www.maledatimes.com የዶባ (ራያ) ነገር - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የዶባ (ራያ) ነገር

By   /   June 27, 2017  /   Comments Off on የዶባ (ራያ) ነገር

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 30 Second

…………………………………
ጌኦርግ ሄግል የተባለው ጀርመናዊ ፈላስፋ “ አንዳንድ ሰዎች እና አምባገነን መንግስታት ከታሪክ ምንም ነገር እንዳልተማሩ ወይም ካገኙት ትምህርት ምንም እንዳልተጠቀሙ ተሞክሮና ታሪክ አስተምሮናል” ብሏል። ሄግል ስለ ሕይወት ባለው ፍልስፍና የማይስማሙ ብዙ ሰዎች ይኑሩ እንጂ በዚህ አባባሉ የማይስማሙ ሰዎች ግን እምብዛም አይኖሩም። ሰዎች ከታሪክ ለመማር ያለመቻል ከባድ ችግር ያለባቸው መሆኑ በእጅጉ ያሳዝናል

ሰሞኑን የትግራውያን አክቲቪስቶችን ትንፋሽ ቁርጥ ቁርጥ አድርጎ ልብ ድካም የሚያሲዝ የፖለቲካ ዱብዳ ገጥሟቸዋል። ሄግል እንዳለው እነዚህ ሰዎች ከታሪክ የተማሩ እንዳልሆኑ በየፔጆቻቸው ከሚለቀልቁት መረዳት ይቻላል ። ይሄ ትንፋሽ የሚቆራርጥ ጉዳይ የመጣባቸው ከራያና ከራያ ልጆች አካባቢ የወደቀ ትልቅ የፖለቲካ ቮልካኒክ ፍንዳታ ነው።ራያዎች በአንድ ድምፅ << አማርኛ ተናጋሪ እንጅ ትግሬ አይደለንም >> እያሉ ነው።ይሄን የራያ ህዝብ ጥያቄ ተከትሎ በየፔጁ የሚታየው ምላሽ ጥያቄውን ስለመፍታት ሳይሆን ጠያቂውን ስለመጨፍለቅ ፣ ስለመደምሰስ ነው ። ሰዎች ከታሪክ ለመማር ያለመቻል ከባድ ችግር ያለባቸው መሆኑ በእጅጉ ያሳዝናል።

በመሰረቱ ዛሬ ራያ የሚባለው ህዝብ እና አገር ከስረ መሰረቱ ከተመለከትነው ጉልህ ታሪክ ያለው በሃያልነቱ የሚታወቀው ዶባ የሚባል ህዝብ እና አገር ነበር ። ከ600 አመታት በፊት ጀምሮ የዶባን ጀግና ህዝብ በፍቅርና በጋብቻ እንጅ በሃይል ማስገበር የማይቻል እንደነበር ታሪክ ይነግረናል ። አፄ አምደፂዮን ፣አፄ ዘርአያእቆብ ፣ አፄ አስክንድር ፣አፄ አምደፂዮን ከዶባ ህዝብ ጋር በጋብቻ እየተሳሰሩ ያስተዳድሩ እንደነበር እነ ቼሩሊ እና ዘፍራንሲስኮ አልቫሬዝ ፅፈውታል ። ይሄ ዶባ የሚባለው ህዝብ አሁን ያለበትን አካባቢ ጨምሮ እስከ ሰሜን ኢትዮጵያ የራሱ ግዛት ነበር ። ከኦሮሞ ፍልሰት በኋላ የዶባ ህዝብ ራያ እየተባለ ይጠራ ጀመር ። ይሄ ህዝብ የራሱ ማንነት ያለውና ከትግሬ ጋር የሚያስተሳስረው ምንም ነገር እንደሌለ ማንም የሚያውቀው ሃቅ ነው ።

አሁን ዘግይቶም ቢሆን የራያ ህዝብ (ዶባ) ታፍኖ የኖረውን ጩህቱን እያሰማ ነው። ይሄ የራያ ህዝብ ጥያቄ መቼ እንደሚመጣ አላውቅም ነበር እንጅ ከታፈነበት ፈነቃቅሎ እንደሚወጣ ስድስተኛው የስሜት ህዋሴ ሲያሸተው ነበር ።
ህዝብ በታፈነ ቁጥር መተንፈሻ ይፈልጋል ። ይሄ የተፈጥሮ ህግ ነው ። ብልሆች ቀድመው ይሄን ህግ ያከብራሉ ። መተንፈሻውን የተነፈገ ህዝብ ግን ላዩ ላይ የተመረገበትን የአገዛዝ ኮንክሪት ደረማምሶ መውጣት ያለና የነበረ ወደፊትም የሚኖር ሃቅ ነው። አሁንም መፍትሄው የራያን ህዝብ ጥያቄ በውል ተገንዝቦ መፍታት እንጅ በሃይል ለመጨፍለቅ መሞከር እዳው ብዙ ነው።
#ቬሮኒካ መላኩ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on June 27, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 27, 2017 @ 7:22 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar