* አንድ አሸባሪ ራሱን በራሱ አጥፍቷል
* 10 ሰዎች ቆስለዋል
* አንድ ሴትን ጨምሮ አምስት ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል
የሳውዲ ደህንነት ልዩ ግብረ ኃይል በዛሬው እለት ታላቁን የመካ ካዕባ መስጅድ ለማጥቃት የተደረገ ሙከራን ማክሸፉን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሜ/ጄኔራል መንሱር አልቱርኪ አስታውቀዋል ።
ከደህነት የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ጥቃቱን ለመከዎን ሶስት ቡድኖች ሁለቱ ቡድኖች ከመካ ሶስተኛው ቡድን መሰረቱን ያደረገው ጅዳን እንደነበር ተጠቅሷል ። የመጀመሪያው ሁለተኛው የጥቃት ሙከራዎች መካ ውስጥ በተለያዬ ቦታ ተደርሶባቸው መክሸፋቸው ታውቋል ። ጥቃት ሊያደርሱ ከነበሩት አሸባሪዎች መካከል አንዱ መካ ውስጥ አጅያድ በተባለው መንደር በክትትል ተደርሶበት እጁን ለጸጥታ አስከባሪዎች እንዲሰጥ ቢጠየቅም ፈቃደኛ አልሆነም ተብሏል ።
አሸባሪው እጁን አልሰጥም በማለት በጸጥታ አስከባሪዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ የነበረ ቢሆንም ማምለጫ ሲጠፋው ራሱን የታጠቀውን ቦምብ ራሱን በራሱ ማጥፋቱን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ተናግረዋል ። በተኩስ ልውውጡ ስድስት ያህል ሰላማዊ ሰዎችና አምስት የጸህንነት ጸጥታ አስከባሪዎች የቆሰሉ መሆኑም ታውቋል ።
ከሽብር ጥቃቱ ጋር በተያያዘ አንድ ሴትን ጭምሮ በአጠቃላይ አምስት ያህል ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን በመገናኛ ብዙሃን የተሰራጨው መረጃ ያስረዳል ።
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓም
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating