በስልክ አመጹን ሲያስተባብር ነበር” በሚል መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።
አቃቢ ሕግ ክስ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ባቀረበው ክስ ላይ፤ ተከሳሾቹ በኢሬቻ በዓል በተፈጠረው ግርግር ለሞቱት ሃምሳ አምስት ሰዎች መሞት ተጠያቂ መኾናቸውን ዘርዝሯል።
በችሎቱ የተገኙት ተከሳሾች የተመሰረተባቸው ክስ የተነበበላቸው ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹን መቃወሚያ ለመስማት ለፊታችን ግንቦት ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል።
በዓመቱ መጀመሪያ ላይ መስከረም ፳፪ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. በቢሾፍቱ (ደበረዘይት) በተከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ የሞቱ ወገኖች በመቶዎች እንደሚቆጠሩ ገለልተኛ የሆኑ ወገኖች ቢናገሩም፤ መንግሥት ግን ቁጥሩ ፶፭ ብቻ ነው ማለቱ ይታወቃል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating