Read Time:6 Minute, 7 Second
#የፍኖተ ዴሞክራሲ ዜናና ኃተታ – ሰኔ 13 ቀን 2009 ዓ.ም.
#ርዕሰ ዜና
# በአየር ለውጥ ምክንያት የኢትዮጵያ የቡና አብቃይ አካባቢዎች ይጎዳሉ ተባለ
#በአዲስ አበባ መሬት መቀማትና ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው ማባረር ተጠናክሮ ቀጥሏል
#ተመድ የተምች መንጋ መስፋፋቱን ገልጾ ለመቆጣጠርና ለማጥፋት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገለጸ
#የግብጹ አይሲሲ ወደ ካምፓላ ሄዱ፤ የአባይ ግድብም በርካታ ችግሮች አሉበት ተባለ
#የኦርሚፋ ቋንቋ በላቲን ፊደሎች ተሻሽለው እንዲጻፉ የአሜሪካን መንግስት ያበረታታ መሆኑ ተገለጸ
#በኢትዮጵያ የቱርክ ትምህርት ሽብርተኛ ናቸው በማለት ለሎች እንዲሰጡ ተደረገ
#የወያኔው ንብረት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፈረንሳይ ኤርባሶችን ገዛ
#የዛሬውን የስደተኛ ቀን አስመልክቶ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስርኞች አንድነት ኮሚቴ ምዕራባውያን ለስደተኛ በራቸውን እየዘጉ መሆናቸውን ጠቆመ
#ኢጋድና የአፍሪካ ህብረት ለሻዕቢያና ለጂቡቲ መልእክት ላኩ
#የግንባታ ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ ጽ/ቤት ተከራየ
##ዝርዝር ዜናዎች##
#በዓለም ላይ እየተባባሰ በሄደው የአየር ለውጥ ምክንያት በኢትዮጵያ የሚገኙ የቡና አብቃይ አካባቢዎች በከፍተኛ ደረጃ ሊጎዱ እንደሚችሉ ኔቸር ፕላንትስ በተባለ መጽሔት ላይ ሰሞኑን የታተመ አንድ ጥናት ገለጸ። 30 ሊሎሜት ርዝመት ካላቸው ቦታዎች ላይ የተለያዩ መረጃዎችን የሰበሰበው ይኸው ጥናት በምዕተ ዓመቱ መጨረሻ ላይ ከ 40 እስከ 60 በመቶ የሚሆኑ የቡና ተክሎች በአየር ጠባዩ ሳቢያ ሊበላሹ እንደሚችሉ ገልጿል። የቡና መጠን መቀነስ ብቻ ሳይሆን ጣዕሙም ሊበላሽ እንደሚችል ጥናቱ ይጠቁማል።፡የአየር ንብረት ለውጥ ከሚታዩባቸው አገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ስትሆን በተሰበሰበ መርጃ መስረት ከ1950 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ያለው የዝናም መጠን በ40 ኢንች ያህል የቀነሰ መሆኑ ይነገራል። ጥናቱ በመደምደሚያው እንደገለጸው ከዚህ አደጋ መውጣት የሚቻለው በዓለም አቀፍ ደረጃ በአየር ንብረት ብክለትን ለመቀነስ በሚወሰድ እርምጃ እና የቡና ተክልን ወደ ከፍተኛ ቦታዎች በመውሰድ ጥረት ከተደረገ ነው ብሏል። የቡና ተክልን በከፍተኛ ቦታዎች ላይ ማስፋፋትን በሚመለከት ተግባሩ ቀላል አለመሆኑን ገልጾ የታቀደና የታሰበበት የመንግስትና የዜጎችን ትብብር እንደሚጠይቅ ገልጿል።
#የአዲስ አበባን መልክ ለመቀየርና ለማልማት እየተባለ ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው ማስወጣትና ማባረር የተለመደ ቢሆንም ሰሞኑን በአራዳ ወረዳ በወረዳ 1 ቀበሌ 16 እየተካሄደ ያለው ቤቶች የማፍረስ ተግባር በርካታ ዜጎችን ያስቆጣና ያስመረረ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል። ብዙዎች አለምንም ማስጠንቀያያ በላያቸው ላይ የቤታቸው ጣሪያ እንዲፈርስ የተደረገ መሆኑ ሲነገር ከፊሎቹም ያለምንም ምትክ እና ያለምንም ካሳ ከቤታቸው እንዲወጡ የተደረጉ መሆናቸው ተረጋግጧል። ምትክና ገንዘብ ተሰጥቷቸዋል የተባሉትም የተሰጣቸው ቤት መስኮትና በር ያልተገጠመለት፤ የመጸዳጃ አገልጎት የሌለው ሲሆን ቤቱ እስኪያልቅ ድረስ በቀድሞ ቤታቸው ለመቆየት ቢገደዱም በላያቸው ላይ ቤታቸው የፈረሰባቸው መሆኑን ይናገራሉ፡፤
#የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ማስተባበሪያ አገልግሎት ሰኞ ዕለት በሰጣው ሳምንታዊ መግለጫ በኢትዮጵያ የተከሰተው የተምች መንጋ በኢትዮጵያ ስድስት አካባቢዎች በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑን ገልጾ ሁኔታውን ለመቆጣጠር ከተመድ የምግብና የእርሻ ድርጅት ጋር በመተባበር የተደረገው መድሃኒት የመርጨት ተግባር 35 ከመቶ የሚሆነውን ቦታ የሸፈነ መሆኑንና እንዲሁም ሌላ 26 ከመቶ የሚሆን ቦታ ለመሸፈን ዕቅድ የተያዘ መሆኑን ተገልጿል። በተጨማሪም ከአየር ንብረት መረጃዎች በመነሳት መጭው የክርምት ወር በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደብቡ ምዕራብ እና በማዕከል የሚዘንመው ዝናም አጥጋቢ መሆኑን እንዲሁም በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በደቡብ ምስራቅ የሚጥለው መጠናኛ መሆኑን የተነበየ መሆኑም ጠቁሞ የጎርፍ አደጋን ለመከላከል ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል። በጎርፍ አደጋ ሊጎዱ የሚችሉ 230 ቦታዎች ተለይተው እንዲታወቁ የተደረጉ ሲሆን ጉዳት ሊደርስባችው ለሚችለው የተለየ እርዳታ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉም ተገልጿል።
#የግብጹ ፕሬዚዳንት አል ሲሲ የአባይ ተፋሰስ ሀገሮች በካምፓላ ዩጋንዳ በሚያደርጉት ስብሰብስ ለመካፈል ወደ ካምፓላ ሄደዋል ። በአባይ ግድብ ተብዬው ግንባታ የተነሳ ግብጽ ተቃውሞዋን ስታሰማ የቆየች ሲሆን ቀስ በቀስም ዩጋንዳና ሌሎች ሀገሮችን ወደ ጎራዋ መሳቧ ሊታወቅ ተችሏል። ግድቡ ከተጠናቀቀ የአባይ ውሃ ድርሻዬ ይቀንሳል በሚል ግብጽ ያላት ስጋት ትክክል ነው ያሉ ታዛቢዎች ግብጽ ግን ያላትን የአንበሳ ድርሻ ለመጨመር በመፈለግ–በበረሃ አዲስ ከተሞችን መስርቶ ሚሊዮኖችን ለማስፈር በመፈለግ- የግል ስግብግብነትና እያሳየች መሆኑ ጠቅሰዋል ። ለግብጽ አመቺ ሆኖ የተገኘው ሀቅ ግን በአባይ ግድብ ስራ ላይ ወያኔ ራሱ ፈጽሞ ያለው ሻጥር ነው ። በቅድሚያ ለግንብታው የሚሆን ገንዘብ ሊያገኝ አለመቻሉ ሲጠቀስ በዚያው ደረጃ ደግሞ ይህ ግዙፍ ግድብ የሚፈልገውን ግዙፍ ቱቦዎች (ተርባይን) ውዳቂ የሆነውና በሙስናው ጄኔራል ክንፈ የሚመራው የወያኔ ሜቴክ እሰራለሁ ብሎ መድረቁ ነው ። የግድቡ ስራ ቢያንስ ለሁለት ዓመታት መጎተቱትን ሰሪዎቹ ራሳቸው አምነዋል ያሉት ውስጠ አዋቂዎች የወያኔ ሜቴክ ከቻይና ጋር በማበር ከዚህ ቀደም ፋና የሚል ስም ሰጥቶ የእጅ ቴሌፎንና ቴሌቪዥንም እሰራለሁ -ብሎ- -እንደከሸፈበትም አስታውሰዋል ።ግብጽ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ ካለብኝ በሚል በቂ ዝግጅት ያደረገች ሲሆን የኢትዮጵያን ሀገራዊ ጦር ፍርስርሱን አውጥቶ በመንደር ጄኔራሎች የተካው ወያኔ ግን በጉራ መደንፋት ላይ አተኩሮ ይገኛል ። በቀድሞ አገዛዞች የግብጽ ወኪሎች የሆኑ ዜጎች ወደ ጣናና አባይ እንዳይጓዙ ክልክል የነበር ሲሆን ወያኔ ግን በባህር ዳር እንዲንቀሳቀሱ መፍቀዱም መረሳት የለበትም ተብሏል ። በተጨማሪ ወያኔ ከሱዳን ጋር ተጣብቆ ጸረ ግብጽ አቅዋም ከመያዙ ሌላ ከነዩጋንዳ፤ ደቡብ ሱዳን ወዘተ በመጋጨቱ ለግብጽ አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል ተብሏል ።
#ኦሮሚፋ ቋንቋን በላቲን ፊደሎች (ቁቢ ) መጻፍ የሚለውን አቅዋም የአሜሪካ መንግስት የእርዳታ ፕሮግራም አበረታቷል፤ደግፏል የሚል ክስ ተሰንዝሯል ። ወያኔ በቁቢ ይሁን ብሎ የወሰነው በቂ ጥናት ላይ ተንተርሶ ወይም ሕዝብን አማክሮ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ላይ ባለው ጥላቻ የግዕዙን ፊደል የአማራ በሚል ከኦሮሞ ጽንፈኞች ጋር ተስማምቶ መሆኑ ታውቋል ተብሏል ። በቅርቡ በበርካታ የደቡብ የኦሮሞ ትምህርት ቤቶች በተደረገ ጥናት ብዙዎቹ ተማሪዎች የቁቢ ንባብ ችግር እንዳላቸው ሊታውቅ ተችሏል ያሉ ታዛቢዎች ልጆች በእናት አባታቸው ቋንቋ መማራቸው ጠቅሚ መሆኑ የሚካድ ባይሆንም ሁሉንም ሊያገኝና ሊጠቅም የሚችለውን ፊደል በጥላቻ አሽቀንጥሮ መጣሉና በርከት ያለው ሕዝብ ግንኙነቱን ከባእድ ማድረጉ ለሀገርም ለሕዝብም የሚበጅ አይደለም ብለዋል ። የሶማሌ ቋንቋ በላቲን የተጻፈው ሌላው አማራጭ አረብኛ በመሆኑና ባለመፈለጉ ነው ያሉ ክፍሎችን ኦሮሚፋም ሆኑ ሌሎቹ ቋንቋዎች በግእዝ ፊደል ቢጻፉ ምንም ችግርና ጉዳት ባልፈጠሩ ነበር ብለዋል። ኢትዮጵያን ማዳከምና መከፋፈል ዓላማቸው የሆነው ምዕራባውያን ቁቢን መምረጣቸውና መደገፋቸው ከቅን ልቦና ሳይሆን በሕዝብ መሃል ልዩነትን ለማስፋፋት ነው ተብሏል።
#ወያኔ ብዙ ገንዘብ ተከፍሎት በአዲስ አበባ አስከፍቶ የነበረውን የቱርኮች ትምህርት ቤት የቱርክ መንግሥት የሽብርተኞች ነው በማለቱ አሳልፎ ሰጥቷል ተባለ ። የትምህርት ቤቱ ሀላፊዎችና መስራቾች የአክራሪው ፋቱላህ ጉለን ተከታዮች ሲሆኑ ይህ ቡድን ደግሞ የቱርኩ ኤርዶጋን መፈንቅለ መንግስት የሞከረብን ነው በሚል በሽብርተናነት እንደከሰሰውም ይታወቃል። ከቱርክ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያለው የወያኔ ፕሬዛዳንት አማላጅ ሆኖ ትምርት ቤቶቹ ለቱርክ መንግስት እንዲሰጡ ረድቷልም የሚል ዘገባ አለ።
#ከስሙ በስተቀር ባለቤትነቱ የወያኔ የሆነው “የኢትዮጵያ አየር መንገድ” በ3 ቢሊዮን ዶላር ወጭ አስር A350S ኤርባስ በመባል የሚታወቁትን የፈረንሳይ የመጓጓዣ አውሮፕላች ለመግዛት አንዳቀደ ብሉምበርግ ዘገቦ፣ ስምምነቱ በዚህ ሳምንት ውስጥ ፈረንሳይ ውስጥ በሚደረገው የአየር በረራ ትዕይንት አንደሚጠናቀቅም አያይዞ ገልጿል። የወሮበላዎች ጥርቅም የሆነው ወያኔ በ26 ዓመት አገዛዝ ዘመኑ፣ አገሪቱንን ትውልድ ከፍሎ የማይጨርስው አዳ ውስጥ አንዳልዘፈቀ ሁሉ፣ 8 ሚሊዮን የአገሪቱ ዜጎች ለአስከፊ ረሀብ በተጋለጡበትና ድረሱልን አያሉ ባሉበት ባሁኑ ሰዓት፣ ይህ ዓረመኔ ቡድን “ከሰላም ባስ” ባልተለየ የግል ኩባንያው ያደረገውን አየር መንገድ ለማስፋት በቢሊዮኖች ሲያፈስ ማየት ወያኔያዊ አብሪቱን ሊያስተነፍስለት ለተነሳሳው ሕዝባዊ አመጽ የበለጠ ነዳጅ የሚሰጥ አንጅ ሌላ ሊሆን አይችልም የሚሉ ታዛቢዎች ብዙ ናቸው።
#ማክሰኞ ሰኔ 13 ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚክበረውን የስደተኞች ቀን በተመለከተ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ይህን ቀን አክባሪ ነን ባዮች በርካታ የምዕራብ ሀገሮች ድንበራቸውን አጥረውና ዘግተው ስደተኛ አንቀበልም ባይ መሆናቸውን ጠቁሟል። ወደ ውጭም በሀገር ውስጥም የተፈናቀሉ ቁጥር ወደ 70ሚሊዮን ደርሷል ያሉ ክፍሎች የስደት ምክንያት ከቁም ነገር መግባት የለሌበት ነው ሲሉ አስምረውበታል ። ዛሬ የኤኮኖሚ ስደተኛ በሚል ሚሊዮኖችን ከድንበራቸው ሊያርቁ ወይም የጥገኝነት መብት ሊከለክሉ የተነሱት እንግሊዞ፤ ጀርመኖች፤ አይሪሾች፤የኖርዌይ፤የስዊድንና የኤንማርክ ተወላጆች ሁሉም በረሃብና ችግር የተነሳ ወደ አሜሪካ የተሰደዱ እንድነበርም ተጠቅሷል ። ከበለጸገች ሀገር የሚሸሹ የሚሰደዱ ሚሊዮኖች ይኖራሉ ብሎ መገመት አይቻልምና ለስደት ዋናው ምክንያት በሀገር ውስጥ መብት ተከብሮ የሚኖርበት ሁኔታ መጥፋት ግልጽ ነው ሲል ኮሚቴውም አብራርቷል ። ስደት የሞት አደጋን ያዘለ መሆኑ በሟቾቹ ቁጥር የተረጋገጠ ሆኖ ሳለ ብዙዎች ወደ ስደት የሚያቀኑት አለመሰደዱ ገሃነም ሆኖባቸው ነው ማለት ነው ሲል ኮሚቴው አብራርቶ የወያኔ ዘረኛ ጨቋኝ አገዛዝ፤ ያለው የከሰረ ኤኮኖሚና ረሃብ ዋናው ተጠያቂ ነውና ለዚህ ሁኔታም ወያኔን የሚታደጉት ምዕራባውያን በጋራ ተጠያቂ ናቸው ሲል አቅርቦ በየቦታው በሀገራችን ስድተኞች ላይ የሚደርሰውን በደልም አውግዟል።
#የግንባታ ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር መስሪያ ለዋና መስሪያ ቤትነት ያገለግል ዘንድ ለዓምስት ዓመት 120 ሚሊዮን ብር ከፍሎ ባለ ብዙ ፎቅ ሕንጻ ተከራየ የሚለው ዓይን ያወጣ ዜና በረሃብ ከምትሰቃየው ኢትዮጵያ ደርሷል። ሚኒስቴሩ የነበረው የቀድሞ ቢሮ በቂው እንደነበር የጠቀሱት ታዛቢዎች በገቢሩ መቸም ተደንቆ የማያውቀው መስሪያ ቤት ይህን ያህል ገንዘብ ለቢሮ ማባከኑ በጣም አጠያያቂና አሳዛኝም ነው ሲሉ አቅርበዋል። ህንጻው የተሰራበት መሬት ቀደም የአትሌት ምሩጽ ይፍጠር ነው የተባለ ሲሆን መሶቡ ሲገለጥ ዋናው ተጠቃሚ ወያኔ ወይም የክልል አንድ ስው ለመሆኑ ምንም አያጠራጥርም ያሉት ውስጠ አዋቂዎች ሙስናና በስልጣን ዋልጌነት በዚህም ይገለጣል ብለው ተችተዋል ።
#የካታር ወታደሮች ከኤርትራና ከጂቡቲ ወሰን አካባቢዎች ከተነሱ በኋላ ሻዕቢያ ወታደሮችን ልኮ ቦታውን በመቆጣጠሩ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት የፈጠረ መሆኑ ታውቋል። ጂቡቲ የሻዕቢያ ድርጊት ከማውገዝ በላይ ክስ ያሰማ ሲሆን ኢጋድ የተባለው ተቋምና የአፍርካ ህብረት የተፈጠረውን ውጥረት እንዲያቀዘቅዙ ለሁለቱም አገሮች ጥብቅ ማሳሰቢያ ልከዋል።
Average Rating