www.maledatimes.com ፍኖተ ነጻነት እንደገና ለህትመት በቃች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ፍኖተ ነጻነት እንደገና ለህትመት በቃች

By   /   October 24, 2012  /   Comments Off on ፍኖተ ነጻነት እንደገና ለህትመት በቃች

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 20 Second

ፍኖተ ነፃነት የየአንድነት ፓርቲ ቀድሞው ጠ/ሚ/ር አቶ መለስ ዜናዊ የሞቱ ዕለት ባወጣው ልዩ እትም የተነሳ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት አላትምም ብሎ ያገገደው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዛሬ በአዲስ አበባ እና በመላው ኢትዮጵያ ታትሞ መበተኑን የ የአንድነት ፓርቲ ኤዲቶሪያል ቦርድ አስታወቁ። በኢትዮጵያ የሚገኙ ማንኛውም የግል እና የመንግስት ማተሚያ ቤቶች በመንግስት በተዘዋዋሪ በሚደረግባቸው ፖለቲካዊ ጫና ምክንያት የሚያትመው ማተሚያ ቤት በመጥፋቱ የተነሳ አቶ መለስ ዜናዊ ከሞቱ ጀምሮ ያልታተመው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዛሬ በኢትዮጵያ የታተመው በአንድ የግል ማተሚያ ቤት መሆኑን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።

የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ ብቸኛዎቹ ደፋር ጋዜጦች ፍትህ እና ፍኖተ ነጻነት እንዳይታተሙ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን፤ ፍትህ “አዲስ ታይምስ” በሚባልና ድሮ ይታተም የነበረን መጽሔት ስም በመጠቀም በመጽሔት መታተም ጀምራለች። ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ግን ስሟን ሳትቀይር ዛሬ በኢትዮጵያ ታትማ እንድትወጣ ያደረገው ማተሚያ ቤትን ብዙዎች በአድናቆት ተመልክተውታል። ማተሚያ ቤቱ ፍኖተ ነጻነት ማተሚያ ቤት በፍትህ ሚ/ር ያልታገደ ጋዜጣ በመሆኑ ለማተም ግድ የለኝም” በሚል መንፈስ ይህን ጋዜጣ አትሞ ማሰራጨቱና በመንግስት የሚደርስበትን ጫና ወደ ኋላ ማለቱ ብዙዎችን ያስደሰተ ከመሆኑም በላይ ጋዜጣው ታትሞ ከመሰራጨቱ ገበያ ላይ መጥፋቱንም ከአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል።

ፍኖተ ነጻነት እና ፍትህ ጋዜጣ እንዳይታተሙ በመንግስት ፖለቲካዊ ጫና መደረጉ በሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ላይ የተቃጣ ዱላ መሆኑን የተለያዩ የሰብ አዊ መብት ተሟጋቾች ሲገልጹ እንደከረሙ ይታወሳል።
ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ የአንድነት ፓርቲ ያሳትማት እንጂ ሚዛናዊ የሆኑ ዘገባዎችን ለሕዝብ በማድረስ “ሰፊ የሚድያ ሽፋን ያለው መንግስት ራሱ በጋዜጣው መድረክ ላይ እንዲጠቀም” የጋበዘች ነጻ ጋዜጣ ናት። የፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ በPDF በተወሰኑ ሰዓታት ውስጥ በኦንላይን ይሰራጫል ተብሎ ይጠበቃል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 24, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 24, 2012 @ 11:27 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar